www.maledatimes.com ይብላኝ ለወለደች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  POEMS  >  Current Article

ይብላኝ ለወለደች

By   /   October 11, 2013  /   Comments Off on ይብላኝ ለወለደች

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 17 Second

ይብላኝ ሇወሇደች

መአዛዋ ጠፍቶ በሃዘን ቆርቁዛ
አንገትዋንም ደፍታ በጣሙን ቀዝቅዛ:
ከመንገድ አግኝቼ ስምዋን ብጠይቃት
ሃገሬን አገኘሁ ሃገር እንደሌላት::

በይ ሂጅልን አልዋት ልብዋን አቆሽሸው
ጡትዎችዋንም ነክሰው ጨቅላ ልጅዋን ነጥቀው:
ባህር ይብላው አልዋት ስደት ያንከራተው::

ጀርባውም ይሸከም በርሃም ይምሇጠው
እግራቸው ይመርቅዝ ይብዛ ስቃያቸው
ስንቱን ጀግና አባብሎ ካኖረው መዳፍሽ
ውሃ ጥም አቃጥሎ ጠኔ ይንገስብሽ?!

ጉልቻው ይቀየር ሌላውም ይተካ
ወጡ እንደው ላይጣፍጥ ጣ‘ሙ ላይቀይር
ከበሮው ይመታ ውዳሴ ይደርደር
ሃገር የሇም ሇኛ ከሆዳችን በቀር!
ብሇው ፈረዱባት ሃገሬን እንደጠላት
ቦጥቡጠው መጠጥዋት:
ወዝዋንም በአመድ
ሇውሰው ሇውሰው ሇውሰው
መቃብርዋን ምሰው!

ሇስዋ ማንም የላት ካሇኛ በስተቀር
ቢሻን በግልምጫ በጡጫ በርግጫ
ቀጥቅጠን ጠፍጥፈን
እንደፈሇግን አርገን
እንገዛሇን ገና……………ወንድስ የት አሇና?
ብሇው ዘበቱባት ሃገሬን በታትነው
ማንም እንደሌላት አይንን በጨው አጥበው::
እንደው ግን….
ጦሙንስ ጦማሇች ……… እግዚኦ እያሇች
ሶላትም ሰግዳሇች ……… ዘካውን ሰታሇች
ታድያስ ምን አጠፋች ምንስ አጐደሇች?
እድሜ ልክ በስቃይ በፍዳ የኖረች?
ይች ሃገር የማን ናት?
በመንገድ የቆመች
በመከራ ወልዳ በ‘ራ የመገበች
በታንኴ ላይ ጭና ሇ‘ዋ የገበረች!
አጥባና ገንዛ በቄስ አስፈትታ:
ካፈር ያልከተተች
ትናንትና ፈጥራ ዛሬን ያላኖረች::
እግዚኦ …… እግዚኦ………
እኔማ እኔ ነኝ
ይብላኝ ሇወሇደች::

በበርሃና በባህር ላሇቁት
አሇማየሁ ጥበቡ
መስከረም 2006 ዓም
ጀርመን::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on October 11, 2013
  • By:
  • Last Modified: October 11, 2013 @ 6:15 pm
  • Filed Under: POEMS

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

አንድዬ

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar