www.maledatimes.com የህወሃት/ኢህአዴግን የግፍ አገዛዝ በማስወገድ በምትኩ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የህወሃት/ኢህአዴግን የግፍ አገዛዝ በማስወገድ በምትኩ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት

By   /   July 16, 2013  /   Comments Off on የህወሃት/ኢህአዴግን የግፍ አገዛዝ በማስወገድ በምትኩ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት

    Print       Email
0 0
Read Time:16 Minute, 54 Second

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት
Ethiopian National Transitional Council
የህወሃት/ኢህአዴግን የግፍ አገዛዝ በማስወገድ በምትኩ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት
የመተካት ሂደትና የሽግግር ምክርቤቱን የውስጥ ጉባኤ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
የህወሃት/ኢህአዴግን የግፍ አገዛዝ በማስወገድ በምትኩ ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግሥት የመተካት ሂደት ላይ የተዘጋጀው ታሪካዊ
የምክክር ጉባዔ እና የሽግግር ምክር ቤቱ የውስጥ ጉባኤ ሰኔ 25 እስከ 27 ቀን 2005 (July 2-4, 2013) በሸራተን ሲልቨር ስፕሪንግ /
ሜሪላንድ (Silver Spring, MD) ከተካሄደ በኋላ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
በምክክር ጉባዔው ላይ ሁሉም የሀገራችን ኢትዮጵያ ጉዳይ በለቤት የሆኑ (stakeholders)፤ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሴቶችና ወጣቶች
ማህበራት፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ድርጀቶች፣ የሚዲያ ተቋማት፤ ታዋቂ ምሁራን/ግለሰቦችና ተጋባዥ እንግዶች የኢትዮጵያ ብሔራዊ
ሽግግር ምክር ቤት አካባቢ ምክር ቤት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በተለያዩ ወቅት በመግለጫዎቻችን እንደገለፅነው የዚህ ጉባኤ ዋና አላማ ሁሉም
የህብረተሰብ ክፍልና የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላት ተገናኝተው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አስከፊ ስርአት በማስወገድና
ከሁሉም በላይ ደግሞ ከተወገደ በኋላ በምን ሊተካ እንደሚችል አማራጮቻቸውን የሚቀርቡበት የምክክር ጉባኤ ነበር።
አስቀድሞ ያልተቀናጀና እቅድ የሌለው የሽግግር ስርአት የሚያስከትለውን መዘዝ ዛሬ በግብጽና በሌሎች አገሮች ላይ እያየነው ነው። የህዝብ
ትግልና መስዋእትነት የሚፈለገውን የዲሞክራሲና የነጻነት ራእይ የሚያመጣው አስቀድሞ የድህር-ወያኔ የሽግግር ወቅትና ስርዓት ምን
መምሰል እንዳለበት ሁሉም ባለድርሻ ሲመክርበት እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት በጽኑ ያምናል። ለዚህም ነው የዚህን
ጉባኤ አስፈላጊነት በማመንና ጠንክሮ በመስራት እውን እንዲሆን ያደረገው።
ይህንን መሰረት በማድረግ በተባበረ ሃይልና በተቀናጀ ህዝባዊ ትግል ስርዓቱን አስወግዶ ወደ ዲሞክራሲ መንገድ የሚወስድ ሁሉን አቀፍ
ህዝባዊ የሽግግር መንግስት ማቋቋም አስፈላጊነት የሽግግር ምክር ቤቱ ያቀረበውን ሀሳብ የጉባኤው ተሳታፊዎች ተስማምተውበታል። ሁሉን
አቀፍ የሽግግር መንግስት አስፈላጊነት በሽግግር ምክር ቤቱ ከተነሱት ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል፤
• ስርአቱ መወገድ አለበት ለዚህም ተባብራችሁ ታገሉ፤ ትግሉ የጋራ ድሉም የጋራ ይሁን የሚለዉን የአብዛኛዉን ህዝብ ጥያቄ
ሰለሚመልስ
• ከለዉጥ በሗላ ምን ሊፈጠር ይችላል ለሚለዉ ጥያቄ/ፍራቻ ምላሽ ስለሚሰጥ
• የሽግግር ሂደቱ ቅድመ ዝግጅት ካሁኑ መጀመሩ ሀገሪቷ ወደከፋ ችግር ወይም ብጥብጥ እንዳትገባ ዋስትና የሚሰጥ በመሆኑ
• የህዝቡ የትግል ዉጤት በብልጣ ብልጦችና በባእዳን ተድእኖ እንዳይሰረቅ ዋስትና ስለሚሰጥ
• ለሽግግር መንግስት ዝግጅት ከሚካተቱና በሂደቱ ከሚመለሱ ጥያቄዎች ውስጥ ከብዙ በጥቂቱ – ይህ ስርአት ሲወድቅ የጦር
ሰራዊቱ ሚና ምን ይሆናል? በየደረጃው ያሉ የወያኔ/ኢህአዴግ ባለስልጣኖችና አጋሮቻቸው እጣ ምን ይሆናል? የእነዚህ
ጥያቄዎች መልስ ማግኘት፤ የወያኔ/ኢህአዴግ ባለስልጣናት፤ የፀጥታ ሀይሎች፤ የወታደራዊ ሀይል አባላት፤ በማንኛውም ሁኔታ
በሚፈጠረው አጋጣሚ ከህዝብ ጋር ለመወገን ብርታቱን ይሰጣቸዋል። የወያኔ አገዛዝን እየከዱ ከህዝብ ጋር ለመወገን
ለሚወስኑ ግለሰቦች መንገድ ስለሚከፍት
• ከላይ የተዘረዘሩትን መሰረት ያደርገ ስምምነትና ትብብር፤ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ አስተማማኝ
አማራጭ ሆኖ መቅረብ ስለሚያሰችል
85 S. Bragg Street
Alexandria, VA 22312, USA
Tel: 1-571-335-4637
+44-7958-487-420
www.etntc.org
contact@etntc.orgየአፈጻጸም ሂደቱን በተመልከተ የሽግግር ምክር ቤቱ የሚከተለውን ረቂቅ (proposal) አቅርቧል፤
1. ሁሉአቀፍ ህዝባዊ የሽግግር መንግስት በኢትዮጵያ እንዲቋቋም የሚያስችል ዝግጅት በአስቸኳይ ይጀመር
2. የሽግግር መንግስት የቅድመዝግጅት ኮሚቴ ይቋቋም
3. የሽግግር ወቅት ቻርተር የሚያረቅ ቡድን ይሰየም
4. የወያኔን ስርዓት ለማስወገደ ሀገርአቀፍና ዓለማቀፍ የህዝባዊ እምቢተኝነት ዘመጃ ይታወጅ
5. የህዝባዊ እምቢተኝነት ዘመቻውን የሚያቀነባበር ግብረሃይል ይቋቋም
የምክክር ጉባኤው ተሳታፊዎች ያቀረቧቸውን አማራጮችንና የተደርገውን ውይይት በተመለከተ በ 7/7/2013 ባወጣነው ሪፖርት ላይ
መግለጻችን ይታወሳል። (ለማንበብ እዚህ ይጫኑ)
ከዚህ ጥልቅና ሰፊ ውይይት በኋላ የሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ስምምነት ተደርሷል።
1. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሽግግር ምክር ቤት ያቀረበው የሽግግር ሂደት አማራጭ ከሞላ ጎደል በምክክር ጉባዔው ተሳታፊዎች ካቀረቧቸው
አማራጮች ጋር ተመሳሳይነት ስላለው የመነሻ ሰነድ ሆኖ እንዲወሰድና የመስማሚያ መጨረሻ ሰነድ የሚያዘጋጅ ኮሚቴ እንዲቋቋም
2. ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው፣ ዶ/ር መሳይ ከበደ፤ ዶ/ር ካሳ ከበደ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሽግግር ምክር ቤት ተወካይና የኢትዮጵያ ወጣቶች
ብሔራዊ ንቅናቄ ተወካይን ያካተተ ኮሚቴ ጉባኤው አቛቁሟል
3. ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው የኮሚቴው ሰብሳቢ እንዲሆኑ ተወስኗል
4. ኮሚቴው ሥራ የሚፈፅምበት የሚፈፅምበት የጊዜ ገደብ እንዲኖረውና የኮሚቴው ሰብሳቢ ይህንን እንዲያሳውቁ የምክክር ጉባዔው ተስማምቷል።
በመጨረሻም በዚህ ታሪካዊ የምክክር ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሽግግር ምክር ቤትና የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ መካከል
የተደረገው ስምምነት (memorandum of understanding) ለምክክር ጉባዔው ተነቧል። ስምምነቱም እንደሚከተለው ነው፤
1… የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነት ትግል ከግብ መድረስ ካልቻለበት አብይ ምክንያቶች አንዱ የድርጅቶች ጠንካራና ቆራጥ አመራር መስጠት
አለመቻል መሆኑ ታምኖበት ፀረ ኢትዮጵያ ፣ ፀረ ህዝብና ፣ ፀረ ዴሞክራሲ በሆነው የወያኔ/ኢህአዴግ ስርአት ላይ የጠራና
የማያወላውል አቋም መወሰድ አለበት። ይህም ማለት ስርዓቱ በአስቸኳይ መወገደ አለበት። ከወያኔ ስርዓት ጋር ለመደራደር ወይም
ምንም አይነት ስምምነት ላይ ለመድረስ መሞከር የትግሉ እንቅፋት እንደሆነ ታምኖበታል።
2… የወያኔን ስርዓት ለማስወገድ በሚደረገው ትግል የህዝባዊ እምቢተኝነት ዘመቻ እቅዶችን በመንደፍ ፣ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን
በማስተባበርና ፣በማከናወን በጋራ ይሰራሉ።
3… የወያኔን ስርዓት የሚተካ ሁሉን አቀፍ የሆነ የሽግግር መንግስት የማቋቋም ሂደት ቀደም ሲል ሊጀመር ሲገባው እስካሁን ድረስ ትኩረት
እንዳልተሰጠው እና ነገር ግን አሁን በአሰቸኳይ ዝግጅት መጀመር እንዳለበትና ይህንንም ለማሳካት የሽግግር ምክርቤቱና የወጣቶች
ንቅናቄ በፅናት አብረው ይሰራሉ።
4… ወጣት ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው የፖለቲካ ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉና በአመራር ደረጃ እንዲሳተፉ የሽግግር ምክርቤቱ
ከወጣቶች ንቅናቄ ጋር ሁኔታዎችን ያመቻቻል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሽግግር ምክር ቤት፤ በዚህ አጋጣሚ ይህ ታሪካዊ የምክክር ጉባዔ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍና ትብብር ላደረጉ፤ ጥሪያችንን
ተቀብለው ለዚህ ከፍተኛ ሃገራዊ ጉዳይ ምላሽ ለሰጡና ለተሳተፉ ወገኖች ሁሉ የአክብሮት ምስጋና ያቀርባል።
ከዚህ ታሪካዊ የምክክር ጉባኤ በኋላ በመርሃ ግብሩ መሰረት የሽግግር ምክርቤቱ የመንፈቅ አመት የውስጥ ጉባኤውን አካሂዷል። ጉባኤው
በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን አስተላልፏል። ውይይት ከተደርገባቸው ነጥቦች ውስጥ፤ የአባላትና የቻፕተሮችን ማደራጀት ስራ፤ የአቅም ግንባታ፤ ህገደንብ፤ ፖሊሲ፤ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ስለሚድረጉ ግንኙነቶችና ስምምነቶች፤
በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚደረጉ እንቅስቃሴዎችና ድርጅታዊ ስራዎች፤ ቀጣይ ተመሳሳይ የምክክር ጉባኤ፤ እና በሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ላይ
ውይይት ተደርጎ ውሳኔዎች ተላልፈዋል። ጉባኤው ከመጠናቀቁ በፊት በጎደሉ የአመራር አባላቶች ምትክ ሁለት አዳዲስ የአመራር አባላት
በመምረጥና የሽግግር ምክር ቤት ቀጣይ የውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ በጁላይ 2014 እንዲደረግ ውሳኔ ተላልፏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሽግግር ምክር ቤት አመራር አባላት ሙሉ ዝርዝር፤
አቶ ስለሺ ጥላሁን – አፈጉባኤ
ወ/ሮ መቅደስ ወርቁ – ም/አፈጉባኤ
አቶ ደምስ በለጠ – ፀሃፊ
አቶ ደርጀ ደምሴ – ም/ፀሃፊ
አቶ ሰለሞን ኤፍሬም – የፋይናንስ ሀላፊ
አቶ መንሱር ኑር – የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ
ው/ሮ ፊፊ ደርሶ
አቶ አበባየሁ አሉላ
ኢትዮጵያ ለዘላለም ተኑር!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሽግግር ምክር ቤት

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 16, 2013
  • By:
  • Last Modified: July 16, 2013 @ 12:25 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar