www.maledatimes.com “ባድሜ የኤርትራ ነው::” አቶ በረከት ስምኦን - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“ባድሜ የኤርትራ ነው::” አቶ በረከት ስምኦን

By   /   October 23, 2013  /   Comments Off on “ባድሜ የኤርትራ ነው::” አቶ በረከት ስምኦን

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 40 Second

minilik salsawi
የድሪምላየን ሆቴል ባለአክሲዮን የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን በኤርትራውያን የፓልቶክ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው መንግስታቸው ባድሜ የኤርትራ ህዝቡም እርትራዊ ነው ሲሉ መስክረዋል::ይህም በሕወሓት ኢሕኣዴግ ውስጥም የሚታመንበት እንደሆነ የተናገሩት አቶ በረከት ከኢትዮጵያ የድንበር ከተሞች አብዛኛዎቹ የኤርትራ ስለሆኑ ሊመለሱ ይገባል ፌዴራል መንግስታችን ደሞ ይህን ያምናል ብለዋል::

የትግራይ ህዝብ በተለይም የመከላከያ ሰራዊቱ ጥያቄ ማንሳቱን ተከትሎ የሄግ ውሳኔን በተግባር ለማዋል ያልቻሉት የወያኔ ባለስልጣናት ባድሜን አሳልፈው ለመስጠት መቸገራቸውንም አቶ በረከት ለኤርትራውያኑ በፓልቶክ መድረኩ አልሽሸሸጉም::
በተለያዩ ጊዜያት ከሕግዴፍ ሰዎች ጋ ተገናኝተው እንደሚነጋገሩ ያወሱት አቶ በረከት በአፋጣኝ ባድሜን እና ሌሎች ኤርትራ የጠየቀቻቸውን የድንበር ከተሞችን ለማስረከብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አምነዋል::አቶ ኢሳያስን ለማነጋገር ሞክረን አልተሳካም ያሉት አቶ በረከት ለኤርትራ እና ለኤርትራውያን መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ በአጽንዎት ተናግረዋል::

ከካፒቴኑ ጋር የድሪምላየን ሆቴል ባለድርሻ የሆኑት አቶ በረከት በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ላይ ማሴር አይሆንም የሚል ጠንካራ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ለማድበስበስ ሞክረዋል::የባድሜን መሬት ለእርትራውያን ካስረከቡ በኋላ የትግራይ ህዝብ ስሜት ምን ይሆናል? ባድመን ነጻ ለማውጣት የተሰዉ የኢትዮጵያ ወታደሮች መቃብር ስፍራ በሻእቢያ ተቆፍሮ ሲወጣ እና ሲጣል ኢትዮጵያውያን ስሜታቸው ምን ይሆን? የትግራይ ህዝቦች አንጡራዊ ሃብት የሆነው የባድመ ወርቅ ስፍራ በሻእቢያ እየተቆፈረ ወደ አስመራ ሲጋዝ የትግራይ ህዝብ ስሜት ምን ይሆናል? አቶ በረከት ሳይመልሱ አድበስብሰው ያለፉት ጥያቄ::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on October 23, 2013
  • By:
  • Last Modified: October 23, 2013 @ 12:44 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar