www.maledatimes.com - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

<<ከአቦይ ጋር ጥቂት ቆይታ>>

By   /   July 29, 2012  /   Comments Off on <<ከአቦይ ጋር ጥቂት ቆይታ>>

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 17 Second

w/selassie nega( sebhat nega ) photo maledatimes library

የሃሳብ ልዩነት ያለ ነው፡፡ ልዩነቱን መድረክ ላይ አምጥቶ ለማሸነፍ መሞከር ትክክለኛ አካሄድ ነው፡፡ ከዛ ውጪ ሞትን መመኘት ከሰውነት እንዴት እንደራቀ የሚያሳይ የወረደ አመለካከት ነው፡፡ የጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊን ጤንነት አስመልክቶ እርስዎ ለአሜሪካን ድምፅ በሰጡት ቃለምልልስ ጠቅላይ ሚ/ሩ ህክምናቸውን ጨርሰው በቅርቡ በስራቸው ላይ እንደሚገኙ ሲገልፁ አቶ በረከት ስምዖን ደግሞ እረፍት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡ የቱን እንመን? ህዝብ ማወቅ ያለበት አቶ በረከት የሰጡትን መግለጫ ነው፡፡ የእሳቸው መግለጫ ኦፊሻል ነው፡፡ እርስዎ ለአሜሪካን ድምፅ ከሰጡት ጋር እንዴት እናስታርቀው? የግድ መታረቅ አለበት ወይ? የአቶ በረከትን መግለጫ ውሰዱ፡፡ የሁለታችሁም መግለጫ ቀናቶችን አስቆጥረዋል፡፡ የጠቅላይ ሚ/ሩ የጤና ሁኔታ በአሁኑ ወቅት እንዴት ነው? አጠገቡ ካሉ ሰዎች እንደምሰማው ጤንነቱ በፍጥነት እየተሻሻለ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚ/ሩ ያሉበትን ቦታ አስመልክቶም የተለያዩ መረጃዎች ይወጣሉ፡፡ የት ነው ያሉት? አውሮፓ አውሮፓ የት? በትክክል አላውቀውም፡፡ ለእረፍት አሜሪካን ሄዱ ተብሏል አይመስለኝም፡፡ የቀድሞው የህወሓት ታጋይ የነበሩት አቶ ግደይ ዘርአፅዮን “ጠቅላይ ሚ/ሩ ቢሞቱ ለአገሪቱ መፍትሄ ይሆናል” በማለት የሰጡትን አስተያየት እንዴት አዩት? የሃሳብ ልዩነት ያለ ነው፡፡ ልዩነቱን መድረክ ላይ አምጥቶ ለማሸነፍ መሞከር ትክክለኛ አካሄድ ነው፡፡ ከዛ ውጪ ሞትን መመኘት ከሰውነት እንዴት እንደራቀ የሚያሳይ የወረደ አመለካከት ነው፡፡ በቅርቡ አድዋ የሚገኘው የንግስተ ሳባ ትምህርት ቤት ሰባኛ ዓመት ሲከበር እርስዎ የደርግ ዘመን የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚደንት የነበሩትን ኮለኔል ፍስሀ ደስታን ይዘው ሄደው ነበር፡፡ እስቲ ስለሱ ይንገሩኝ፡፡ የንግስተ ሳባ 70ኛ ዓመት የተከበረው ለተከታታይ አራት ቀናት ነበር፡፡ በአሉ በሚከበርበት ወቅት የትምህርት ቤቱን ታሪክ አስመልክቶ የፓናል ውይይት ነበር፡፡ የትምህርት ቤቱ ታሪክ ላይ ከፍተኛ ሚና ያለው፣ እኔን ጨምሮ ብዙዎችን ጥሩ ተማሪዎች እንድንሆን ያደረገን የፍሰሀ ደስታ ታላቅ ወንድም፣ የት/ቤቱ ዳይሬክተር የነበረው መኮንን ደስታ ነው፡፡ ፍሰሀ ደስታ ደግሞ የቀድሞው የት/ቤቱ ተማሪ ነው፡፡ የኔ የታናሽ ወንድሜ ጓደኛ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ በአል መካፈል አለበት፤ መለየት የለበትም ስል ራሴ ጠይቄው ነው የወሰድኩት፡፡ ፍሰሀ ደስታ የደርግ ምክትል ፕሬዚደንት ነበር፡፡ ፍሰሀ ደስታን መንግስት ሌሎች የደርግ ባለስልጣኖችን ሲፈታ ፈትቶታል፡፡ በቀረው እድሜ ደስ ብሎት እንዲኖር እፈልጋለሁ፤ መገለል የለበትም፡፡ እስር ቤት ሆኖም እጠይቀው ነበር፡፡ አድዋ ስትደርሱ ምን ስሜት ፈጠረ? የሚበዛው ሰው ተገረመ!! አንዳንዶች ደስ አላቸው!! ቅር ያላቸው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እኔን በግልፅ ወጥቶ የተናገረኝ የለም፡፡ እኔም ለምን ቅር አላቸው? ለምን ደስ አላቸው ወይም ለምን ገረማቸው ለሚለው መልስ አልሰጥም!! እኔን ደስ ያለኝን ሌላን ሰው የማይጐዳ ነገር አድርጌያለሁ፡፡ የደርግ ባለስልጣን ከነበሩ ሌሎች ጋርስ ቅርበት አለዎት? በደርግ ጊዜ የግብርና ሚ/ር እና በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ከነበረው አሁን በህይወት ከሌለው ከዶ/ር ገረመው ደበሌ ጋር በጣም ወዳጆች ነበርን፡፡ በየቀኑ ነበር የምንገናኘው፡፡ መንግስቱ ግለ መሪ እና ፈላጭ ቆራጭ ነበር፡፡ ሌሎቹ የመንግስቱ ጓደኞች ስልጣን ነበራቸው ብዬ አላምንም፡፡ እነሱ ራሳቸውን የበደሉ ናቸው፡፡ ስርአቱን የሚያምኑበት አይመስለኝም፡፡ መንግስቱ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ያጠፋ ሰው በጥፋቱ መቀጣት አለበት፤ እንደሰው ግን መንግስቱ ቢመጣ ሰላም እለዋለሁ፡፡ እርስዎ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ሃሳብዎን ይገልፃሉ፡፡ ለጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ይህ ከየት የመጣ ነው? ጋዜጦቹ ሲፅፉብኝ የፃፉትን መሰረት አድርጌ መልስ መስጠት መብቴም ግዴታዬም ነው፡፡ ባይፅፉ ኖሮ ጋዜጣ ላይ አልፅፍም፡፡ የአሜሪካን ድምፅም ስለጠየቀኝ ነው የተናገርኩት፡፡ አንቺም ስለጠየቅሽኝ እኮ ነው መልስ የምሰጥሽ፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 29, 2012
  • By:
  • Last Modified: July 29, 2012 @ 12:59 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar