www.maledatimes.com ለንደን የኢ\ኦ\ተ\ቤ\ክ\ን የአውሮፓ ስብከተ ወንጌል ጉባኤን አስተናገደች በታምሩ ገዳ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ለንደን የኢ\ኦ\ተ\ቤ\ክ\ን የአውሮፓ ስብከተ ወንጌል ጉባኤን አስተናገደች በታምሩ ገዳ

By   /   July 30, 2012  /   Comments Off on ለንደን የኢ\ኦ\ተ\ቤ\ክ\ን የአውሮፓ ስብከተ ወንጌል ጉባኤን አስተናገደች በታምሩ ገዳ

    Print       Email
0 0
Read Time:20 Minute, 58 Second

zena gybayee Dpdf with picture atttachment ለንደን የኢ\ኦ\ተ\ቤ\ክ\ን የአውሮፓ ስብከተ ወንጌል ጉባኤን አስተናገደች በታምሩ ገዳ
የለንደን ከተማ የአስራ አምስተኛውን የመላው አውሮፓ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የወንጌል ጉባኤን በደመቀ
ሁኔታ አሰተናገደች ፡፡በአገር ቤት እና በተለያዩ የአለማት ክፍሎች በሚገኙ ህዝበ ክርስቲያን ላይ አየደረሰ ያላው የመብት ረገጣ
እንዳሳሰባቸው እና እርምጃውም በአስቸኳይ ለማስቆም ልዩ የሆነ ምህላ እና ጸሎት እንዲደረግ መንፈሳዊ ጥሪ ቀረበ፡፡
በለንደን የርእሳነ አደባራት ቅድስት ማሪያም ቤ\ክን ለሶስት ቀናት ከሀምሌ 13-15 2004 አ.ም( ሃምሌ 20-22 2012 እኤአ)የአሰራ
አምሰተኛው የመላው አውሮፓ የኢ\ ኦ\ ተ\ ቤ\ክን የወንጌል ጉባኤን በደመቀ ሁኔታ ያስተናገደች ሲሆን በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ
በአገራችን ኢትዮጵያ ባሉት ወቀታዊ የሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ የሆኑ ችግሮች ከዚያም አልፎ በመካከለኛው ምስራቅ እና በተቀረው
የአለማት ክፍል ተበታትነው የሚኖሩ ወገኖች ላይ የሚደርሰውን ሃይማኖታዊ ጭቆና እና ሰቆቃ ይቆም ዘንድ ከዚህ ቀደም
ከሚደረገው ምህላ እና ምልጃ በተለየ መለኩ ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን በእየ አጥቢያ ቤ\ክኑ ኢትዮጵያ እና ልጆቿን በማሰብወደ
ፈጣሪው በእንባ እና በጸሎት ተገቶ እንዲጸልይ ጉባኤተኛው በጋራ መጠየቁን የቤተክርስትያኗ አሰተዳዳሪ ቆሞስ አባ ግርማከበደ
መልክቱን አሰተላልፈዋል፡፡ልዩ የሆነውን የጸሎት እና ምልጃ አስፈላጊነትን በተመለከተ በስዊዲን አገር የመድሃኒ አለም ቤ\ክን
አገለጋይ እና ከጉባኤው መሰራቾች መካከል አንዱ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ጌጡ የሃላሸት ” ጸሎት ይደረግ ሲባል ከዚህ ቀደም
ጸሎት አድርገን አናውቅም ነበር ማለት ሳይሆን ዘወትር ስንጸልይ ቆይተናል፡፡ከዚህ ቀደም የነበሩን ችግሮቻችንን በሰላማዊ ሰልፎች
አሳይተናል፡ ለሰዎች ( ምድራዊ ገዤዎች) ያስገባናቸው በርካታ የቅሬታ እቤቱታዎችም አልሰመሩም፡፡ከዚህ ሁሉ ጣጣ ያሰብነውን
ለመፈጸም ሙሉ ስልጣን ላለው እግዚአብሄር ብናመለክት ኖሮ እግዚአብሄር ያሻነውን ሊያደርግልን የችላል፡፡” ሲሉ የጋራ ጸሎቱ እና
የምልጃውን አሰፈላጊነትን ለጉባኤተኛው አብራርተዋል፡፡
የአጠቃላይ የሰብከተ ወንጌል ፕሮግራሙን በተመለከተ ቆሞስ አባ ግርማ በምድረ አሜሪካ ከላስቭጋስ ከተማ ለሚሰራጨው የህብር
ራዲዮ የምእራብ አውሮፓ ልዩ ዘጋቢ ለሆነው ( ለዚህ ጸሃፊ ) በሰጡት አሰተያየት “የጉባኤው ዋንኛ አላማ ሃይማኖትን
የምንማማርበት እና የምናስተምርበት እንደዚሁም ለነፍሳችን ዘወትር አሰፈላጊ የሆነውን የእግዚአብሄር የምህረት ጸጋን
የምንለምንበት ጉባኤ ነበር ፡፡በተለያዩ ጉዳዮች ያዘኑ ወገኖች በዚህ መስሉ ጉባኤ ላይ በመገኘት ይጽናናሉ፡፡ በማህበራዊ ግንኙነትም
ቢሆን ለረጅም ጊዜያት የተራራቁ ወገኖች በዚህ አይነቱ ጉባኤ አማካኝነት የገናኛሉ፡፡” ብለዋል፡፡የፕሮግራሙን መሳካትም
በተመለከተ “ምንም እንኳን ሃዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ሁሉን ያዘጋጀው እግዚአብሄር ነው አንዳለው በስራዎቹ ውስጥ ሁሉ የፈጣሪ እጆች ቢኖሩበትም በረካታ ወገኖች የበረከቱ ተሳታፊዎች ለመሆን ሲሉ ያሳዩት መተባበር እና የሰጡት ድጋፍ ሊደነቅ እና ለወደፊቱም
ቢሆን ሊበረታታ ይገባዋል ፡በዚህ ጉባኤ አማካኝነት ሰይጣን ድል የተመታበት እና እግዚአብሄር የከበረበት መድረክ ነበር ማለት
እችላለሁ፡፡የስብከተ ወንጌሉን ፕሮግራም ለመከታተል ከተለያዩ የአውሮፓ እና የእንግሊዝ ከተሞች በመምጣት ውድ ጊዜያቸውን
እና ገንዘባቸውን መሰዋት ላደረጉ መምህራን ፡፡ዘማሪያን ፡ዘማሪያት እና በሺህ ለሚቆጠሩ ምእመናን ከፍ ያለ ምስጋናዩን ማቅረብ
እወዳለሁ ” ብለዋል፡፡የወንጌል ትምህርት ለመስጠት ሊቀትጉሃን ጌጡ የሃላሸት (ከስዊድን)፡ቂሲስ መብራቱ ኬሮስ (ከካናዳ )እና
መምህር ታሪኩ አበራ (ከአ\አ) እና ሊቀ መዘምራን ይልማ ሃይሉ (ከአሜሪካ ) በመምጣት መንፈሳዊ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡ የተለያዩ
መንፈሳዊ ግጥሞች እና መዝሙሮችም በሰንበት ት\ቤት ወጣቶች እና ከምእመናን በኩል ቀርበዋል፡፡የስብከተ ወንጌሉን አስፈላጊነት
በተመለከተ ከካህናቱ እና ከምእመናኑ በቀረበው ጥያቄ መሰረት የስብከተ ወንጌሉ ፕሮግራም ሃሙስ ፡አርብ ፡ቅዳሜ እና እሁድ
ሃምሌ 22 2004 አም (ሃምሌ 29 2012 እኤአ) ድረስ እንዲራዘም ተደርጓል ፡፡
የጉባኤው ጠንሳሾች ከሆኑት ጥቂት አባቶች መካከል አንዱ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ጌጡ የሃላሸት በበኩላቸው ለዚህ ጸሃፊ በሰጡት
አሰተያየት “ይህ ጉባኤ ከዚህ ደረጃ ይደርሳል ብዪ አለገመትኩም ነበር፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር ቸረነት እና በህዝበ ከርስቲያኑ
ትብብር ጉልህ የሚባሉ እንከኖች ሳይገጥሙን ፡የዘመኑን አስተዳደራዊ ልዩነቶችን ለጊዜው ወደጎን በመተው፡ ሁላችንንም
ሊያስተሳስርን በሚችለው በስብከተ ወንጌል ዙሪያ በማተኮር ከእዚህ ደረጃ ደረሰናል፡፡ለጉባኤው መጎልበት ጉልህ ሚና ለተጫወቱት
በውጭ አገር የሚገኘው የቅዱስ ሴኖዶስ አባል እና የአውሮፓ እና የደቡብ አፍሪካ ሊቀጳጳስ ለሆኑት ለአቡነ ኢሊያስ ታላቅ ምስጋና
ይገባቸውል፡፡ ያ የዛሬ አስራ ሁለት አመት አካባቢ እንደ ቀልድ ጥቄት ሆነን የጀመርነው ጉባኤ ዛሬ አድጎ እና ትናንሽ ልጆችን
(ጉባኤዎችን ) ወልዶ ማየቱ ሁለችንንም ሊያኮራን ይገባል፡ ይህ ጉባኤ ወደፊትም ቢሆን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጽኑ ምኞት አለኝ፡
፡” ብለዋል፡፡
አቶ ፍሰሃ አስፋው ይባላሉ ፡፡ የለንደን ከተማ ነዋሪ ናቸው ፡፡ በጉባኤው ላይ የታዘቡት ነገር ካለ ለሚለው ለዚህ ጸሃፊ ጥያቄ “
ዝግጅቱን ለማካሄድ የጊዜ እጥረት ያለ ይመስላል ፡፡ይሁናን ይህን መሰል ታላቅ ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ ከተለያዩ የአለማችን ከተሞች
የሚመጡ ተሳታፊዎችን እና የጉባኤውን ጠቀሜታን ከግንዛቤ ውስጥ በማሰገባት መንፈሳዊ ጥሪው ሃያ ሰባቱ የአወሮፓ አገሮችን
ያካተተ ቢሆን መልካም ነው(የጉባኤው ተሳታፊዎች በአመዛኙ ከስዊዲን፡ጀርመን፡ ኖሮዌይ፡እንግሊዝ፡ ፊላንድ ፡ጣሊያን እና
ፈረንሳይ..ወዘተ ከመሳሰሉት አገሮች ነው የተሰባሰቡት ) ፡ በዚህ አይነቱ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ተጠሪዎቹ አገሮቹ ብቻ ሳይሆኑ
አጥቢያ ቤተክርስቲያናት በሙሉ ቢሳተፉ መልካም ነው ፡፡ ጠሪ አክባሪ በመሆኑ ማንኛውም አዘጋጁ ቤተክርስቲን ምንም እንኳን
የአሰተዳደር ልዩነቶች ቢኖሩት እንኳን የጉባኤው ዋንኛ አላማ አንድነተን የሚያጠናክር በመሆኑ ይህንን መሰረት ባደረገ መልኩ
ተጠንክሮ ቢቀጥል በቃለ እግዚአብሄር አማካኝነት ብዙ ነፍሳት ይድናሉ፡ የተራራቁም ምእመናን አጋጣሚውን በመጠቀም በቀላላሉ
የገናኛሉ፡፡” ሲሉ አሰተያየታችውን ሰጥተዋል፡፡
ቲሞቲ (ጤሞቲዮስ) ከነጭ እንግሊዞች ወላጆቹ የተወለደ ወጣት የለንደን ነዋሪ ሲሆን እርሱ እና ቤተሰቦቹ ከአለ አማኒነት (
ኤቲይስት) ወደ የካቶሊሊክ እምነት ከተለወጡ አመታት ተቆጥረዋል፡፡ ከዛሬ ሶስት አመታት በፊት ወደ ቅድስት አገር
እስራኤል(አየሩሳሌም) በተጓዘበት ወቅት በዚያ ከሚገኙ የሃማኖታዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች መካከል አንዱ የሆነውን የኢ\ኦ\ተ\ ቤ\ክን
ንብረት የሆነው የዴር ሱሉጣን ገዳምን ለመጎብኘት እድሉን እንዳገኘ ይናገራል፡፡በለንደኑ ጉባኤ ላይ ከምእመናኑ ጋር ሲያጨበጭብ
እና ፈጣሪን ሲያመሰግን ይህ ጸሃፊ አግኝቶት እንዴት ወደ ቤ\ክኑ እንደመጣ እና ምን እንደተሰማው ላቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ
“ነጫጭ ልብስ የለበሱ በረካታ ሰዎች ወደ ቤ\ክኑ ሲገቡ በማየቴ እኔም ገብቼ መጸለይ አለብኝ በማለት ከተሳፈረኩበት አውቶቡስ
ወርጄ ወደ ቤ\ክኑ በፍጥነት ወረድኩ ፡፡ በደጃፍ ላይ የነበሩ አንድ ካህንን ገብቼ መሳተፍ እንደምችል ብጠይቃቸው በደስታ
ጋበዙኝ፡፡ ምንም እንኳን ቋንቋችሁን ባላውቀውም በዚህ ጉባኤ ተግኝቼ እግዚአብሄር እንደሚባርከኝ ጥርጥር የለኝም፡፡ዛሬ
ተባርኬያለሁ ፡፡ ምክንያቱም ወደ ዚህ ቅዱስ ስፍራ በመምጣቴ መላእክት እና ሰማእታት አንደሚረዱኝ አልጠራጠርም፡፡
ሰባኪዎቹ በጣም ጥልቅ እና መካሪ የሆነ ትምህርት ይሰጡ እንደ ነበር በተለይ ደግሞ መዝሙር እና ምስጋና ሲሰማ ከህዝቡ
የተመስጦ እና ደስታ ፊት ላይ በቀላሉ ማንበብ ችያለሁ፡፡ይህ አይነቱ ደስታ እና መከባበር በሌሎች ክርስቲያኖች ዘንድ ሊኖር
ይገባል፡፡አንዳንድ ቦታ ክርስቲያኖች ከቤተክርስቲያን ሲወጡ ከፊታቸው ላይ አዝነው እና ተክዘው ታያለህ፡፡ ይህ አይነቱ ስሜት
እዚህ አላየሁም፡፡ምክንያቱም የእግዚአብሄር ፍቅር ሰለገባቸው እና ጌታ እየሱስ ክርስቶስን በእጅጉ እንደሚወዱት እና የመንፈስ
ቅዱስ ጸጋም እንዳልተለያቸው ተመልክቻለሁ ፡፡በሰተመጨረሻ ለኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች ሆነ ለአገርህ ልጆች
የምታሰተላልፈው መልእክት ካለህ ለሚለው ጥያቄ ሲመለስ “እናንት ባላችሁ ልትኮሩ ይገባል ፡፡ጥንታዊ የሆነው እምነታችሁ እና
ባህላችሁ ቀላል ነገር አይደለም ፡፡ይህንን የትም የማይገኝ መንፈሳዊ ሃብታችሁን ልታጡት አይገባም፡፡ አያሌ ምእራባዊያን
ክርስቲያኖች ያጡት ክርስቲያናዊ እሴት\ቫሊዩ \ እናንተ ጋር አለ፡፡እኔም ብሆን እንደ አጋጣሚ የዚህ ጉባኤ ተሳታፊ በመሆኔ
ፈጣሪዩን አመሰግናለሁ፡፡”ሲል አሰተያየቱን ደምድሟል፡፡አቶ ሃይለ መስቀል ተሰፋዩ በጉባኤው ላይ መንፈሳዊ ግጥሞችን ካቀረቡ ተሳታፊዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ በአጠቃላይ ምን
እንደተሰማቸው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ከጠበቅሁት በላይ ደምቆ እና የተሳካ ሆኖ ነው ያገኘሁት ፡፡አሰተማሪዎቹ ነፍስን
የሚያረሰርስ ትምህርት እና ምክር ሰጥተውናል፡፡አንግዲህ ዘሩ(ህገ ወንጌሉ )ተዘረቷል ፡፡ ዘሩን ኮትኩተን እና የፍሬው ተጠቃሜዎች
መሆን ይጠበቅብናል ብዮ አምናለሁ፡፡ አንደዚህ የመሰለ ታላቅ ጉባኤ ሲዘጋጅ ቀደም ተብሎ የጥሪው መልክቶች ቢሰራጩ ከዚህ
በበለጠ መልኩ ብዙ ምእመናኖች ሊመጡ ይችላሉ ብዮ እገምታለሁ፡፡በስተመጨረሻም ጉባኤያችንን እግዚአብሄር እንዲያስፋፋልን
ዘወትር በጸሎት ተግተን መጠየቅ አለብን ብይ አሰባለሁ፡፡” ብለዋል ፡፡በለንደን የርእሳነ አደባራት ቅድስት ማሪያም ቤ\ክን የመላው
አውሮፓ የኢ\ ኦ\ ተ\ ቤ\ክን የወንጌል ጉባኤን በደመቀ ሁኔታ ስታዘጋጅ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ቤተከርስቲያኒቱ ከተቆረቆረች ከሶስት
እስርት አመታታ በላይ የተቆጠሩ ሲሆን የራሷ የሆነ ግምቱ ከአንድ ሚሊዮን ፓውንድ (ሃያ ሰባት ሚሊዮን ብር) በላይ የፈጀ ህንጻ
ቤተክርስቲእን በመግዛት በምድረ አንግሊዝ ቀደመት ቤ/ክርን ነች፡፡
ለተጨማሪ አስተያየቶች ወይም ጥያቄዎች ጸሃፊውን በtamgeda@gmail.com ያገኛሉ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 30, 2012
  • By:
  • Last Modified: July 30, 2012 @ 7:30 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar