www.maledatimes.com ምክር ለኢህአዴግ (ምፀታዊ ፅሁፍ ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ምክር ለኢህአዴግ (ምፀታዊ ፅሁፍ )

By   /   October 23, 2013  /   Comments Off on ምክር ለኢህአዴግ (ምፀታዊ ፅሁፍ )

    Print       Email
0 0
Read Time:16 Minute, 24 Second

አሁን አሁንማ ኢህአዴግ እናቱ እንደሞተችበት ህፃን አንጄቴን እየበላው ነው፡፡ከልቅሶየ ብዛት የተነሳ እድርተኞች ዘመድ የሞተብኝ 
ስለመሰላቸው ድንኳን ጥለው
‹‹እግዚብሄር ያፅናህ
››፤
‹‹አይዞህ ቻለው
››፤
‹‹
እግዲህ ጠንከር ማለት ነው መቼስ ምን ይደረጋል አፈር ነህና
ወደ አፈር ትመለሳለህ ተብሏልና
›› ሲሉኝ ከመደንገጤ የተነሳ እንባየን በጋቢየ መጠራረግ ጀመርሁ፡፡ጥሩምባ ሳላስነፋ፤ዘመድ ሞተብኝ
ሳልል ሰው እንዴት ደርሶ ድንኳን ቤቴ ላይ ይጥላል ?ሰው መሞት አቁሟል እንዴ ?ሞት ብርቅ ቢሆን ነው እንጅ እንዴት ሰው ባለቀሰ
ቁጥር ድንኳን ይተከላል ?እኔን ያስለቀሰኝ ኢህአዴግ ነው እንጂ መቼ ሰው ሞተብኝ አልሁና፡፡
አባወራው የሞተበት ኢህአዴግ ገና አልቅሶ ሳይወጣለት፤ተስካር ሳናወጣ፤እንባችን ሳይደርቅ የአመፅ ወሬ ሲናፈስ ስሰማ እንባየን
መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ድፍን 80 ሚሊዮን ህዝብ በኢቲቪ እየቀረበ እንባውን በሊትር እንዳላሰመዘገበ ሁሉ ከልቅሶው ማግስት የአመፅ
ወሬ ስሰማ አዘንኩኝ፡፡እንዲያው ያኔ ያላለቀሰ ሰው አለ እንዴ ብየ ወደ ኢቲቪ ዶክምንቴሽን ክፍል ሂጀ ላጣራ ሳስብ
‹‹ኢቲቪ
ያላሰለቀሰው ማን አለና ?
››ብየ ተውሁት፡፡
አሁን ልቅሶየን ትቼ ላሳዘነኝ፤አንጀቴን ለበላው ለፀሀዩ፤ለወጋገኑ ለኢህአዴግ ከእኔ ውጭ ጥሩ መካሪ የለውምና ልመክረው
ተነሳሁ፡፡
ያው እንደምታውቀው
‹‹ምላስ እንጅ ጆሮ የለህም
››የሚሉህን ስለማልቀበላቸው ጆሮ የሚገባ ምክር ይዤልህ መጣሁ፡፡ምክሬ ምን
መሰለህ ህዝቡ የትዕግስትህንና የቻይነትህን ብዛት አይቶ በአንተ ላይ ሲያምፅ ብዙ ፖሊስ፤ፌደራል፤ወታደር፤ሰላም አስከባሪ፤ጆሮ
ጠቢ፤አስለቃሺ ጭስ፤ዱላ፤ካራቲስት፤ፎረም ወዘተ አያስፈልግህም፡፡ይሄ አድካሚና ብዙ ወጭ ማውጣት ነው፡፡ደግሞም …
የ 19 ኛው ክ /ዘመን እንጂ የ 21 ኛው ክ /ዘመን አስተሳሰብ አይደለም፡፡በዚህ ፈንታ አዋጭው ምን መሰለህ እንደ ባቢሎን
ቋንቋቸውን መደበላለቅ ነው ለዚህም ለአንድ ሰው አንድ ልዩ ቋንቋ በሚል መንቀሳቀስ አለብህ፡፡ህዝቡ በአንድ ቋንቋ
ስለሚነጋገር ለመግባባት ብሎም ለአመፅ ስለተመቸው ይሄን ልማታዊ ቋንቋ ማስተማር አለብህ፡፡ጭቃ ሲል ድንጋይ፤እንጨት
ሲል ውሀ እንዲቀባበሉ ማድረግ በአጭሩ እንዳይግባቡ ማለት ነው፡፡ይህን ለማድረግ እያንዳንዱን ሰው በተናጠል ልማታዊ
ቋንቋ በሚል ዘመቻ ማስተማር ነው፡፡ከዚያም በአጭር ጊዜ ውስጥ የብሄረሰቦች ቁጥር ከ 80 ወደ 80 ሚሊየን አሳደገህ ማለት
ነው፡፡ከዚያ 80 ሚሊየን የብሄር ፓርቲ ይመሰረታል፡፡ይህ ደግሞ የመድበለ ፓርቲ ዴሞክራሲ ለመስፈኑ ማረጋገጫ ነው ብለህ
ለምዕራባውያን ማሳያ ይሆናል ማለት ነው፡፡አየህ ይህ አዲስ ቋንቋ ጠቀሜታው ዘርፈ ብዙ ነው፡፡
እንዴት መሰለህ አነሳሳቸው ወደ አንተ፤ወደ 4 ኪሎ፤ወደ ከፍታህ ስለመጡብህ እንዲያውም አብሶ በጉዳያችን ገባህብኝ ብለው
ስላመፁ እንዳይግባቡና እቅዳቸውን እንዳይፈፅሙ ምክሬን ተግተህ ተግባሪዊ ማድረግ አለብህ፡፡አለበለዚያ
ይግባቡብሀል፤ይነጋገሩብሀል፤ይደማምጡብሀል፤ይደማምጡሀል፡፡
ለሚያምፀው ህዝብ በተናጠል ይሄን አዲስ ልሳን (አዲስ ራዕይ አላልሁም ) የሆነ ነገር ልማታዊ ቋንቋ በደንብ ታስተምራቸዋለህ፡፡
በቀደመው ቋንቋቸው እንዳይነጋገሩ በፓርላማ ህግ ታወጣለህ፡፡አያይዘህም የማስፈፀሚያ አዋጅ፤ደንብና መመሪያወችን
ታወጣለህ፡፡በቀደመው ቋንቋ ሲነጋገር የተገኜን ካስፈለገ በፀረ -ሽብር ህጉ ታስፈርድበታለህ፡፡አዲሱን ቋንቋ (ልማታዊውን)
ለማስተማር ደግሞ ብዙ መምህራንን መቅጠርና ተጨማሪ ኮሌጆችንና ዩኒቨርስቲወችን መክፈት አይጠበቅብህም፡፡ከዚህ በፊት
ታደርገው እንደነበረው እእ ….ህዝቡ ፈቃደኛ ከሆነና እሺ ካለህ መስጊድ ወይም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንድ ካድሬ (ቢቻል
ቁጥራቸው በርከት ቢል ) መድበህ ለእያንዳንዳቸው በተናጠል
ማታዊውን ቋንቋ ታስተምራቸዋለህ፡፡መቼስ ህዝቡ ከፈቀደ ምን የማይቻል ነገር አለ ብለህ ነው፡፡አዲሱ ቋንቋ ካልገባቸው ደግሞ
በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ስም ብታጠምቃቸው የያዛቸው አጋንንት ጮሆ ሲወጣ ልክ እንደ ሀዋሪያት በአዲስ ልሳን ልማታዊውን ቋንቋ ያንቦለቡሉታል፡፡
‹‹ይሄ ህዝብ ወርቅ ብታቀርብለት ፋንድያ ነው የሚልህ
››እንደተባለው ይሄ የአህባሽ ነው ይሄ የእንትን
ነው ካሉህ ደግሞ የሚከተለውን ትሞክራለህ፡፡ተስፋ አለመቁረጥ ነው አለበለዚያ ….
እ….ምን መሰለህ ህዝቡ በሚሰበሰብበት ቀን በተለይ በቦአዚዝ የእድሜ ክልል ያሉትን መርጠህና ሰብስበህ ወደ ቃሊቲ፤ወደ
ዝዋይ፤ወደ ደዴሳ ወደ መሳሰሉት ጥራት ያለው ትምህርት ወደ ሚሰጥባቸው ተቋማት ወስደህ በደረጃ 1፣ደረጃ 2፣ደረጃ 3፣ደረጃ
4 እንዲሁም ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ልማታዊውን ቋንቋ ታስተምራቸዋለህ፡፡አዲሱን ቋንቋ ቶሎ
እንዲለምዱት ይሄ ጠያቂ፤ሂዩማን ራይት ወች፤ሲፒጀ፤ቀይ መስቀልና ዘመድ አዝማድ የሚባል ነገር ሲመጣ በምልክት ብቻ
እንዲግባቡ በፓርላማ ህግ ታወጣለህ፡፡በቀደመው ቋንቋ ሲናገር ተገኘ ምላሱ እንዲቆረጥ የሚያዝ አንቀፅ ካስገባህ በአቋራጭ
አዲሱን ቋንቋ ከማስተማር ተገላገልህ፡፡በቃ እንደ በግ ላት ምላስ ምላሱን መጎንደል እንጅ የምን ልፋት ነው፡፡ግን ይሄ ጥሩ
አይደለም ምክንያቱም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ኒዮ ሊበራሎች የመብት ጥሰት ብለው ቢጮሁ ብድርና እርዳታ
ያስከለክላሉ፡፡በብድርና እርዳታ ላይ
‹‹ውሾች ይጮሀሉ ግመሎች ግን ጉዟቸውን ቀጥለዋል
››አይባልምና፡፡
ህግ ስታወጣ ብዙ ተቃውሞ አይገጥምህም፡፡አቶ ግርማ ሰይፉም ቢሆኑ
‹‹አንድ እንጨት አይነድም
››ነውና ብዙ አያስቸግሩም፡፡
ከግምታችን ወጥተው ህግ እንዳይወጣ የሚስቸግሩ ከሆነ ለእርሳቸው ደግሞ ሌላ አዲስ ቋንቋ ማስተማር ነው፡፡ያኔ በቃ ዲዳ
ሆኑ እርፍ ነው፡፡ይህኔ ነው እንግዲህ ቶሎ ብሎ የፈለጉትን ህግ ማውጣት፡፡
መቼም ነፃ ገበያ ነው ብለህ ትምህርቱን ለግል ባለሀብቱ ክፍት እንዳታደርገው፡፡ያው እንደምታውቀው የኛ ሀገር ባለሀብት
ኪራይ ሰብሳቢ ነውና የትምህርቱን ጥራት ላይጠብቅ ይችላል፡፡ግን ችግር የለውም መጨረሻ ላይ የብቃት ፈተና መፈተንም
ይቻላል፡፡ከዚያም በደንብ የማያስተምሩ የግል ተቋማትን ትዘጋቸዋለህ አለበለዚያም ባለሀብቶቹን በኪራይ ሰብሳቢነት ወደ
ልማታዊ ባለሀብትነት እንዲቀየሩ ልማታዊ ቋንቋ ታስታስተምራቸዋለህ፡፡ለነገሩ ባለሀብቱ እንኳ በዚህ ዘርፍ ላይገባ ይችላ
ምክንያቱም ዘርፉ አዋጭ አልመሰለኝም፡፡ሌላውም የህብረተሰብ ክፍል በዚህ ትምህርት የሚተባበር አይመስለኝም ምክንያቱም
ተማሪ መቀስቀስና መቆስቆሱ ሰልችቶታልና፡፡ያው የህዝብ፤የሀገር ና የታሪክ አደራ ስላለብህ አንተ በነካ እጅህ እዛው
ብትጨርሰው ጥሩ ነው፡፡ራዕዩም የአንተና የእንቶኔ ተብሎ ይወራል፡፡በቃ ታሪክ፤ክብርና ስልጣን ማጋራትን ተወው አትውደድ
አንተ ጨርሰው የምን ማጋራት ነው፡፡
ከዚህ ሁሉ ጥረትህ በኋላ እያንዳንዱ በልማታዊ ቋንቋ መናገር ሲጀምር አንተ እርፍ ትላለህ፡፡ባለ ራዕዩ መሪያችን አመፅ ሲነሳ
ሲያዳፍኑ ሲነሳ ሲያዳፍኑ ኢኮኖሚያችንን በሁለት ዲጅት ገድበውት ቀሩ፡፡አሁን ግን የሚያምፅ፤የሚረብሽ ና የሚያስቸግር
ስለሌለ አይደለም ከአፍሪካ ከዩኒቨርስም ቢሆንአንደኛ፤የመጀመሪያ፤ቀዳሚ፤ተጠቃሺ፤ ባለ … 5፤ባለ 8፤ባለ 10 ዲጅት አሀዝ
የሚያድግና የሚመነደግ ኢኮኖሚ መገንባት ይቻላል፡፡ለዚህ ደግሞ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ሳይሆን ልማታዊ ቋንቋ
ወሳኝነቱ የጎላ ነው፡፡
ከአዲስ ዘመን ጋዜጣና ከኢቲቪ ውጭ ያሉትን የግል ጋዜጦች ካስቸገሩህ እነሱንም ከፕሬስ ህጉ ጋር ልማታዊ ቋንቋ ማስተማር
ነው፡፡ አሁን የሁሉም ቋንቋ ፈጣሪና አስተማሪ ስለሆንህ ለአዲስ ዘመንና ለኢቲቪ ጋዜጠኞች አስተረጓሚ ትመድብላቸውና
እንደፈለገህ እያስተረጎምህ ለፖለቲካ ፓርቲወች በተለይ ለሰማያዊ ፓርቲና ለአንድነት በዜናና በዶክመንታሪ ፕሮግራም
ታቀርብላቸዋለህ፡፡በተለይ ደግሞ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪወች ልማታዊ ቋንቋ በመማራቸው በኑሯቸውና በገቢያቸው ላይ
ለውጥ ማምጣቱን ገለፁ የሚል ዜና ካሰራህ በቃ ተደላደልህ፡፡እድሜ ለልማታዊው ቋንቋ አይደለም 50 ና 100 አመት አልፋና
ኦሜጋ መሆን ትችላለህ፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on October 23, 2013
  • By:
  • Last Modified: October 23, 2013 @ 12:22 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar