www.maledatimes.com ጭምጭምታ ከህወሃት መንደር ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በጠና ታመዋል እስካሁን የደረሱበት ሁኔታም አልታወቀም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጭምጭምታ ከህወሃት መንደር ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በጠና ታመዋል እስካሁን የደረሱበት ሁኔታም አልታወቀም

By   /   July 31, 2012  /   Comments Off on ጭምጭምታ ከህወሃት መንደር ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በጠና ታመዋል እስካሁን የደረሱበት ሁኔታም አልታወቀም

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 25 Second

 

ይህን ዜና ባለፈው ወር የጠቅላይ ሚንስትራችንን በጠና መታመም አስመልክቶ በሚሰሩበት ቤተ መንግስት ጠረጴዛ ላይ ከህመማቸው መክፋት መውደቃቸውን እርሳቸውን በመሳት ከቁጥጥራቸው ውጭ በመሆን እና ህመማቸው መባሱን የደረሱበትም እንዳልታወቀ በማተት ዘግበነው ነበር ዛሬም መለስ ብለን በየጊዜው የተዛቡ ወሬዎች እየደረሱን ሲሆን እስካሁን ለዘገብነው ሪፖርት በተለይም በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የሞት ምክንያት የማለዳ ታይምስ መረጃ ፣መረጃዎችን ምንጭ በመጥቀስ የሚያቀርብ ሲሆን በመረጃ ማእከላችን የደረሱ እውነተኛ ምንጮች ደርሰውን በማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ስም እስካልዘገብን ድረስ የድርጅታችንን ህልውና የሚነካ እንዳለሆነ እየጠቀስን ማናቸውም መረጃዎች ሲደርሱን ምንጮቻችንን በመጥቀስ ልናቀርብላችሁ እንወዳለን ። በተለይም  በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ከአቶ በረከት ስምኦን ይሰጣል ተብሎ የተጠበቀው በጠቅላይ ሚንስትር የጤንነት ሁኔታ እስካሁንም ያለመገለጹ የህዝቡን አመለካከት በሁለት ጎዳና የከፈለው ሲሆን እስካሁን ጠቅላይ ሚንስትሩ መግለጫ አለመስጠታቸው እና ያሉበት ደህንነት አለመታወቁ ከተጠቀሰላቸው የጊዜ ገደብ በላይ በእረፍት ላይ መቆየታቸው በመገናኛ መድረኮች ለሚቀርቡት ምላሽ አለመሰጠቱ የመሞታቸውን ሁኔታ በአመክሮ ሊያሳምን ሲችል በሌላም እኩል ግን ምንም የሚዳበስ መረጃ ካለመኖሩ እና ከገዢው መንግስት የሚደመጡት መረጃዎች የህብረተሰቡን ቀልብ ሊያንጠለጥሉት እንደቻሉ እስካሁንም ያሉበትን አለማሳወቃቸው ችግሩን ሊያባብሰው ችሎአል ።ስለመታመማቸው ያቀረብነውን የባለፈውን ሪፖርት እንዲህ አቅርበነዋል ።

ከሰሞኑ የህወሃት መንደር በሃሳብ እየታመሰች ነው በተለይም ከፖሊት ቢሮ አመራሮች ትልቁን ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል ።

በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ያሉት የህወሃት አባሎች ስጋታቸው የአቶ መለስ ዜናዊ ጤንነት በአስጊ ደረጃ ላይ መሆኑ ሲሆን በተለይም ከባለፈው የስምንት አባል አገሮች ስብሰባ ከተደረገባቸው አስደንጋጭ…  ተቃውሞ ጤንነታቸው እለት ከእለት ወደ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱ ነው ።ባሳለፍነው ሁለት ሳምንታት ውስጥ በሜክሲኮ ያደረጉት ጉዙ እና ከአቻቸው የቻይናው አምባሳደር ጋር ያደረጉት ውይይት በጥሩ እና በተሳካ ሁኔታ ቢጠናቀቅም በወቅቱ የነበራቸው ጤንነት ግን ይበልጡኑ ትኩረቱን እንደሰጣቸው አድርጓል ።

በአሜሪካ በደረሰባቸው ተቃውሞ የአልጀዚራ ስትሪም አዘጋጅ ከሆኑት ጋዜጠኞች ጥያቄ ሊቀርብላቸው ሲጠየቁ አሻፈረኝ ማለታቸው  እና አበበ ገላውን እና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማወያየታቸው ይታወሳል ይህም ሆኖ ሳለ የመለስ አስተዳደርን ምንኛ አስደንግጦአቸው እንደነበር እና አሁንም ከባድ ችግር ውስጥ እና አዘቅቱን ከማይወጡበት ጎዳና ላይ መውደቃቸውን የሚያሳይ እንደሆነ አመልካች ነው ። በተለይም ለማለዳ ታይምስ አዘጋጆች በደረሰው ኢሜል መሰረት ጠቅላይ ሚንስትሩ የከፋ ደረጃ ላይ ቢሆኑም እሳቸውን ተክተው ሊሰሩ የሚችሉ ሰው በወይዘሮ አዘብ መስፍን በኩል ተዘጋጅቶ መስራት መጀመራቸውን መረጃው ይጠቁማል ።

አቶ ቴዎድሮስ  አድሃኖም አቶ መለስን ተክተው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ከህወሃት መንደር የደረሱን ምንጮች ይገልጻሉ። አቶ ቴዎድሮስ  አድሃኖም  ከአቶ መለስ ጋር በውንጌት ትምህርት ቤት ጓደኛቸው የነበሩ እና የቅርብ ጓደኛ ሲሆኑ በዜግነታቸው ኤርትራዊ  ትውልዳቸው ራማ እና  የሃማሴን ዝርያ ያላቸው  ናቸው ።

አቶ መለስ በፖለቲካዊ አስተዳደራቸው ዲሞክራሲያዊ መንገድ እንከተላለን ብለው “አቢዮታዊ” “ዲሞክራሲን “በመገነጣጠል ዲሞክራሲን ለነፕሎቶ እና ሶቅራጠስ ብለው እሳቸው ግን አብዮት ልጇን ትበላለች የሚለውን የደርግ ብሂል ተከትለው  ከምርጫ 97 ጀምሮ በግፋዊ አስተዳደር ህዝባቸውን ሲገድሉ እና ሲያሰቃዩ የነበሩ ግፈኛ አስተዳደር እንደሆኑ አለም አቀፍ መንግስታቶች ይጠቁማሉ ። በተለምዶ የተለሳለሰ ፖለቲከኛ በማለት የሚያቆላምጡአቸው አለም አቀፍ መንግስታቶች ለጥቅም ሲሉ ሁሉንም እንብላው የሚል አመለካከት እንዳለባቸው  ጠንቅቀው አውቀዋቸዋል ።በቅርቡም የመገናኛ ብዙሃንን በማፈን በሚል በቁጥር አንድ ከሚጠቀሱት መንግስታት አንዱ በመሆን ስማቸው ሲጠራ  ከነጻው ፕረስ ጀምሮ ጋዠጠኞችን እና ስካይፕ የመገናኛ መድረክ ህዝቡ እንዳይጠቀም ማገዳቸውን አለም አቀፍ መረጃዎች ሲያትቱ ከርመዋል ።ይህ ቤንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በዋለው ችሎት በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ላይ የተመሰረተውን ክስ አስመልክቶ ፍርድቤቱ ውሳኔውን ሲያሳልፍ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በማምራት ለመጠየቅ ብትሞክርም አናገናኝሽም የትም እንዳለ አናውቅም ማለታቸውን ተመስገን ደሳለኝ በፌስቡክ ስታትስ ላይ መግለጹ የመንግስት አስተዳደሩ ምን ያህል ጨቋኝ እንደሆነ የሚገልጽ ነው ።አቶ መለስ ህመማቸው እየከፋ ቢመጣም በየጊዜው ለህክምና ወደ ብራስልስ ቤልጂየም የሚሄዱ ሲሆን እስካሁን ግን ወዴት እና እንዴት እንደሆኑ ዝርዝሩ አልደረሰንም ሲደርሰን እናሳውቃለን  ። ከህወሃት መንደር ላደረሱን ሪፖርት ምስጋናችሁን እናደርሳለን

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on July 31, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 20, 2012 @ 10:58 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar