www.maledatimes.com ጨለማው ሲገፈፍ (ይግዛው እያሱ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  POEMS  >  Current Article

ጨለማው ሲገፈፍ (ይግዛው እያሱ)

By   /   September 10, 2013  /   Comments Off on ጨለማው ሲገፈፍ (ይግዛው እያሱ)

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 25 Second

ጨለማው ሲገፈፍ ብርሀን ተመልክተው
ወፎች ሲዘምሩ ከእንቅልፋቸው ነቅተው
ለሰው ልጅ ሲያበስሩ ብርሀን ለመምጣቱ
ሁሉም ይዘጋጃል ለቀጣይ ህይወቱ።
የወፉን ዝማሬ በአበባ ተክቶ
መስከረም ሲያነቃን አዲስ አመት ገብቶ
በደንብ ልንዘጋጅ አቅደን ልንሰራ
በፍቅር እንኑር ሁላችን በጋራ።
እድገት ያለፍቅር አይመጣም በከንቱ
ማስማማት እንምረጥ ሰው ከማፋጀቱ።
በብሔር ከፋፍሎ አንዱን በአንዱ አዝምቶ
ሲያፋጁ መኖሩ እዚህ ላይ አብቅቶ
ከህዝብ ጎን ቆሞ ሚባሉትን መስማት
አሁን ግድ ይለናል በጋራ ለመስራት።
ይህ ተቃዋሚ ነው ያኛው አሸባሪ
ለህዝብ የሚጠቅም ወያኔን አስፈሪ
መባባሉ ቀርቶ ለሀገር አስቦ
በሰላም ይፈታ ልዩነቱ ጠቦ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on September 10, 2013
  • By:
  • Last Modified: September 10, 2013 @ 11:06 pm
  • Filed Under: POEMS

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

አንድዬ

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar