www.maledatimes.com ETHIOPIAN PROTEST AGAINST SAUDI ARABIA IN CHICAGO - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ETHIOPIAN PROTEST AGAINST SAUDI ARABIA IN CHICAGO

By   /   November 21, 2013  /   Comments Off on ETHIOPIAN PROTEST AGAINST SAUDI ARABIA IN CHICAGO

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 45 Second

በቺካጎ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አሶሴሽን ኦፍ ቺካጎ አለመገኘቱ ብዙሃኑን አስቆጥቶአል ።ለኢትዮጵያን ህዝቡ ያልሆነ ኮሙኒቲ ለማን ሊሆን ነው ያረጀ እና ያፈጀ ፖለቲካ ይዞ መንቀሳቀሱ የሚጠቅመው ሳይሆን የሚጎዳው ነው ፣በተጨማሪም ይህ ዘር ቀለም ጾታ እና ዜግነት ሳይለይ እየተጨፈጨፉ ባለበት በዚህ ሁኔታ ላይ በአሜሪካ መንግስት በጋራ ለመስራት የኮሙኒቲው ቆራጥነት መኖር ሲገባው ገለልተኛነቱን ማሳየቱ አሳፋሪ ነው ሲሉ አንዳድን ነዋሪዎች ሃሳባቸውን ለማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል አቅርበዋል ።
ስማቸው እንዳይጠቀስ አንድ የኮሙኒቲው አባል እንደተናገሩት ከሆነ የኮሙኒቲው አስተዳደር የሆኑት ዶ/ር እርቁ ይመር በቺካጎ የሚገኙትን ትልልቅ ባለስልጣናት በማወቅም ሆነ የሚዲያ አካላቶችን በማናገር ይህንን ሰልፍ እቅዱን ተግባራዊ እንዲሆን ማስፈጸም ይችሉ ነበር ሆኖም ግን አለማድረጋቸው አሳፋሪ ነው ሲሉ ተችተዋል ።
በሌላም በኩል ደግሞ ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው በፖለቲካ ጉዳይ ላይ መዘርዝር በየሚዲያው ከሚያቀርቡ እና ከሚቆሙ ለምን እንደዚህ አይነት ከፍተና ቁጣን ላስነሳ እና ሰበአዊ መብትን ለሚያስከብር እና ሊያስጠብቅ ጩኸት ድምጻቸውን ሊያሰሙ አልቻሉም ?ሰምተው እንዳልሰሙ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የኢትዮጵያን ህዝብ ድምጽ ተሸሽጎ እንዲቀር የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው ፡፤እንደዚህ የሚያደርጉት ለሃገር ክብር ሳይሆን ለራስ ጥቅም መስሎአቸው ከሆነ ተሳስተዋል “እኛ ሃገራችንን ክብሯን እና የህዝባችንን ክብር ለማስጠበቅ አሁንም እንጥራለን ሲሉ አክለው ገልጸዋል ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የእጅ ለእጅ አዘጋጅ ደግሞ በትላንትናው እለት በፌስቡክ ገጹ ላይ እንደ ገለጸው ከሆነ አቶ አበራ ሲሳይ የተባለው ግለሰብ “የሳኡዲ አረቢያውን መንግስት ተቃውሞ ለማሰማት የወጡት ወያኔዎች ናቸው ሲል የገለጸበትን ሃሳብ ከቁጣ ጋር እንደሆነ ከሃሳቡ ለመረዳት ችለናል ።ሆኖም ግን ይህ ሰላማዊ ሰልፍ የወያኔዎች ብቻ ሃሳብ ሳይሆን የማንኛውም ኢትዮጵያዊ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ህብረተሰብ ጉዳይ እንጂ በቀድሞዎቹ የፖለቲካ ርዝራዥ የሚመራ ሃሳብ እንዳለሆነ አስተናባሪዎቹ ገልጸዋል ።
አያይዘውም ወያኔም ቢሆን ኢትዮጵያዊ እንጂ ከሌላ ሃገር ኢትዮጵያን ለባርነት ሊገዛ የመጣ አይደለም ፣ይበልጡኑ የምንቃረነው ስርአቱን አስተዳደራዊ መዋቅሩን እንጂ ግለሰቦቹን አይደለም እንደዚያማ ከሆነ በበደርግም ሆነ በኢሃፓ ወይንም በሃይለስላሴ እያላችሁ በቀይሽብር ነጭ ሽብር ነዝታችሁ ዜጎችን ያለ ጥቅማዊ ፖለቲካ ያጋደላችሁት ተጠያቂዎች ናችሁ ሲሉም አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል።በአረብ አገራት ላሉ ጉዳዮች መንግስትም ሆነ እኛ በጋራ መስራት የሚጠበቅብን እንጂ ለምን መንግስት ጣልቃ ገባበት ብለን ልንተወው የሚገባን ሃሳብ ሳይሆን የጋራ ጥምረታችን እና አንድነታችንን ልናሳይ የሚገባን ጊዜው አሁን ነው ።
መንግስት በቸልተኝነት ህዝቡን ከእንደዚህ አይነት ሰቆቃና ግፍን መጠበቅ ባይችልም እኛ ደግሞ የውስጥ ገበናችንን ይዘን ዜጎቻችንን ካሉበት ችግር ማውጣት ግዴታችን ነው ከዚያም ተጠያቂ ይሆናል ብለን የምንለውን መንግስት እና የመንግስት አካላት ግዜው ሲደርስ ብንጠይቀው ተገቢነው ሲሉ አክለዋል ።በስተ መጨረሻም ሼም ኦን ዮ ሳኡዲ አረቢያ ነበር ያልነው አሁንስ ሼም ኦን ዮ ኢትዮጵያን ኮሙኒቲ አሶሴሽን በችካጎ ሲሉ ገልጸዋል !

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on November 21, 2013
  • By:
  • Last Modified: November 21, 2013 @ 9:49 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar