www.maledatimes.com ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ስምንት ሺ ሰራተኞችን ገምግሞ ስምንቱን አባረረ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ስምንት ሺ ሰራተኞችን ገምግሞ ስምንቱን አባረረ

By   /   December 4, 2013  /   Comments Off on ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ስምንት ሺ ሰራተኞችን ገምግሞ ስምንቱን አባረረ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 14 Second
 
በፀጋው መላኩ
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የቀድሞው ከፍተኛ ባለሥልጣናቱ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ ባለፉት ወራት በሰራተኞቹ ላይ ግምገማ ያካሄደ ሲሆን በዚህም ከተገመገሙት 8ሺ ሰራተኞች ውስጥ ስምንቱን አባሯል። በዚሁ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት አዲሱ የባለሥልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በከር ሻሌ ስምንት ሺ ሰራተኞች ተገምግመው ስምንቱ ከስራ መባረራቸው ችግሩ በዚያው ልክ ብቻ ነበር አለማለት መሆኑን ገልፀዋል። የፌዴራል የሥነምግብርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በባለሥልጣን መስሪያቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ላይ እርምጃ ከወሰደ በኋላ በሰራተኞች በኩል ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሮ የነበረ መሆኑን ያመለክቱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ከሁሉም በፊት ሰራተኛውን የማረጋጋት ስራ ከተሰራ በኋላ ከሰራተኛው ጋር የንቅናቄ መድረክ ተፈጥሮ በችግሩና በመፍትሄው ዙሪያ ውይይት ሲደረግ የቆየ መሆኑን አመልክተዋል።
ከግምገማው በኋላ በመድረክ ላይ በሰራተኞች ላይ በቀረበ ግምገማ ብቻ ሳይሆን ባጠፉት ጥፋት ተመርምሮ ትክክለኛ መረጃ በተገኘባቸው ሰራተኞች ላይ ብቻ የማባረሩ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል። ስምንቱ ሰራተኞች በአፋጣኝ ከስራ ይሰናበቱ እንጂ ሌሎች በመቶዎች በሚቆሩ ሰራተኞች ላይም ታዩባቸው በተባሉ ግድፈቶች ላይ የማጣራቱ ሥራ እየተካሄደ መሆኑን አቶ በከር አስታውቀዋል። ማጣራቱ ተጠናቆ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙም አስተዳደራዊ ቅጣትም የሚጣልባቸውም ይኖራሉ ብለዋል። ጥፋተኛ ሰራተኛን በሙሉ በማባረር መፍትሄ ማምጣት አይቻልም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ መፍትሄው ሰራተኞቹ ትክክለኛ አመለካከትን እንዲይዙ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው ብለዋል።
ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከሐምሌ ወር 2005 ጀምሮ ባካሄደው ግምገማ በተገኘው የግምገማ ውጤት በመስሪያቤቱ ያለው የኪራይ ሰብሳቢነት ባህሪና አመለካከት ስር የሰደደ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን ችግሩን በአንድ ጀምበር የማይለወጥ መሆኑ ግንዛቤ መውሰዱን አመልክቷል።n
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 4, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 4, 2013 @ 10:29 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar