www.maledatimes.com ወሲብ ምን ይሰራል? – ጃፓኖች !አድማስ ሬዲዮ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ወሲብ ምን ይሰራል? – ጃፓኖች !አድማስ ሬዲዮ

By   /   October 24, 2013  /   Comments Off on ወሲብ ምን ይሰራል? – ጃፓኖች !አድማስ ሬዲዮ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 59 Second

ከዓለም ታላልቅ ኢኮኖሚ ባለቤቶች አንዷ የሆነችው ጃፓን የህዝቧ ብዛት በዚሁ ከቀጠለ፣ በ2060 ዓ.ም ፣ እንክውን ሊጨምር፣ ጭራሽ አሁን ካለው በ1/3ኛ ሊቀንስ እንደሚችል እየተነገረ ነው።

ይህ የሆነው ደግሞ ጃፓናውያን ወጣቶች፣ የውነት ትዳር ከመመስረት ይልቅ፣ በኮምፒውተር ጌም የውሸት ትዳር መጫወትን መርጠው በመገኘታቸው ነው። በዚህም የተነሳ ለወሲብ ያላቸው ስሜት በጣም ቀንሷል. . ይላል ቢቢሲ።

እስቲ በቁጥር እንየው።

የጃፓን የህዝብ ቆጠራ መስሪያ ቤት እንዳጠናው በ2010 ዓ.ም 39% የሚሆኑት ጃፓናውያን ወንድ ወጣቶች ለወሲብ ምንም ስሜት እንደሌላቸው መናገራቸው ሲመዘገብ፣ ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ይህ ቁጥር በሁለት እጥፍ ማደጉ ተነግሯል። የሚገርመው በፍቅር ግንኙነት ያሉ ጃፓናውያን እንኳን ለወሲብ ያላቸው ስሜት አነስተኛ ነው፣ በቅርቡ በተደረገ ጥናት፣ ከነዚሁ ጥንዶች መካከል በሳምንት ቢያንስ አንድ ቀን ወሲብ የሚፈጽሙት 27% ብቻ ናቸው። ከጋብቻ ውጭ የሚወለዱ ህጻናት ቁጥር 2% ብቻ መሆኑ ጭራሽ ክጋብቻ ውጭ ልጅ እንደማይታሰብ ነው። ያገቡትም ቢሆኑ ልጅ የመውለድ ፍላጎታቸው በጣም ዝቅተኛ ነው።

እንደዚያም ሆኖ ወደ ጃፓን የሚፈልስ መጤ ወይም ስደተኛ ቁጥርም ትንሽ መሆኑ የወደፊቱን የጃፓን ህልውና የሚያሳስብ ሆኗል። ለምሳሌ እንግሊዝ ውስጥ ከ 8ቱ አንዱ ሌላ አገር የተወለደ (መጤ) ሲሆን፣ በጃፓን ግን ከ60 አንዱ ብቻ ነው ሌላ አገር የተወለደ። እንግሊዝ አገር 60ሺ ከውጭ አገር የመጡ (የውጭ ትውልድ ያላቸው) ሃኪሞች ሲኖሩ፣ በጃፓን 60 ብቻ ናቸው።

ጃፓን ህዝቧ እየቀነሰ፣ ወሲብ አልፈልግም እያለ፣ በትዳር ተጣማሪው ቁጥር በ እጅጉ እየቀነሰ፣ በስደት ሰዎች እንዳይመጡባትም ህጓን በጣም አጥብቃ እስከመቼ ትዘልቃለች? በርካታ የጃፓን ወንዶች በኮምፒውተር ጌም የሚያገኟትን ፍቅረኛ፣ እንደ ፍቅረኛ እያዩ በመዝናናት ላይ ናቸው። የ እውነት ፍቅረኛ ቢቀርብንስ ባይ ሆነዋል። ቢቢሲ ዘገበው፣ ድንቅ መጽሔት -አትላንታ በራሱ ዘይቤ ተረጎመው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on October 24, 2013
  • By:
  • Last Modified: October 24, 2013 @ 7:15 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar