www.maledatimes.com ስ – ን – á‹‹ – á‹° – ድ ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  POEMS  >  Current Article

ስ – ን – á‹‹ – á‹° – ድ !

By   /   October 1, 2013  /   Comments Off on ስ – ን – á‹‹ – á‹° – ድ !

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 5 Second

የሰው ዘር እንደሆን ፍቅር ነው ሲሰራ 
ያረክሰዋል እንጂ ክፋት እየሰራ
ነገር እየዘራ
ተ – ራ!

አየህ ስንዋደድ . . .

አማልክት በሰማይ ጧፍ እየለኮሱ
ሉባንጃና ከርቤ ብርጉድ እያጤሱ
የሰላም ማእጠንት እያርከፈከፉ
ለፍቅራችን ፀዳል ቅኔ እየዘረፉ
ይኸው በዝማሬ በጀነት አለፉ።

አየሽ ስንላመድ . . .

ጨረቃና ኮከብ እየተጣቀሱ
ምድርና ፀሐይ ባንድ እየደነሱ
ኮረብታና አድማስ እየተቃቀፉ
ወንዝና ጅረቶች ፍቅር እየተላፉ
በፌሽታ ይሰክራሉ ፍጥረታት በሞላ
በህብረታችን ሲቆም የጎጇችን ባላ።

አየህ ስንፋቀድ . . .

ጠጅሳር፣ ጤናዳም፣ ደማከሴ፣ ጦስኝ
ፌጦ፣ ጥቁር አዝሙድ፣ ያሪት ዘር ችግኝ
ኮሰረት፣ ድምብላል፣ ድምቡሽ ኮረሪማ
ዝንጅብል፣ ሽንኩርቱ አብሮ እየተስማማ
ሕላዌ እንዲቀምም በሕይወት አውድማ
እነኚያው አማልክት በሰማይ የሚያርሱ
ከጀነት እርሻ ላይ በደቦ እያፈሱ
እዪው ወደ ምድር ዘር ሲነሰንሱ።

አቤት ስንፋቀር . . .

“የጸደቁ ነፍሶች በፍቅር የላቁ
ለምድር ሽልማት ክፋትን የናቁ!”
ብለው እያሞካሹ ስለኛ እያዜሙ
አእዋፍ በሰማይ በፍቅር ተመሙ።

እያቸው !
. . . እዪያቸው !
. . . . . . እዩዋቸው በሞቴ !
ክንፋቸው ሲራገፍ ከላይ ታች ሲማታ
አዳፍቶ ሲያፈርጠው የፀብን ቱማታ።

አየህ !
. . . አየሽ !
. . . . . . አየን !
ለምን ተለያየን ?!

ወግድ የታባቱ!
ለፀብ ፊት አትስጡት
ያብሮነትን ቀዬ በጭቃ አትርገጡት
በጥላቻ በትር ጥላቻን ቀጥቅጡት
ፍቅር !
… ሰላም !
… … ህብርን !
አንድ ላይ ቀይጡት።

___________
/ አብዲ ሰዒድ /
ተፃፈ: 2005 E.C
ኡፕሳላ፣ ስውዲን

One Love !
ብጥስጣሽ ሃሳቦች (bT’sT’ash) .

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on October 1, 2013
  • By:
  • Last Modified: October 1, 2013 @ 7:05 am
  • Filed Under: POEMS

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

አንድዬ

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar