www.maledatimes.com የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባልደረባ በፈፀመው ወንጀል ተቀጣ – 89 በርሜል ሬንጅ ተጭበርብሯል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባልደረባ በፈፀመው ወንጀል ተቀጣ – 89 በርሜል ሬንጅ ተጭበርብሯል

By   /   December 4, 2013  /   Comments Off on የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባልደረባ በፈፀመው ወንጀል ተቀጣ – 89 በርሜል ሬንጅ ተጭበርብሯል

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 7 Second
በአሸናፊ ደምሴ
የፌዴራሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ ግምቱ 239 ሺህ ብር የሚያወጣ የመንገድ መስሪያ ሬንጅ አጭበርብሯል ሲል ክስ የመሠረተበት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባልደረባን በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ። ለአራት መንገዶች ፕሮጀክት ይውል የነበረውን 89 በርሜል ሬንጅ በማጭበርበር ጥፋተኛ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ሲል ቅጣቱን ያስተላለፈው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት በትናንትናው ዕለት በ7 ዓመት ፅኑ እስራትና በ5 ሺህ ብር እንዲቀጣ ወስኖበታል።
እንደ ዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ዝርዝር ከሆነ፤ ኤርሚያስ ሙሉጌታ የተባለው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የንብረት አስተዳደር ኦፊሰር ሆኖ በሚሰራበት ወቅት በዋናው ካባ፣ በአጉስታ፣ በገርጂና በመካኒሳ አካባቢዎች የአስፋልት መንገድ ግንባታ ጥቅም ላይ እንዲውል ባለስልጣኑ የገዛውን አይነቱ 85 በመቶ የተሰኘ ሬንጅ አጠቃላይ የገንዘብ ግምቱ 239 ሺ ብር ሆኖ ሳለ 89 በርሜል እንዲጐድል ማድረጉን ባለስልጣኑ ታህሳስ 12 ቀን 2003 ዓ.ም ባካሄደው ማጣራት ማረጋገጡን ይገልፃል።
ይህም በመሆኑ ተከሳሹ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲል የህዝብና የመንግስትን አደራ ወደጐን በመተው ከፍተኛ የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈፅሟል ያለው የፌዴራሉ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ፤ ተከሳሹ ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክዶ በመከራከሩ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎቹን ለፍርድ ቤት አቅርቦ አስረድቷል። ተከሳሹም በሰጠው የመከላከያ ኀሳብ ሬንጁ ቀልጦ ወይም ተሰርቆ ይሆናል የሚል ሲሆን፤ ያቀረበው መከራከሪያ ፍርድ ቤቱን ሊያሳምነው ባለመቻሉ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ተብሏል።
በትናንትናው ዕለትም ጉዳዩን ሲመረምረው የቆየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪከርድ የሌለበት፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪና በአካባቢውም መልካም ስም የነበረው መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት በ7 ዓመት ፅኑ እስራትና በ5 ሺህ ብር እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል።¾

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 4, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 4, 2013 @ 10:36 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar