www.maledatimes.com በፖለቲካ ቋሚ ጠላትና ቋሚ ወዳጅ የለም!!! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በፖለቲካ ቋሚ ጠላትና ቋሚ ወዳጅ የለም!!!

By   /   October 18, 2013  /   Comments Off on በፖለቲካ ቋሚ ጠላትና ቋሚ ወዳጅ የለም!!!

    Print       Email
0 0
Read Time:19 Minute, 15 Second

ከዘካሪያስ አሳዬ

ብሶት የወለደው ብሎ ነው ወያኔም ሲታገል የነበረው ብሶት ታዲያ ወያኔን ብቻ አይደለም ወልዶ መአን የሆነው ብሶት እስካለ ድረስ አመፅ አለ።

የግንቦት 7 ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በተናገሩት ንግግር በአለም ላይ መወያያና መነጋገሪያ ሆኖ ነበር እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስተሩ ጨምሮ በኢቲቪ መስኮት ከተናገሩት ንግግር አንዱ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ትግል ነበር።ግንቦት 7ና የኤርትራ ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኖ የተለያዩ ሰዎች ፁሁፎች ይፅፋሉ አንዳንድ ድርጅቶችም መግለጫ  እያወጡ ትክክል አይደለም ከጠላት ጋር አብሮ መውጋት ነው እያሉ መግለጫ ያወጣሉ።አንዳንድ ሰዎች አስተያየት የሚሰጡት ከወዳጅነት የተነሳ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ አላማቸው አይታወቅም። ስለ ኢሳያስ አፈወርቄ የሰጡት አስተያየት አላስፈላጊ ነው ከሚል ይነሳል ምክንያቱም በ principle ደረጃ በኤርትራ በኩል የሚመጣ ማንኛውም ለውጥ ለኢትዮጵያ አደገኛ ነው በሚል አቋም ያላቸው ድርጅቶች አሉ።

ለምን የሚል አስተያየተ የለኝም ግን ስጋቱ ለምን መጣ የሚለውን ማየት ይኖርብናል።ፀረ_ሻቢያ ፕሮፓጋንዳ ላለፉት 17 ዓመት ስለ አሰብ ጉዳይ የተለያዩ ሰዎች ሀሳባቸውን ሲናገሩ ቆይተዋል።ቀጥሎም በባድመ ጉዳይ ህውሃት/ወያኔም ቀጥሎበት ነበር።በህዝቡ ውስጥ ሻቢያና ህውሃት በኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና በግዛቷ ልዋላዊነት ላይ የመጣውን አደጋ የሚረሳ አይደለም በዚህ ሂደት ውስጥ ኤርትራ የምትባል አሁን አገር እንደሆነች የሚረሱ ሰዎች አሉ።ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥላለች።

ኤርትራን በማስገንጠል በኩል የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር ታግለዋል።አነሳሳቸውና ትግላቸው ፀረ_ኢትዮጵያ የሆነ ትግል ሳይሆን የብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ ነው ተብሎ ከተማሪ እንቅስቃሴ ጀምሮ የሚታወቅ ነው።በኋላ ግን አፈታቱ ላይ ከቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ጀምሮ በኋላም ደርግም በወሰደው የኃይል እርምጃ ነገሩ ስር እየሰደደ ለወያኔ መፈጠር ፣ለወያኔ መጎልበት ትልቅ አስተዋፅዎ አደረገ።አሁን አገራችን ኢትዮጵያ ስለደረሰችበት ሂደት ደረጃ ከፍተኛ አስተዋፅዎ ያደረገ ነው።

 

በተለይም ሻእቢያ አጅቦ ቤተ_መንግስት ድረስ በማድረስና በማስገባት በተወሰነ ግዜ በነበራቸው ማሊሙ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚረሳው ነገር አይደለም።ብዙ ሀብትና ንብረት ተዘርፏል፣በአንድ ወቅት ኤርትራዊያኖች የቡና ላኪ እስከሚሆኑ ድረስ ከፍተኛ ደረጃ ደርሰው ነበር።እነኒህ ነገሮች እንዳሉ ሆነው ግን ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኢኮኖሚ ፣የፖለቲካ ፣የማህበራዊ አፈናና የሰብኣዊ ጥሰት በሚመለከት ህዝቡ እየታገለ መሆኑን መርሳት አያስፈልግም።

ህዝቡ ደግሞ የሚታገለው በዲዛይን አይደለም፣በድርጅትም አይደለም ብሶት የወለደው ብሎ ነው ወያኔም ሲታገል የነበረው ብሶት ታዲያ ወያኔን ብቻ አይደለም ወልዶ መአን የሆነው ብሶት እስካለ ድረስ አመፅ አለ።የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የሚታገሉ ህዝቦች አሉ።በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ታግለው ስላቃታቸው የሞት ፍርድና ዕድሜ ልክ የተፈረደባቸው ሀይሎች ደግሞ በሌላ መልክ ትግል ያደርጋሉ።በዚህ ጉዳይ ላይ አቋም በመውሰድ የሚያስፈልገውን ትግል በየት በኩል ይምጣ ፣የቱ ጋር ይደራጅ የሚለው የድርጅቱ ጉዳይ ነው የሚሆነው።

ዛሬ ባለው ሁናቴ ላይ የአቶ አንዳርጋቸው ንግግር በጣም BOLD ሆኖ መውጣት ምንአልባት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህል ውስጥ ያልተለመደና ትንሽ አስቸጋሪ ቢሆንም አሁን ግን እውነታው መድረክ ላይ ስለመጣ የኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካ ስንመለከት ዛሬ ለትጥቅ ትግል አመቺ የሆነ የጎረቤት አገሮች ብዙም የሉም ምንአልባት ወያኔ ሲታገል የነበረበት ጊዜ ሻእቢያ በተደራጀበት ሁናቴ የሱዳን፣የሱማሌ ወይም የሌሎች አረብ አገሮች እርዳታ የለም ዘመን ተቀይሯል፣ጂኦፖለቲካ ተቀይሯል ።

አሁን እውነታው ግን ለጊዜው በሻእቢያና በወያኔ መካከል የተፈጠረ ግጭት አለ።አንዳንድ ሰዎች አሁንም ወያኔና ሻእቢያ አንድ ናቸው የሚል የደረቀ ክርክር አለ።

በፖለቲካ ቋሚ ጠላትና ቋሚ ወዳጅ የለም።ኤርትራ አሁን አገር ናት ኤርትራን እንደ አገር ካየን እንደ ሱዳን እንደነ ኬንያ ነው የምናየው።ስለዚህ የኤርትራ መንግስት ለራሱ አጀንዳ ሊሆን ይችላል ወይም በተለይ ለነኒ ብሶት ለወለዳቸው ታጋዮች የሚለውን የድርጅቱ መልስ ነው።ለምን ግን ግንቦት 7 ላይ ትኩረት እንደተደረገ አላውቅም እንጂ ከዛ በፊት ጫካ የገቡ የአርበኞች ግንባር፣የ T P D F እነኒ ላይ ትኩረት ተደርጎ ሲተች ሰምቼ አላውቅም ዛሬ ለምንድን ነው ግንቦት 7 ላይ ትኩረት እንደተደረገ ግን አይገባኝም።ግንቦት 7 ዛሬ ጫፍ ላይ ያለ ነው ለትግሉ በኤርትራ መንግስት እርዳታ ልናገኝ እንችላለን ጥሩ green light አለ እንዲሁም ያለው እርዳታ በአቶ አንዳርጋቸው አባባል እንዳሉት በአሜሪካ ስብሰባቸው ላይ ከአራተኛ ኮከብ ሆቴልና ከአምስተኛ ኮከብ ሆቴል ያላነሰ እርዳታ ነው የምናገኘው ከምንጠብቀው በላይ ነው ከዚህ በላይም ከኤርትራ መንግስት መጠበቅ የለብንም እዛ ተደራጅተን ትግላችንን በአገራችን ውስጥ እናደርጋለን ነው የሚሉት ይኽንን ደግሞ እሳቸው ጫካ ወርደው 4 አመት ቆይተው አይተው ያሉትን ሲናገሩ እኔ አልቀበልም የሚል የሞራል ድፍረትም የለኝም እዛ ብዙ የታጠቁ ሀይሎች አሉ እዛ ታጥቀው የፖለቲካ leadership and training የሚያስፈልጋቸው ሀይሎች አሉ ለእነሱ leadership የሚያደርግ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ተፈጥሯል ስለዚህ ይህ ግንቦት 7 ሻእቢያ አያንቀሳቅሰውም የሚባል ክስ አለ በአንድ በኩል ደግሞ በሻእቢያ በኩል የሚመጣው ውጤት አስቸጋሪ ነው የሚባል ነገር አለ በዚህ በኩል የሚመጣ ነገር ሌላ ወያኔ ነው የሚመጣው የሚል ክስ ነው።አንዳንዶቹ ደግሞ የግል ጠብ በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ላይ ያለ ይመስላል።አገራዊ ጥቅምና አጀንዳ የጎደላቸው ትችቶች ናቸው የሚቀርቡት በዚህ አስተያየቶች በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ይቆማል ወይ ነው ትልቁ ጥያቄ? መሆን ያለበት ዛሬ ይህ ትግል ሊቆም አይችልም።

ዛሬ በኢትዮጵያ ያሉት  የሰላማዊ ተቃዋሚ ታጋዮችን torture እያደረገ ነው ያለው የወያኔ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በሰጡት መግለጫ 99 የተለያዩ ፓርቲዎች አሉ በየሳምንቱ ሰላማዊ ሰልፍ እየወጣቹ ከምጨውብን ተደራጅታቹ ወጣቹ ብጮሁ ይሻላል ነው ያሉት ዛሬ በሰላማዊ  ፓርቲ  ውስጥ ያሉት አመራሮች አንበርክኮ በመግረፍ እና ሰላማዊ ሰልፍ አትወጡም በማለት የተለያዩ በደል ሲፈፅምባቸው እያየን ምንድነው የሚጠበቀው።

በግል ጥላቻ የተነሳ የተለያዩ አስተያየት ይሰጣል።አንዳንዱ ግንቦት 7 አመፅ እንዲመጣ ይፈልጋል እያሉ ሟርት የሚናገሩ ሰዎች አሉ ለዚህ ሁላ ተጠያቂው ወያኔ ነው ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም፣በፍትህ፣በዲሞክራሲ፣በህግ ህገ መንግስቱን አንተርሶ ጥያቄዎችን እያቀረበ መልስ ሳይሰጠው በየአደባባዩ በጥይት መደብደብ ፣መታሰር ፣መሰደድ ሆኗል መልሱ ስለዚህ አላፊነቱን መውሰድ ያለበት ወያኔ እንጂ ግንቦት 7 አይደለም።

ታዲያ ግንቦት 7 ብረት አንስቶ ቢታገል ምንም አይገርምም በተለይ ለውጥ ፈላጊ ነን የሚሉ ድርጅቶች ይህን የትግል አጋር መሆን ሲገባ ትችቱ ከየት የመጣ ነው ? ወያኔ አምባገነን ስርዓት ነው እያሉ ትግል ደግሞ አያስፈልግም ማለት ከሀሳባቸው ጋር የሚጣረስ ስለሆነ እራሳቸውን ዞር ብለው ቢመለከቱ መልካም ነው።

ሰርቶ ማሳየትነውእንጂተቃዋሚሆኖመግለጫማውጣህዝብንማደናገርይብቃ።አንዳንድተቃዋሚእንዴትመታግልእንዳለባቸውየገባቸውአይመስለም::ትግልምንእንደሆነምየሚያውቁአይደሉም::ማነንነውየምታሰተባብሩትለሚለውጥያቅምመልስየላቸውም::በአንድቦታተሽጉጠውመግለጫማውጣትብቻነውስራቸው::መግለጫማውጣትየትግልውጤትአይደለም::የሚጨበጥናየሚታይነገርይዞብቅማለትይሻላል::ታግሎውጤትማምጣትከአልተቻለቦታውንለሚታገሉድርጅቶችበስላምናበቅንነትመልቀቅእራሱአገርንእንደመርዳትይቆጠራል::ከፈረሱጋሪውይቀድማልብሎማስብዓይነትትግልከመታገልበሚመጥናቸውቦታመስማራትይገባል:: ለትግልየሚሆንድርጅትአይደለም::የሚሰራውንድርጅትከመተቸትአለንየምትሉከሆነአቅርቡትእንይላችሁ::

ኢትዮጰያ፣ኢትዮጵያ›ማለትብቻውንጉንጭንማልፋትነው፤የወገንፍቅርይኑረን–ያንንምበተግባርናለማስመሰልሣይሆንከእውነትእናሳይ፤አናቱንየሚያሳክከውንእግሩንብናክለትኅሊናችንምታካኪውምይታዘቡናልናበአፋጣኝእንለወጥ፤በሞተሕዝብላይለመንገሥከምንራወጥየሚሞተውንሕዝብጠላቶቻችንናቸውብለንከፈረጅናቸውወገኖችጋርምቢሆን“ተመሳጥረን”እናድነው፤ከወገንጋርተባብሮናተመሳጥሮሕዝብንከመግደልይልቅከጠላትጋርተባብሮሕዝብንማዳንበፈጣሪምበታሪክምታላቅዋጋአለውናአሁንለአቃቂርናለወሬስለቃጊዜእንዲኖረንፈቃዳችንአይሁን፡፡ለዚህየተቀደሰተግባርደግሞሁሉም ወገንመተባበርአለበት፡፡ወገንእየተሰቃዬ፣እየተሰደደ፣አካሉእየተቆራረጠናለመለዋወጫነትእየተሸጠ…ባለበትየሚዘገንንሁኔታበድሎትናበቅንጦትመኖር፣ገንዘብንምበአልባሌሥፍራናለአልባሌተግባርማዋልበእግዚአብሔርዘንድበኃጢኣተኝነትባይሆንምእንኳንበነውረኝነትሳያስፈርጅየሚቀርአይመስለኝም፡፡እናምከዚህአንጻርብዙዎቻችንብዙመሥራት፣ራሳችንንምበጥሞናናበተመስጦመፈተሸይጠበቅብናል፡፡በተለይምእዬዬምሲደላነውናሕዝባችንላይየተሰኩትንእሾሆችለመንቀልምንምጥረትሳናደርግናፈቃደኝነትሳይኖረንእርስበርስበነገርጦርብንጠዛጠዝታሪክምሮአይምረንም።

ከዘካሪያስ አሳዬ

edenasaye@yahoo.com

 

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on October 18, 2013
  • By:
  • Last Modified: October 18, 2013 @ 2:14 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar