www.maledatimes.com የሰማያዊ ፓርቲ አደረጃጀት በድሬዳዋ ተገመገመ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሰማያዊ ፓርቲ አደረጃጀት በድሬዳዋ ተገመገመ

By   /   July 16, 2013  /   Comments Off on የሰማያዊ ፓርቲ አደረጃጀት በድሬዳዋ ተገመገመ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 1 Second

የሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት መዋቅር ውስጥ አንዱ የሆነው የድሬዳዋ አስተዳደር የሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር የስራ-እንቅስቃሴ ከሀምሌ 6-7/2005 ዓ.ም. ባሉት ቀናት የፓርቲው የስራ-አስፈጻሚ አባላት ተዘዋውረው ተመለከቱ፡፡
የስራ-እንቅስቃሴውን ለመጎብኘት የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ጌታነህ ባልቻ እና የጥናትና ስትራቴጂ ኃላፊ አቶ ወረታው ዋሴ ተገኝተዋል፡፡ ከጉብኝቱም በኃላ በድሬዳዋ አስተዳደር የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጋር አጠቃላይ በፓርቲውና በድሬዳዋ አስተዳደር መዋቅር ላይ ሰፊ ውይይትና ግምገማ በማድረግ የወደፊቱን የፓርቲውን ስራ በማጠናከር ሰላማዊ ትግሉን በሚያስቀጥሉበት ስራዎች ዙሪያ ተመካክረው የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በመጨረሻም ሁሉም አካላት የተጀመረውን ትግል እንደሚያጠናክሩ ይህንንም ለሌሎች በድሬዳዋ ለሚገኙ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች እንደሚያሳውቁ በመግለጽ የዕለቱ ውይይታቸውን አጠናቀዋል፡፡

 
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on July 16, 2013
  • By:
  • Last Modified: July 16, 2013 @ 2:39 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar