www.maledatimes.com አዲሶቹ የኢዴፓ አመራሮች ዛሬ መግለጫ ይሰጣሉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አዲሶቹ የኢዴፓ አመራሮች ዛሬ መግለጫ ይሰጣሉ

By   /   October 23, 2013  /   Comments Off on አዲሶቹ የኢዴፓ አመራሮች ዛሬ መግለጫ ይሰጣሉ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 30 Second
 
በዘሪሁን ሙሉጌታ
ሰሞኑን ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ አዳዲስ አመራሮችን የመረጠው የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኤዴፓ) አዳዲሶች አመራሮች ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጡ ፓርቲው አስታወቀ።
የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለሰንደቅ ጋዜጣ እንዳስታወቀው አዳዲሶቹ የፓርቲው አመራሮች የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎችና አቋሞች እንዲሁም በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ገልጿል።
ዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2006 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል ከአስር ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ዘጠኙ የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ አባላት እንደሚታወቁም ፓርቲው ጨምሮ አስታውቋል።
ኢዴፓ ቀደም ሲል ፓርቲውን ሲመሩ የነበሩ እነ አቶ ልደቱ አያሌውና አቶ ሞሼ ሰሙ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት በመያዝ ፓርቲውን ሙሉ በሙሉ በሚያስችል መልኩ በአዳዲስ አመራር አካላት መተካቱ ይታወቃል።
ፓርቲው ሰሞኑን በቅሎ ቤት አካባቢ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ አቶ ጫኔ ከበደን ፕሬዝዳንት፣ ዶ/ር ባንተይገኝ ታምራትን ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም አቶ ሳህሉ ባዬን ደግሞ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አድርጎ መምረጡ አይዘነጋም።n
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on October 23, 2013
  • By:
  • Last Modified: October 23, 2013 @ 9:56 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar