www.maledatimes.com ፕሮፌሰር ዮሐንስ ክንፉ የአፍሪካ አመራር 2013 ተሸላሚ ሆኑ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ፕሮፌሰር ዮሐንስ ክንፉ የአፍሪካ አመራር 2013 ተሸላሚ ሆኑ

By   /   December 4, 2013  /   Comments Off on ፕሮፌሰር ዮሐንስ ክንፉ የአፍሪካ አመራር 2013 ተሸላሚ ሆኑ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 52 Second
በፀጋው መላኩ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአካውንቲንግ ፕሮፌሰር እና በሚድሮክ ኢትዮጵያ የስልጠና እና የልማት ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ዮሐንስ ክንፉ የአፍሪካን አመራር 2013 ሽልማት አሸነፉ። ፕሮፌሰሩ ሽልማቱን ያገኙት በፕሮፌሰርነት የአገልግሎት ዘመናቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በነበራቸው የስራ ዘመን ቆይታ እውቅና በማግኘት ነው። ሽልማቱ ለፕሮፌሰሩ የተበረከተው በሞሪሽየስ በተካሄደው የአፍሪካ – ህንድ የሽርክና ስብሰባ ላይ (Africa – India Partnership Summit) መሆኑን ከሚድሮክ ኢትዮጵያ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
የአፍሪካ የትምህርት አመራር ሽልማት የሚሰጠው “ወርልድ ኰርፖሬት ሶሻል ሪስፖንስብሊቲ” የተባለ ቀንን መታሰቢያ በማድረግ ነው። ሽልማቱ የሚበረከተው በአመራር ላይ የላቀ ውጤትን ላመጡ ግለሰቦች እንዲሁም አርአያ ለሚሆኑ ተቋማት ጭምር ነው። በዚህ ሽልማት ከሚካተቱት ግለሰቦች መካከል ግለሰባዊ የአመራር ጥበባቸውን፣ ትምህርታዊ ፈጠራቸውንና ቀጣይ መሪዎችን ለማፍራት ለተቋማት ግንባታ ያዋሉ ሰዎች ናቸው። ሚድሮክ ኢትዮጵያም ምሁሩ ለዚህ ሽልማት በመብቃታቸው ደስታውን የገለፀላቸው መሆኑ ተመልክቷል።
ፕሮፌሰር ዮሐንስ አሁን ካገኙት ሽልማት በተጨማሪ ባለፈው የካቲት 2012 ዓ.ም ላይም በዓለም አቀፉ የሰው ኃይል ልማት ኰንግረንስ አማካኝነት በሙምባይ የስልጠና እና ልማት አመራር ሽልማትን አግኝተዋል። ይህ ሽልማት የተበረከተላቸው በስልጠና እና በልማት ፕሮግራም ብቁ የሰው ኃይልን ለማፍራት ባደረጉት ስራ እውቅና በመስጠት ነው። ፕሮፌሰር ዮሐንስ ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ የሂሳብ ባለሙያ አባት በማለት በለንደን ከፍተኛ የአካውንቲንግ ባለሙያነት እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ፕሮፌሰር ዮሐንስ ለ44 ዓመታት ያህል በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ እና በድህረ ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን የአካውንቲንግ ትምህርትን ሲያስተምሩ ቆይተዋል።
ፕሮፌሰሩ ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ አየር መንገድና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሰው ኃይል ልማት ላይ ስልጠና ሲሰጡ ቆይተዋል። በአካውንቲንግና በኦዲቲንግ ዙሪያም መፃህፍቶች በመፃፍ ያበረከቱ ሲሆን፤ በECA እና በUNDP ድርጅቶች ውስጥም በስልጠና አማካሪነት ሰርተዋል። እ.ኤ.አ. ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በሚድሮክ ኢትዮጵያ የስልጠና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው።¾
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 4, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 4, 2013 @ 10:38 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar