www.maledatimes.com 30ኛው የኢትዮጵያን ባህል እና ስፖርት ፌደሬሽን ዝግጅት እንዴት ተከበረ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

30ኛው የኢትዮጵያን ባህል እና ስፖርት ፌደሬሽን ዝግጅት እንዴት ተከበረ?

By   /   July 16, 2013  /   Comments Off on 30ኛው የኢትዮጵያን ባህል እና ስፖርት ፌደሬሽን ዝግጅት እንዴት ተከበረ?

    Print       Email
0 0
Read Time:31 Minute, 49 Second

30ኛው የኢትዮጵያን ባህል እና ስፖርት ፌደሬሽን ዝግጅት እንዴት ተከበረ? ESFNA 30th year report
ከተመሰረተ 30 ዓመት ያስቆጠረው የባህልና ስፖርት ፌዴሬሽኑ ሠላሳኛ ዓመቱን ከጁን 29 Eስከ ጁላይ 6
በሜሪላንድ ዋሽንግተን Aክብሯል። በዚህ ዝግጅት ላይ ምን ያህል ሰው Eንደተገኘ ከፌዴሬሽኑ በይፋ የተነገረ ነገር
Eስካሁን ባይኖርም ፣ ከ30ሺ ያላነሰ ሰው Eንደነበር መገመት ግን ይቻላል። ስቴዲየሙ በጠቅላላ 54ሺ ሰው
የሚይዝ ሲሆን፣ ቢያንስ ግማሽ ያሉ ቦታ ሞልቶ ታይቷል፡፡ በዚህ ውድድር በማሸነፍ ዋንጫ ለወሰደው የቨርጂኒያ
ቡድን Eንኳን ደስ Aላችሁ Eንላለን።
ይህ ዝግጅት በዓይነቱ ለየት ከሚልበት ነገሮች Aንዱ የሆነውን ሁሉንም Iትዮጵያዊ የማቀፍ ማEከልነቱን ዘንድሮም
Aስከብሯል ማለት ይቻላል። ውድድሩም በደመቀ መልኩ ነው የተከፈተው። የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት Aቶ ጌታቸው
ተስፋዬ የEንኳን ደህና መጣችሁ መልክት Aስተላለፈዋል – ልዩ ልዩ የመክፈቻ ስነ ሥርዓትም ተከናውኗል። የደመቀ
የመክፈቻ ዝግጅት ነበር ማለት ይቻላል።
ከዚያ ቀጥሎ ባሉት Aራት ቀናት፣ ማለትም ከሰኞ Eስከ ሃሙስ ድረስ በተለመደው መልክ የ30ዎቹ ክለቦች ውድድር
በወጣለት ፕሮግራም ተከናውኗል። Aንዳንድ ጊዜ የፕሮግራም መጋጨት Aልነበረም ለማለት Aይቻልም፣ ለምሳሌ
የAትላንታ ቡድን ሶስተኛ ጨዋታውን ያደረግው፣ ባልተዘጋጀበትና ፎርፌ በልቻለሁ ብሎ በተዘናጋበት ሰAት
Eንደነበር የቡድኑ ተጫዋቾች ለAድማስ ሬዲዮ ተናግረዋል። በዚህ Aጋጣሚ የAትላንታ ቡድን Aንዴ Eኩል ወጥቶ
፣ ሁለት ጊዜ ተሸንፎ ፣ ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ከመውረድ ለጥቂት ተርፎ መመለሱን መግለጽ ያስፈልጋል።
Aርብ ጁላይ 5 ቀን የነበረው የIትዮጵያ ቀን ዝግጅት፣ ለተወሰኑ ጊዜያት የመብራት መቋረጥ ከማጋጠሙና
ያልተዘጋጁ የሚመስሉ Aንዳንድ Aርቲስቶች ከመቅረባቸው በቀር የተወጣለት ነበር። የሰAት መራዘሙ ግን በተለይ
ልጆች ይዘው የመጡ ቤተስቦች ሲንገላቱና የግድ Aቋርጠው Eንዲሄዱ ማድረጉ የታየ ነውና የሰAት ጉዳይ
ሊታሰብበት የሚገባ ሆኖ Aግኝተነዋል። Eጅግ ደማቅ የሆነው ይህ የIትዮጵያ ቀን ዝግጅት የሙዚቃ፣ የሙዚቃዊ
ድራማ Eና የክብር Eንግዶች ንግግሮች የቀረቡበት ነበር። በዚህ ዝግጅት የሴቶች ጉዳይ ጎልቶ መነሳቱ ተገቢና
ወቅታዊ ሆኖም Aግኝተነዋል።
ከሰዉ ብዛትና ከሚታየው የAረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ብዛት Aንጻር ለጥቂት ጊዜ Iትዮጵያ ያለን ቢመስል
የሚደንቅ Aልነበረም። ይህ ሁሉ ህዝብ ለAንድ ሳምንት በAንድ ቦታ ከተሞ የሚጋነን የጸጥታ ችግር ሳይገጥም
ማለቁ Iትዮጵያውያን ጨዋ መሆናችንን ያሳያል። ለዚህ ሁሉ ከAሜሪካ ግዛቶች ቀርቶ ከAውሮፓና ከIትዮጵያ
ጭምር በርካታ ተሳታፊዎች ለተገኘበት ዝግጅት ምክንያት የሆነው የሰሜን Aሜሪካ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን
በመሆኑ Eንደ ተቋም ሊመሰገን ይገባዋል።
ይህም ሆኖ በፌዴሬሽኑ በኩል ችግሮች Aልነበሩም ማለት Aይቻልም፡ Aንዳንዶቹ ጥቃቅን፣ ሌሎቹ የጎሎ ችግሮች
፣Aንዱ ደግሞ በኛ Eምነት ትልቅ ችግር ሆኖ ያገኘነውም ነበር። ምንም ፌዴሬሽኑ የኛ ቢሆን፣ ችግሩን Eኛው
ካልነገርነው ሌላ ሊነግረው Aይችልምና Aንዳንዶቹን ማንሳት ግድ ነው።
ገና ሲጀመር ፣ የክብር Eንግዳ Aመራረጥ ላይ ችኮላና የመወሰን ችግር Eንደነበረበት ታይቷል። Eስከመጨረሻዋ
ደቂቃ ድረስ በፌዴሬሽኑ ድረገጽም ሆነ በለቀቃቸው ማስታወቂያዎች “Eንግዶቼ” ብሎ ከጠቀሳቸው ውስጥ ቢያንስ
Aራቱ ጭራሽ Aልመጡም። የብሄራዊ ቡድናችን Aሰልጣኝ Aቶ ሰውነት ቢሻው፣ Aትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰረት
ደፋር Eና ጢቂ ገላና ይመጣሉ ተብሎ የተነገረላቸው ግን ያልመጡ ናቸው። ለመሆኑ በርግጥ ግብዣውን
ተቀብለዋል? ወይስ ደብዳቤ ስልተላከላቸው ብቻ ነው ይመጣሉ ተብሎ የተወሰነው? ወይስ Eንመጣለን ብለው በኋላ
ላይ ነው ሃሳባቸውን የቀየሩት? ይህን የሚመሉስት የፌደሬሽኑ ሃላፊዎች ይሆናሉ። 30 ዓመት Eንደሞላው ትልቅድርጅት ግን Eንዲህ Aይነት ስህተት መኖር Aልነበረበትም። ከሆነም ደግሞ በግልጽ ምክንያቱን ለታዳሚው
መንገርና ይቅርታ መጠየቅ ያስፈልግ ነበር።
ሌላው ችግር በምግብና ደረቅ Eቃ ሻጮች ላይ የተፈጠረ ነው። Eነዚህ ምግብና ደረቅ Eቃ ሻጮች በያመቱ ገንዘብ
ከፍለው ድንኳን በመከራየት ዝግጅቱን ከኳሱ ያላነሰ የሚያደምቁ ናቸው። ብዙዎቹ ብዙ ገንዘብ Aውጥተው፣
በሳምንቱ ውስጥ ትርፍ ለማግኘት የተዘጋጁ ናቸው። Eነዚህ ነጋዴዎች ከሚያቀርቡት ቅሬታ Aንዱ የመጀመሪያውን
ሶስት ቀን መብራት ስላልተሰጣቸው ለሶስት ቀን ያህል ሥራቸውን Aለመስራታቸውን ነው። ይህም ከተከፈለው 3200
ዶላር Aንጻር የሶስት ቀን ኪሳራ Aስከትሎባቸዋል። ምግብ Aቅራቢዎቹ ይህንኑ ቅሬታቸውን በጽሁፍ ለፌዴሬሽኑ
Aሳውቀዋል፣ የሶስት ቀን ሂሳብ ተሰልቶ ማስተካከያ Eንዲደረግም ጠይቀዋል። መልስ Eየጠበቁም ይገኛሉ። የመኪና
ማቆሚያም የነዚሁ የነጋዴዎች ሌላው ቅሬታ ነው። ለድንኳን ለከፈሉ ቢያንስ ለAንድ መኪና ነጻ ማቆሚያ መሰጠት
ሲገባው፣ Eቃ ለመግዛትና ለማስገባት በወጡና በገቡ ቁጥር ለማቆሚያ 15 ብር በተደጋጋሚ መክፈል ነበረባቸው።
ሌላው ቅሬታቸው ከፔፕሲ ምርት በቀር Aታምጡ መባሉና Eሱንም ራሱ ፌዴሬሽኑ ነበር የሚሸጥላቸው። ከውጭ
ገዝተው ቢያመጡ የበለጠ Eንደሚቀንስ ይናገራሉ።
የሙዚቃ ሲዲና ዲቪዲ ለመሸጥ የተመዘገቡት በበኩላቸው፣ ሲዲ ለመሸጥ የተመዘገቡት Eነሱ ሆነው ሳለ፣ ሁሉም
ባለድንኳን በትላልቅ ስፒከር ሙዚቃ መልቀቁና፣ Aንዳንዶቹም ሲዲ ደርድረው ሲሸጡ Eየታየ ያንን የሚቆጣጠር
የፌዴሬሽኑ Aካል Aለመኖሩ በሥራቸው ላይ ተጽEኖ Eንዳሳደረ ይናገራሉ። ምግብ የሚሸጡትም፣ ፍላየር
የሚያድሉትም፣ የበጎ Aድራጎት ድርጅቶቹም ሁሉም Eነዚያን የሚያካክሉ ስፒከሮች Eንዲሰቅሉና ሙዚቃ ቤት
Eንዲመስሉ መፈቀድ Aልነበረበትም ነው የሚሉት።
ለፌዴሬሽኑ ከፍተኛውን ክፍያ በመፈጸም (ጎልድ ስፖንስር) የሆኑም ከችግሩ Aላመለጡም። ያን ያህል ገንዘብ
የከፈሉት Eንደሚፈልጉትና Eንደተስማሙበት ሊደረግላቸው ሆኖ ሳለ፣ ገንዘቡን Eስኪከፍሉ የነበረው Eንክብካቤ
ገንዘብ ከከፈሉ በኋላ ድራሹ Eንደጠፋ ነው የሚናገሩት። ከነዚሁ ድርጅቶች የAንዱ ተወካይ ሲናገሩ “ትልቁን
ገንዘብ ከከፈሉት ውስጥ Aንዱ ነን፣ ነገር ግን ድርጅታችንን በስፒከር Eንኳን ለማስተዋወቅ፣ ሜዳው ድረስ ወርደን
በተደጋጋሚ ማስታወስና መጨቅጨቅ ነበረብን” ይላሉ። ያም ብቻ Aይደለም – የፌዴሬሽኑ ሃላፊዎች ርስ በርስ
የሚነጋገሩ Eስከማይመስል ድረስ Aንዱ ያዘዘውን ሌላው Aያውቀውም ይላሉ። በተያያዘም “በድንኳናችን ውስጥ
ለሰዎች ስለ ሥራችን በርጋታ ማሰረዳት የነበረብን ቢሆንም ከፊት ለፊታችን ያለው ድንኳን የተሰጣቸው ሰዎች ፣
ከሥራቸው በማይገናኝ ሁኔታ በትልቅ ስፒከር የሚለቁት ሙዚቃ Eንኳን ለሰዎች ለማስረዳት ርስ በርሳችን Eንኳን
ማውራት Eንዲያቅተን Aድርጎናል ..” ይላሉ። የትኛው ድርጅት ከየትኛው Aጠገብና ፊት ለፊት መሆን Eንዳለበት
Eንኳን የተደረገ ጥናት Aልታየም። Eናም ትልቁን ክፍያ ፈጽመን፣ የፈለግነው ግን Aልሆነም …. ይላሉ።
ከዚህ ቀደም በነበሩት [ለምሳሌ በAትላንታ] የስፖርት በዓል ወቅት የነጋዴዎች ድንኳን ቅዳሜ ጠዋት ተተክሎ፣
ሁሉም ከሰAት Eቃውን Aስገብቶ ለEሁድ መክፈቻ ይዘጋጅ ነበር። በዘንድሮው የሜሪላንድ ዝግጅት ግን ድንኳን
መተከል የጀመረው ቅዳሜ Aመሻሹን ሲሆን፣ Eጣ ወጥቶ ድንኳኑ ተከፋፍሎ Eቃ ለማስገባት ጊዜው ባለመብቃቱ
Eሁድ መሸጥ በሚጀመርበት ቀን ገና ነጋዴዎች Eቃ ለማስገባት ተገደው ነበር። ይህም ሌላው የነጋዴዎቹ ቅሬታ
ነው።
የፌዴሬሽኑ Aመራር Aባላት ከውድድር በፊትና በውድድር ወቅት የተለያዩ ሰዎች መሆናቸው Eንዳለፈው ዓመት ሁሉ
ዘንድሮም ታይቷል። ከውድድር በፊት በቃለመጠይቆች የሚገቡት ቃል፣ በዚህ Aንድ ሳምንት ውስጥ የት Eንደሚገባ
Aይታወቅም። Aንዱ ማስረጃ የመግቢያ ባጅን የሚመለከት ነው።
ፌዴሬሽኑ በAሰራሩ፣ ሁልጊዜም ቢሆን ለሚዲያ ሰራተኞች የሚዲያ ባጅ ይሰጣል – ወይም መሰጠት Aለበት።
[ቢደላማ የጋዜጠኞች ማEከል – [ሚዲያ ሴንተር] ሊዘጋጅም ይገባ ነበር] … Eናም ሁልጊዜ ከውድድሩ Aንድ ወር
በፊት ፎቶ ላኩ ይባላል፣ ዘንድሮም ፎቶ የላክነው ከወር በፊት ነው። ነገር ግን ማንም Aስታውሶ መታወቂያውን
ያዘጋጀ ሰው Aልነበረም፣ ጭራሹኑ የተላከው ፎቶ ማን ጋር Eንደደረሰ Eንኳን ርስ በርስ መግባባት Aልታየም።
የመክፈቻው Eለት የደረሱ ጥቂት ጋዜጠኞች በስንት ሙግት Eዚያው EንደAዲስ ፎቶ ተነስተው መታወቂያ
ሲሰጣቸው፣ በማግስቱና ከዚያ በኋላ የደረሱ በሙሉ የሚዲያ መታወቂያ የሚሰጣቸው Aካል Aልነበረም። ጉዳዩ
ይመለከታቸዋል የሚባሉት Eንኳን Aንዱ በAንዱ ከማሳበብ በቀር ምንም ሊፈይዱ Aልቻሉም፣ የመግቢያው በርላይ የነበሩ Aንዳንድ የፌዴሬሽኑ ሰራተኞች “ሚዲያ ከመለፍለፍ በቀር ምን ይጠቅማል? ተዋቸው ሲፈልጉ ከፍለው
ይግቡ፣ ሳይፈልጉ ይመለሱ” ሲሉም ተደምጠዋል። በርካታ ጋዜጠኞች፣ ከሩቅ ከተማ ፎቶና ቪዲዮ ካሜራ ጭነው
መጥተው በር ላይ ለክፍያ ከመሰለፋቸውና ከፍለው ከመግባታቸው በተጨማሪ ፣ Eንደልባቸው ሰዎችን ለማነጋገርና
ሜዳ ውስጥ ገብተው ለመዘገብ Aልቻሉም። ለጋዜጠኞች መታወቂያ የሚሰጠው በር ላይ 20 ብር Eንዳይከፍሉ ብቻ
Aይደለም፣ ቁምነገሩ መክፈሉም Aልነበረም፣ ይልቁኑ ያለ ሚዲያ ባጅ በሁሉም ቦታ ተዘዋውሮ ለመስራትና ሰዎችን
ለማነጋገር Aለመቻሉ Eንጂ! .. ነገር ግን ሁልጊዜም “ዘንድሮ ችግር የለም” Eየተባለ ቀድሞ ይነገራል – ጊዜው
ሲደርስ ግን ችግር Aለ። የመግቢያ ባጅ ችግር የጋዜጠኞች ብቻም Aይደለም። የፌዴሬሽኑ መስራቾችና Aንጋፋ
የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ጭምር፣ በፊት Eንደሚደረግላቸው ዘንድሮ የመግቢያ ባጅ የሚሰጣቸው ጠፍቶ
Eየከፈሉ ሲገቡ ታይተዋል።
መኪና ማቆሚያ ቦታ ፈዴሬሽኑ ከሚተችበት ነገር Aንዱ ሆኖ ተገኝቷል። በድረ ገጹ ላይ የተወሰነ ቦታ በነጻ የቀረው
የጋራዥ ማቆሚያ ግን በ 5 ዶላር ማቆም Eንደሚቻል ቢገልጽም፣ ሰዎች ሲገቡ ግን የተተከለው ማሽን ከ15 ዶላር
በታች የሚቀበል Aልነበረም። ለቅናሽ የሚሆን ኮድ ማሽኑ ቢጠይቅም ድረ ገጹ ላይ ግን የለም፣ ስለዚህ 5 ዶላር
ብሎ የመጣ ሁሉ 15 ዶላር Eየከፈለ ለማቆም ተገዷል። Eንግዲህ በር ላይ የሚከፈልን Aማካይ 20 ብር ጨምሮ
Aንድ ሰው ስቴዲየም ለመግባት ብቻ በቀን 35 ዶላር ያወጣል ማለት ነው።
በየቦታው ስለተደረጉት የመዝናኛ ዝግጅቶች ብዙ Aቤቱታ Aለ – በሌላ ዘገባ Eንመለስበታለን። ነገር ግን ስለ
መጨረሻው የቅዳሜ ማታ የመዝጊያ የሙዚቃ ዝግጅት ማንሳት ግዴታ ነው። ይህ የመጨረሻው ዝግጅት የሚደረገው
በሰሜን Aሜሪካ የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ነው። ይህ ዝግጅት ፌዴሬሽኑ ጠቀም ያለ ገቢ ከሚያገኝበት ዝግጅት
Aንዱ Eንደሆነም ይታወቃል። ለዚህ ነው በምሽቱ ሌላ ቦታ ሙዚቃ የማይኖረውና ፌዴሬሽኑ ብቻ የሚያዘጋጀው።
የዘንድሮው ዝግጅት የተደረገው በሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ ትንሿ ዝግ ስቴዲየም ነው። ይህ ዝግ ስቴዲየም በ1955
ዓም የተስራ ሲሆን 15ሺ 450 ሰው ይይዛል። ታዲያ ፌዴሬሽኑ የሙዚቃ ዝግጅቱን Eዚህ ስቴዲየም ሲያዘጋጅ
ቢያንስ 10ሺ ሰው ቢመጣልኝ ብሎ መሆኑ Aይጠረጠርም .. 3 Eና 4ሺ ሰው ተጠብቆ ቢሆንማ ከስቴዲየም ይልቅ
ትልቅ Aዳራሽ ፌዴሬሽኑ ይከራይ ነበር ብለን Eንገምታለን። የሚገርመው ግን ይህ ዝግ ስቴዲየም ጨርሶ Aየር
ማቀዝቀዣ የለውም። ፌዴሬሽኑም የተከራየው ማቀዝቀዣ Eንደሌለው Eያወቀ ነው።
ነገር ግን በጁላይ ወር የዲሲና Aካባቢው ሙቀት፣ [ቀን ላይ በሜሪላንድ የሙቀቱ መጠን 101 ዲግሪ ደርሶ ነበር]
የAየር ማቀዝቀዣ በሌለው ቦታ ዝግጅት ማድረግ ለምን ተፈለገ? በሙቀት የተነሳ ችግር ቢፈጠር ማን ነው
ተጠያቂው? Aንድ ሰው 40 ብር ከፍሎ ሲገባ ከሙዚቃው ባላነሰ የሚፈልገው ቢያንስ የማይሞቅና የማይቀዘቅዝ
ቦታ ነው። Aዳጊ ወጣቶች ነበሩ፣ ደካማ Aዛውንቶች ነበሩ፣ ወጣቶች በላብ ተነክረዋል፣ ሴቶች ጸጉርና ልብሳቸው
ተበላሽቷል። ሙዚቃውን ከሚያየው ያላነሰ ብዛት ያለው ሰው ውሃ ፍለጋ ወዲያ ውዲህ ሲል ነበር፣ በዚያ ዝግጅቱ
በሚደረግበት ሌሊት Eንኳን ወጥተን Eንደለካነው ከሆነ የውጭው ሙቀት 82 ዲግሪ ነበር። በዚህ የሙቀት ወቅት፣
ማቀዝቀዣ በሌለው ቦታ ዝግጅቱን በማድረጉ ሊፈጠር ይችል ለነበረው ችግር ሃላፊነቱን ማን ነው የሚወስደው?
የመጣው ሰው 2ሺ Aካባቢ የሚገመት ሆነ Eንጂ፣ Eንደቦታው Aያያዝ 10ሺ ሰው ቢመጣ ኖሮ ስንት ሰው በሙቀት
መውደቅ፣ ስንቱም መታመምና ከዚያ በላይ ነገር ያጋጥም ነበር? ሆን ተብሎ Aየር ማቀዝቀዣ Eንደሌለው
Eየታወቀ ለሰዉ ጤንነትና ምቾት ምንም ሳይታሰብ ገና ለገና ብዙ ሰው ይይዛል ወይም ርካሽ ነው በሚል ምክንያት
ከሆነ ፌዴሬሽኑ የተከራየው ተጠያቂነት Aለበት። በዚህም በሙቀት የተሰቃየውን ታዳሚ ይቅርታ መጠየቅ፣ ድርጊቱን
ሆን ብሎ የፈጸመው Aካልም ሃላፊነት መውሰድ Aለበት። የስቴዲየሙ ሃላፊዎች ይህንን ቦታ ላለፉት 10 ዓመታት
ለንደዚህ ዓይነት ትልቅ ዝግጅት Aከራይተውት Aያውቁም። Aንዱ ምክንያታቸው Aየር ማቀዝቀዣም ሆነ ማሞቂያ
ስለሌለው ነው። Aሁንም Aከራዮቹ Eንደሚናገሩት ከሆነ በዚህ የፌዴሬሽኑ የማታ ዝግጅት ላይ ድንገት በሙቀት
የተነሳ ችግር ቢፈጠር በሚል Aምቡላንስ ደጅ Eስከማቆም፣ ልዩ የማቀዝቀዣ ክፍልም ለብቻ Aዘጋጅተው ነበር።
ይህንንም ያደርጉት Aከራዮቹ የዩኒቨርሲቲው ሃላፊዎች Eንጂ ፌዴሬሽኑ Aልነበረም።
የፌዴሬሽኑ በሆነው በዚህ የመጨረሻ ዝግጅትም 40 ዶላር ከፍሎ ለገባ ሰው Aንዲት የክትፎ ሳንዱች 13
ዶላር፣ ቤቱ ማቀዝቀዣ Eንዴሌለውና በሙቀት የተቸገረው ሰዉ ወደደም ጠላም ሌሊቱን ሙሉ 4 Eና 5 የሚጠጣው
ውሃ Eንደሚያስፈልገው Eየታወቀ Aንድ ውሃ 3 ዶላር መሸጥ ተገቢ ነው? ይህ Eሳት ለኩሶ፣ በጎን Eሳት ማጥፊያ
ለገበያ Eንደማቅረብ Aይቆጠርም? ለመሆኑስ ምግብና መጠጥ በዚህ ዋጋ Eንዲሸጡ የተፈቀደላቸው ነጋዴ ከሌሎችጋር በግልጽ ተወዳድረው ያገኙት ቦታ ነው? ሁልጊዜ ይደረግ Eንደነበረው ለምን ሌሎች ቀን ስቴዲየም በጸሃይ
ሲራወጡ የነበሩ ምግብ ሻጮችም በጨረታው Eንዲወዳደሩ ክፍት Aልተደረገም?
በመጨረሻ፣ የሚቀጥለውን ዓመት ውድድር ፌዴሬሽኑ Eዚያው ሜሪላንድ ሊደግመው Aስቧል የሚሉ
ጭምጭምታዎች ይሰማሉ። ካልሆነ Eሰየው፣ ከሆነ ግን ይህ በራሱ ሌላ ክርክር የሚያስነሳ ከመሆኑም በቀር
“Iትዮጵያውያንን Aንድ ማድረግ” የሚለውን የፌዴሬሽኑን Aቋም የሚጻረር ነው። Iትዮጵያውያን Aንድ የሚሆኑት
Eኮ ተመሳሳይ ከተማ ስለተሰባሰቡ ብቻ Aይደለም፣ Aንዴ Aንዱ ጋር፣ ሌላ ጊዜ ሌላው ከተማ Eየሄዱ
ስለሚቀላቀሉም Eንጂ። Eንዲህ ዓይነት ትልቅ ውድድር ሲያልቅ ሁሉም ሰው Eንደ ስበር ዜና የሚጠባበቀው ጉዳይ
“በሚቀጥለው ዓመት የት ይሆን?” የሚለውን ጥያቄ ነው ..፣ Aሜሪካንን ለሁለት ከፍሎ ምስራቅና ምEራብ
Eያፈራረቁ የሚደረገውን የውድድር ባህልም የሚያፈርስ ነው …፣ ሌሎች ከተሞች ያሉ Iትዮጵያውያን ነጋዴዎች
ይህን ውድድር Eየጠበቁ በመስራት ከኪሳራ ድነዋል፣ Aዳዲሶች ተከፍተዋል ..፣ Aዳዲስ ሥራ ተፈጥሯል .. ሰዎች
..Aዳዲስ ከተማ በያመቱ Eያዩ ለኑሮ የሚመችን በመምረጥ ወደዚያ ከተማ ኑሯቸውን ቀይረዋል፣ …፣ ይህንን
የፌዴሬሽናችንን የዓመት ውድድር Eየጠበቁ ዘንድሮ ደግሞ ባጋጣሚው ያላየነውን ግዛት ልናይ ነው Eያሉ ልምድ
ያደረጉ ብዙ ናቸው ..፣ … Eርግጥ ነው ሜሪላንድና Aካባቢው ቢሆን ፌዴሬሽኑ ብዙ ገንዘብ ሊያገኝ ይችል
ይሆናል። ግን የታየው “የሚገኘው ገንዘብ ብቻ ከሆነ” የንግድ ድርጅት ሆኗል ማለት ነው። ከሆነ Eሱን ተቀብለን
ጸጥ Eንበል። ዴንቨርም ያሉ፣ ሲያትልም ያሉ፣ Aትላንታም ያሉ፣ ካሊፎርኒያም ያሉ .. ወዘተ. የኛ ዝግጅት
የሚሉት Aንድ ቀን ከተማቸው ውስጥ Eንደሚደረግ ስለሚያውቁም ጭምር ነው። በተደጋጋሚ ዲሲ ብቻ
Eናዘጋጃለን ያሉ ሌሎች Eኮ “የዲሲ ዝግጅት” Eየሆኑ Eንደመጡ የሚታይ ነው። ፌዴሬሽናችን የ30 ዓመት
ከተማን ከከተማ ፣ Iትዮጵያዊን ከIትዮጵያዊ በየከተማው Eያዞረ የማገናኘት ባህሉ በማይሆን ውሳኔ Eንዳይጠፋ
ሊታሰብበት ይገባል።
30 ዓመት የቆየና Iትዮጵያውያን በAንድነት የሚገናኙበት ብቸኛ ድርጅት በግለሰቦች ምክንያት መልካም ስሙን
ማጣት የለበትም። ሥራቸውን በAግባቡ የማይሰሩ ግለሰቦች ሊቀየሩ ይችላሉ። ፌዴሬሽኑ ግን ለዘላለም ይኖራል።
(የዚህ ጽሁፍ Aዘጋጅ Aቶ ቴዎድሮስ በAትላንታ ከተማ የAድማስ ሬዲዮ Aዘጋጅ ናቸው)

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 16, 2013
  • By:
  • Last Modified: July 16, 2013 @ 2:55 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar