www.maledatimes.com ጠ/ሚ ኃይለማርያም ከማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አንድነት አሳሰበ- MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ከማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አንድነት አሳሰበ

By   /   October 23, 2013  /   Comments Off on ጠ/ሚ ኃይለማርያም ከማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አንድነት አሳሰበ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 46 Second
 
በመስከረም አያሌው
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ካለፈው ስህተታቸው በመማር ከአጉልና ማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አሳሰበ።
ፓርቲው ከትናንት በስትያ ባወጣው መግለጫ እንደገለፀው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ባለፈው ሳምንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በመሪ ደረጃ በማይጠበቅ መልኩ የአንድነትን እንቅስቃሴ ስም ለማጥፋት በመሞከራቸው ከዚህ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የራሳቸው አጀንዳ የላቸውም፣ የሻዕቢያ መልእክት አድራሾች ናቸው ያሉት የራሳችን አጀንዳ እንዳለን ጠፍቷቸው ሳይሆን ሆን ብለውና አቅደው ስም ለማጥፋት እንዲሁም ህዝቡ ውስጥ ጥርጣሬ ለመጫር በመፈለግ ነው ብሏል።
ፓርቲው ተላላኪነቱ ለኢትዮጵያ ህዝብና ይጠቅማል ብሎ ለቀረፃቸው የፖለቲካ ፕሮግራም ብቻ መሆኑን የገለፁ ሲሆን፤ እንዲህ አይነቱን ስም ማጉደፍም በቸልታ እንደማያልፈው ገልጿል። በተጨማሪም የሙስሊም ወገኖችን ጥያቄ በተመለከተ ፓርቲው በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ይመለስ፣ ዜጎች የመብት ጥያቄ ሲያነሱ መፈረጁ ይቁም እንዲሁም ካለአግባብ የሃይማኖት ነፃነት ጥያቄ በማንሳታቸው ወደ እስር ቤት የተወረወሩ ዜጎች በአስቸኳይ ይፈቱ የሚል ጥያቄ ማንገቡን ፓርቲው ገልጿል። በመሆኑም ፓርቲው ከኢፍትሃዊት ጋር እንደማይደራደር እና እንደማይቀበለው አመልክቶ፣ ፓርቲውን ከሙስሊም ወገኖች ጥያቄ ጋር በማያያዝ ትርፍ ፍለጋ መሯሯጥ ወንጀል ነው ብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰላማዊ ሰልፍን በተመለከተ የተናገሩት በህገ መንግስቱ የተቀመጠውን መብት በአደባባይ የጨፈለቀ ነው ብሏል ፓርቲው። ሰላማዊ ሰልፍ ለሚያደርጉ በቂ ጥበቃ የለንም በሚል ተልካሻ ሰበብ የዜጎችን መብት መንጠቅ እንደማይቻል የገለፀው ፓርቲው፤ ጥበቃ ማድረግ ያልቻለ መንግስትም ስልጣኑን ለህዝብ በማስረከብ ይቅርታ ጠይቆ መሄድ እንጂ ከአሁን በኋላ መብታችሁን አታገኟትም ብሎ መዛት ትዝብት ላይ ይጥላል ብሏል።
ፓርቲው አያይዞም የአፍሪካ መሪዎች ተሰብስበው አይ ሲሲ ሊከሰን አይገባም ሳይሆን ማለት ያለባቸው፣ የዜጎቻቸውን እንባ ማበስ እና ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲረጋገጡ መጣር ነው ብሏል። መሪዎች በርካታ መፍትሄ ፈላጊ ችግሮች ባሉባት አፍሪካ ተሰብስበው እንግደል፣ እንሰር፣ እንጨፍጭፍ፣ ዘር እናጥፋ፣ ዜጎቻችንን እናሰቃይ ግን መታሰርም፣ መከሰስም የለብንም የሚለው አቋም አሳፋሪ በመሆኑ ፓርቲው እንደማይቀበለው ገልጿል። በመሆኑም ዜጎች ላይ ግፍና ስቃይ የሚፈፅሙ ሁሉ ሳይውል ሳያድር ወደ ፍርድ መቅረብ አለባቸው በማለት፤ አንዳንድ የአፍሪካ መሪዎች አይሲሲን በተመለከተ የሚያራምዱትን የአትክሰሱን አቋም ፓርቲው እንደማይቀበለውም ገልጿል። n
(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 9ኛ ዓመት ቁጥር 424 ረቡዕ ጥቅምት 13/2006)
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on October 23, 2013
  • By:
  • Last Modified: October 23, 2013 @ 9:58 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar