www.maledatimes.com በመጥረቢያ የግድያ ሙከራ የፈፀመው ግለሰብ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ – ተከሳሹ ተሰውሯል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በመጥረቢያ የግድያ ሙከራ የፈፀመው ግለሰብ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ – ተከሳሹ ተሰውሯል

By   /   December 4, 2013  /   Comments Off on በመጥረቢያ የግድያ ሙከራ የፈፀመው ግለሰብ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ – ተከሳሹ ተሰውሯል

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 20 Second
በአሸናፊ ደምሴ
የስራ ባልደረባውን በቂም በቀል ተነሳስቶ በመጥረቢያ አንገቱን በመምታት የግድያ ወንጀል ሊፈፅም አስቦ ከባድ የግድያ ሙከራ አድርጓል ሲል የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ በከባድ የሰው መግደል ሙከራ ወንጀል ክስ የመሠረተበት ተከሳሽ ዘውድነህ ደግፌ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ፍርድ ቤት በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ህዳር 22 ቀን 2006 ዓ.ም ወሰነ።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት የዐቃቤ ሕግን የክስ መዝገብ ሲመረምር፤ ተከሳሽ ወንጀሉ ከመፈፀሙ በፊት ባሉት ቀናት ውስጥ ከተበዳይ ጋር በጋራ ይሰሩበት በነበረው ሃይገር አውቶብስ ላይ ረዳቱ ሆኖ የሰበሰበውን ገንዘብ አልሰጠኝም በሚል ተጣልተው የነበረ መሆኑን አስታውሷል። በመሆኑም ይህንን ቂም በቀል መነሻ አድርጐ ተከሳሽና ተበዳይ ወይራ ሰፈር ተብሎ በማጠራው አካባቢ በዕረፍት ላይ ሳሉ ተከሳሽ ስለት ያለውን መጥረቢያ ይዞ በመምጣት የተበዳይን አንገት ለመምታት የሰነዘረ ቢሆንም በመሀል የገቡ አገላጋይ እጃቸው ላይ ጉዳት እንዲደርስ ከማድረጉም በተጨማሪ የተበዳይን ጭንቅላት በተደጋጋሚ በመምታት ከፍተኛ ደም እንዲፈሰው በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስበት አድርጓልም ሲል በሐኪም ማስረጃ አረጋግጧል።
ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ ዘውድነህ ደግፌን በሌለበት ጥፋተኛ ያለው ሲሆን፤ በፈፀመው ከባድ የግድያ ሙከራ ወንጀልም እጁ ከተያዘበት ጊዜ አንስቶ በሚታሰብ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ባሳለፍነው ሰኞ የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፏል።¾
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 4, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 4, 2013 @ 10:32 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar