www.maledatimes.com አቶ ሐብታሙ አያሌው ዛሬ ፍ/ቤት ይቀርባሉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አቶ ሐብታሙ አያሌው ዛሬ ፍ/ቤት ይቀርባሉ

By   /   October 23, 2013  /   Comments Off on አቶ ሐብታሙ አያሌው ዛሬ ፍ/ቤት ይቀርባሉ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 2 Second

 

በዘሪሁን ሙሉጌታ
የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት አባልና የፓርቲው ምክትል የሕዝብ ግኝኑነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሐብታሙ አያሌው በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።
አቶ ሐብታሙ ከአንድ ዓመት በፊት ታህሳስ 16 ቀን 2005 ዓ.ም አንድን ግለሰብ “አንተ የወያኔ ካድሬ አንገትህን ነው የምቆርጥህ ብለው ዝተውብኛል” በማለት የቀረበባቸውን የዛቻ ክስ ለመከላከል በዛሬው እለት በፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የመከላከያ የሰው ምስክሮችንና የሰነድ ማስረጃ ይዘው ይቀርባሉ።
አቶ ሐብታሙ በክሱ ላይ ባለፈው አንድ ዓመት አካባቢ ለአምስት ጊዜያት ያህል ፍ/ቤት መቅረባቸውን የገለፁ ሲሆን ከእሳቸው ጋር ተባባሪ ተብለው የተከሰሱ ሁለት ሰዎች መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ መሰናበታቸውንና እሳቸው ግን መከላከል እንዳለባቸው ፍ/ቤቱ በመበየኑ መከላከያቸው ዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2006 ዓ.ም ፍ/ቤት ቀርበው እንደሚያሰሙ አስታውቀዋል።
የክሱ አቤቱታ የቀረበባቸው የባለ ራዕይ ማህበር ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት ዛቻ ተፈፅሞብኛል ያሉት ግለሰብ ዘጠኝ ሰዎችን በቡድን ይዘው በመምጣት የአባልነት ጥያቄ ቢያቀርቡም የማህበሩ አባል ለመሆን በቡድን ሕጉ ስለማይፈቅድ በግለሰብ አባል እንዲሆኑ ከማሳሰብ ባለፈ ዛቻ አለመፈፀማቸውንና ሰዎችም ላይ ለመዛትም የግል ስብዕናቸው እንደማይፈቅድ ተናግረዋል።
ክሱም የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸውን ለመንካት ከሚደረግባቸው ጫናዎች መካከል አንዱ ሊሆን እንደሚችልም ያላቸውን ጥርጣሬ ገልጸዋል።
አቶ ሐብታሙ ቀደም ሲል በወጣቶች የፌዴሬሽን አመራርነት በኢህአዴግ አባልነትና በልዩ ልዩ አመራርነትና የቦርድ አባልነት ደረጃ ሲንቀሳቀሱ ቆይተው በኋላም ከኢህአዴግ በኀሳብ በመለየት ባለራዕይ የወጣቶች ማህበር ካቋቋሙ በኋላ እንደገና ከማህበሩ አመራርነት በመልቀቅ አንድነት ፓርቲን መቀላቀላቸው ይታወሳል።n
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on October 23, 2013
  • By:
  • Last Modified: October 23, 2013 @ 9:55 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar