www.maledatimes.com ሼህ አልአሙዲ በኢትዮጵያ ያላቸውን ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ቃል ገቡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሼህ አልአሙዲ በኢትዮጵያ ያላቸውን ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ቃል ገቡ

By   /   December 4, 2013  /   Comments Off on ሼህ አልአሙዲ በኢትዮጵያ ያላቸውን ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ቃል ገቡ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 56 Second
 
በጋዜጣው ሪፖርተር
የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ በኢትዮጵያና በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች እያደረጉ ያለውን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንደሚያሳድጉ አስታወቁ። ሼህ ሙሐመድ ይህን የገለፁት የአፍሪካ ከፍተኛ የገበያ ዕድገት ተብሎ በተጠራውና ታዋቂው ዘ ኢኮኖሚስት መፅሔት በአዲስ አበባ በሸራተን አዲስ ሆቴል ሰሞኑን ባዘጋጀው የቲንክ ታንክ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው። ከትናንት በስቲያ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ አፍሪካ በአሁኑ ወቅት በፍጥነት እያደገች በመሆኑ ዕድገቷ ቀጣይነት እንዲኖረው ኢንቨስትመንት ይበልጥ እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ሼህ ሙሐመድ እርሳቸው በዚህ ረገድ የላቀ ሚና ለመጫወት እንደተዘጋጁ አመልክተዋል።
እንደ ሼህ ሙሐመድ ገለፃ፤ ኢትዮጵያ በምታስመዘግበው የኢኮኖሚ ዕድገት ለአካባቢው ሀገሮች ሞዴል እየሆነች መምጣትዋን ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ የገበያ ትስስር እንዲፈጠር ለኬንያ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ፍላጐት ማሳየትዋ አበረታች ነው ብለዋል።
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ግማሽ የሚሆነው ህዝብ በድህነት አረንቋ ውስጥ እንደሚገኝ በበሽታና በግጭት እንደሚሰቃይ ሳይጠቅሱ አላለፉም።
ከዚህ አኳያ ችግሩን ለመቅረፍ በመንግስትና በግል ዘርፉ መካከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቅሰው የእርሳቸው ኩባንያዎችም በዚህ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚጫወቱ ተናግረዋል። በሳዑዲ ስታር፣ በኤልፎራና በሌሎች ኩባንያዎቻቸው 66 ሺህ ሔክታር መሬት በእርሻ ማልማታቸውን የጠቀሱት ሼህ ሙሐመድ በዚህ አጋጣሚም 148 ሺህ ሰዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ መሠረተ ልማቶችን እንደዘረጉ ተናግረዋል።
በአፍሪካ የሚታየውን የሰለጠነ የሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ እጥረት ለመቅረፍም በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር የሚገኘው ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የጠቀሱት ባለሀብቱ በዚህ ረገድ ዕውቀት ለልማት በግብአትነት እንዲያገለግል እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። አያይዘውም ልማትን በአፍሪካ ለማስፋፋትና ሁሉንም ህዝብ የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እንደ ኢትዮጵያ ያለ ኃላፊነት የሚሰማው መንግስት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
ስብሰባው ለአንድ ቀን ተኩል በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዶ ትናንት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ከበርካታ የዓለም ሀገሮች የመጡ የኢኮኖሚና የቢዝነስ ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል።¾

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 4, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 4, 2013 @ 10:33 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar