www.maledatimes.com የሰሞኑ ፍጥጫ መለሰ ዜናዊ እና መለሰ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሰሞኑ ፍጥጫ መለሰ ዜናዊ እና መለሰ

By   /   July 28, 2012  /   Comments Off on የሰሞኑ ፍጥጫ መለሰ ዜናዊ እና መለሰ

    Print       Email
0 0
Read Time:12 Minute, 57 Second


አቶ መለሰ ዜናዊ ከሞቱ፡ ወይ ደግሞ በጠና ተይዘው ለረጅም ጊዜ ከአልጋ ላይ ከዋሉ ብዙ ሰዎች ሊከሰት ስለሚችሉ ጉዳዮች ብዙ የተለያየ ግምቶችን ና መላምቶችን ሰንዝረዋል; በመሰንዘር ላይ ናቸው፡ ወደፊትም ይሰነዝራሉ። በእርግጥ መላ ምቶችን መገመት ቀላል ባይሆንም መገመት ግን ይቻላል። ምን አልባት አንድን ግምት የተሳካ ወይ ደግሞ ለስኬቱ የቀረበ የሚያደርገው የማያሻማ ጥሩ መረጃና የመረጃ ምንጭ፡ የአሁን አጠቃላይ ተጨባጭ ሁናቴ፡ ያለፈው የታሪክ ተሞክሮ፡ እንዲሁም ሁኔታው እየተከናወነ ያለበት ማዕቀፍና ጊዜ እና ወዘተረፈን በግርድፉ ሳይሆን በጥልቁ መረዳት ሲቻል ነው። እነዚህ ከላይ የዘረዘርኩዋችውን ሆነ ያልዘረዘርኩዋቸውን ግብአቶች በመነሻነት በመንተራስ የሚሰጡ ግምታዊ መላምቶች ሁልጊዜም ልክ ባይሆኑ አብዛኛው ጊዜ የመሆን ና የመከናወን ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። መላምቶቹን በቅጡ ከታሰበበት በአጭር ይሁን በረጅም የጊዜ ሒደት ውስጥ ፍሬ አፍርተው እና ስጋ ለብሰው ማየታችን አይቀሬ ነው።

አብዛኛውን ጊዜ በሁለት በለየላቸው ባላንጣዎች መካከል የሚደረገው ትግል አንዱ የሌላኛውን መስመር አሸንፎ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት የሚያስችለውን አሰላለፍና አካሄድ ይከተላል።አንዱ ሌላኛውን ሊሸነፍ የሚችልበትን ዕጣ ፈንታ ከፍ ለማድረግም ካሉት ብዙ አማራጮች ውስጥ አንዱን ከሌላው አወዳድሮና አበላልጦ ቅድሚያ የሚሰጠውን ሰጥቶ ከፊቱ የተደቀኑትንና የተደረደሩትን መላምቶች ለቆመለት ዓላማ ለመውሰድ በጊዜ ቀምሮ አቅሙንም መዝኖና ራሱን ፈትሾ ወደ ትግሉ ይቀላቀላል። ለትግሉም መሳካት የባላንጣውን ብቃት፡ የባላንጣውን አስላለፍ እንዲሁም ከባላንጣ ጎራ ከተሰለፉ ታማኝ የውስጥ ሓይላትን መጠቀም ና ከጎኑ ማሰለፍ የትግሉን መስመር በአሸናፊነት ለመደምደም በሚያስችል አደረጃጀት ና ብቃት መዘጋጀት የግድ ነው።

የመለስ ጎራ አጠቃላይ ዝግጅት ከዚህ ቀደም ሲያናፍሱት የነበረውን የስልጣን መተካካት ሒደት ትግበራ የሌለው ባዶ ውጥን መሆኑን እና ይተካሉ የተባሉት ግለሰቦች በሕወሃት የሚታመንባቸው አለመሆናቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳየው የአቶ መለሰ ዜናዊ የሰሞኑ ድንገተኛ ሕመም ነው። የአቶ መለሰ ዜናዊ በመኖሪያ ቤታቸው (ቤተ-መንግስታቸው) እራታቸውን እየተመገቡ በነበሩበት ወቅት ድንገት ራሳቸውን ስተው በመውደቃቸው ና በአፋጣኝ ወደ አውሮፓ ከዋነኛው ተተኪአቸው ማለትም ከአቶ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ጋር በመጓዛቸው ጎራው ሰሞኑን እየታመሰ ይገኛል። ለመለስ ታማኝ የሆኑት የሕወአት አባላት ማለትም አባይ ጸሐዮ ፡ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድአኖም፡ አቶ አርዕከበ ዕቁባይ ከመለስ ጋር ሲሰለፉ ፡ በተለያየ የጥቅም ግጭት ከተለያዮ ስልጣን ቀስ በቀስ ገሸሽ የተደረጉ እየተደረጉ ያሉ እንደ አቦይ ስብሃት ነጋ፡ ጸጋዮ በርሄ፡ ስዮም መስፍን በሌላ ወገን ሲሰለፉ፤ በረከት ስምኦን እና ሳሙራ ይኑስ ለሁለቱም ቡድን የይስሙላ ድጋፋቸውን ቢሰጡም ሁለቱም ማለትም በረከት ስምኦን እና ሳሙራ ይኑስ አፍቃሪ መለስ በመሆናቸውና ከመለስና አዜብ መስፍን ጋር ያስተሳሰራቸው ከፍተኛ ጥቅም ስላለ ወደ አዜብ ቡድን መቀላቀላቸው እንደማይቀር የሚተነትኑ ሲኖሩ ይህንን ለማመን ሕወአት ያለፈበትን ሒደትና ታሪኩን ማገላበጥ በቂ ነው ይላሉ።

በረከት ስምኦን እና ሳሙራ ይኑስ የመለስ ዜናዊ የሕወአትን የበላይነት ጫፍ ለብቻቸው መቆናጠጣቸ ለእነሱም ስጋት እንደሆነ ቢያወቁም ሳሙራ ይኑስ ጤና ስለሌላቸው በረከት ስምኦን ደግሞ በባህሪያቸውና ማንንታቸው ሽሩድና ፈሪ ስለሆኑ ድሮም፡ ዛሬም ወደፊትም ሁለቱንም የመለስ ዜናዊ ባሪያ አድርጎአዋል፤ ወደ ፊትም ያደርጋቸዋል፤ አንዳች ሓይል ካላለፈባቸው በቀር። የበረከት ስምኦን ባህሪይ በአቶ መለስና በወ/ሮ አዜብ ዘንድ ስለሚታወቅ እንደ ቅሪላ ኳስ አንዴ ወዲህ ሌላ ጊዜ ወዲያ ይቀባበሉዋቸዋል። አቶ በረከት ስምኦን የአዜብ ነገር ሁልጊዜም ባይጥማቸውም በፍርሃት እንዲሁም ወ/ሮ አዜብ የበረከት ስምኦን ጉዳይ አንድም ቀን ደልቶአቸው አያውቁም በመለስ ብርታት እንደምንም እንደ ምንም አብረው ዘለቀዋል። በ1997/98 የምርጫ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንኳን ወ/ሮ አዜብ አቶ በረከት ስምኦንን በእንዝላልነት ሲከሱዋቸው እንደነበር ይታወቃል። አቶ በረከት ስምኦን ማደግደግ ስለለመዱና የምጸት በሚመስል አብሸቅ ሳቃቸው ወ/ሮዋን እያነደዱም ቢሆን ከስራቸው ሌላ አደግዳጊ ቁርጥ መሳያቸው የሆኑትን አቶ ሸመልስ ከማል በመፍጠር ተሳክቶላቸዋል።
ይህ ሁሉ ግምት ተሳክቶ ተሳክሮ ….የአዜብ መራሹ ቡድን በድል ከተወጣ አቶ ሓይለማሪያም ደሳለኘን ለይስሙላ ከፊት አስቀድሞው አዜብ መስፍን እና አቶ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ከሃላ ቼ ሊሉዋቸው ጉዞአቸውን ሲያሳምሩ፡ እነ አባይ ጸሀዮና በረከት ስምዖን እንደ እነ ስዮም መስፍን ባህር አቋርጠው አምባሳደሮች ይሆናሉ ሊያውም ጸባያቸውን ካሳመሩ ነው፤ ካልሆነ ግን ወይ በእነተፈራ ዋልዋ መንገድ ጡረታ፡ ወይ በእነስዮ አብርሃ ጎዳና ቃሊቲ (ቅሊንጦ) ፡ ከከፋም በሓየሎም የመጨረሻ ምሽት ድግስ አይነት ታሪካቸው ይከደናል። ይህንን መጻኢ ተስፋቸውን አቶ በረከት ስምኦን ሳይመለከቱት አይቀሩምና ልዮ ሓይል ከረዳቸው የአቦይ ስብሃትን ቡድን ተንተርሰው ራሳቸውን ያስመልጡ ይሆናል። ይህ መቼም የማይመስል ነገር ….. ነው።

በተቃራኒው ጎራ የተሰለፉት ይህንን ዕድል እንዴት ይጠቀሙበት ይሆን? ከፊታቸው ተደቀኑትን ብዙ አማራጮችን ለመምረጥ ተቸግረው ሲንደፋደፉ ዳር ቆመን ታዝበን አይ ሁሉ አማረሽን ገበያ አታዉጧት እንል ይሆንን ወይንስ አንዱን ከሌላው አወዳድረውና አበላልጠው የሚበልጠውን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው አምነው አንጥረው ወደ ትግሉ በሙሉ ሓይላቸው በመሳተፍ ሕዝቡ የጠማውን ነነት እኩልነት ፍትህ ዲሞክራሲ ለማጎናፍ አዲስ ምዕራፍ ይክፍቱ ይሆን?
ሕዝቡስ ምን አደርግ ይሆን? እንደግብጽ ሕዝብ ጨቋኙን ስርአት እንዲገለብጡልን ሃያላን መንግስታትን አንጠብቅም በማለት ሕዝባዊ ትግሉን ያቀጣጥሉት ይሆን? ዛሬ በሕዝበ ሙስሊሙ የተጀመረውን የእምነት የነጻነት ጥያቄ ወደ ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች ቀይሮ በተለያዮ ከተሞች ሕዝባዊ ትዕይንቶችን እናይ ይሆን?
ለሁሉም ዘመኑ የለውጥ ነው። ድልና ለውጥ የሚመጣው በብዙ ምኞት አይደለም፡ ድል እና ለውጥንም እንዲሰጡን የምንጠበቀው ሓያላን አገራት የሉንም። እኛ የምንስማው ተባብረን ስንጮህ ነውና ተባብረን እንጮሃለን። ደግሞም እንሰማለን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 28, 2012
  • By:
  • Last Modified: July 28, 2012 @ 11:45 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar