www.maledatimes.com ሴት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ እንዲሰሩ የሚያግዝ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሴት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ እንዲሰሩ የሚያግዝ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

By   /   December 4, 2013  /   Comments Off on ሴት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ እንዲሰሩ የሚያግዝ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 20 Second
በመስረም አያሌው
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሞያ ሴቶች ማህበር ከማይክሮ ኒውትሬንት ኢንሼየትቭ ጋር በመተባበር ሴት ጋዜጠኞች በእናቶች ጤና፣ በህጻናት ጤና እና በስርዓተ ምግብ ላይ የሚያተኩር ስራ ለመስራት የሚያስችል የኮሙኒኬሽን ፕሮጀክትን ይፋ አድረገ።
ማህበሩ ትናንት በሂልተን ሆቴል ፕሮጀክቱን ይፋ ያደረገ ሲሆን በማህበሩ እና በማይክሮ ኒውትሬንት ኢንሺየቲቭ መካከልም ስምምነት ተፈርሟል። ይህ የቫይታሚን ኤን ጠቃሜታ በማስተማር እንዲሁም እናቶችና ህፃናት ጤና እና በስነ ምግብ ስርዓት ላይ የሚያተኩረው ፕሮጀክት ለዘጠኝ ወራት ያህል የሚተገበር ሲሆን፤ በዚህ ጊዜ ውስጥም 60 ያህል የማህበሩ አባላት ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በፕሮጀክቱ መክፈቻ ላይ የተገኙት የማህበሩ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ምናለ ገበየሁ እንደገለፁትም ይህ ፕሮጀክት ይፋ በመደረጉ ሴት የመገናኛ ብዙሃን የእናቶች እና ህፃናትን ህይወት ለመታደግ የሚኖራቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ያግዛቸዋል። በተለይ በእናቶች ዘንድ ስለ ቫይታሚን ኤ ያለውን አመለካከት በመቀየር እና ጠቀሜታውን በማስረዳት ረገድ ሴት የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች የበለጠ ቀረቤታ እንዳላቸው የገለፁት ወይዘሮ ምናለ፤ በዚህ ፕሮጀክት ታግዘውም የበርካታ እናቶችና ህፃናትን ህይወት ይታደጋሉ ብለዋል።
በትብብር በመስራት የበርካታ እናቶችና ህፃናትን ህይወት መታደግ ስንችል በመዘናጋት ብዙ ህይወት እንዲያልፍ ፈቅደናል ያሉት የማይክሮ ኒውትሬንት ኢንሺየቲቭ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ሄኖክ ገዛኽኝ በበኩላቸው ይህ ፕሮጀክት ድብቅ ረሀብ የሆነውን የቫይታሚን ኤ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለመቀነስ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል። የተመጣጠነ ምግብ ማጣት ማለት ምግብ ከማጣት ተለይቶ እንደማይታይ የገለፁት አቶ ሄኖክ፤ በዚህም ሳቢያ በርካቶች ህይወታቸውን እየተነጠቁ ነው ብለዋል።
ቫይታሚን ኤን ጨምሮ ስለእናቶች እና ህፃናት አመጋገብ በቂ የሆነ እውቀት ከማጣት የተነሳ ቀደም ሲል በመስኩ ብዙም ስራ ያልተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ሄኖክ፣ ይህን ችግር ለመቅረፍ ሴት የመገናኛ ብዙሃን ባሞያዎችን ስለእናቶችና ህፃናት ጤና እንዲሁም ስለ ስነ ምግብ በቂ እውቀት እንዲኖራቸው ስልጠና በመስጠትና በማብቃት ወደ ስራ ለመግባት መታቀዱን ገልጸዋል። ሴት የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች በቀላሉ ወደ ማህበረሰቡ የመግባት እድሉ ስለሚኖራቸው እነዚህን ባለሞያዎች በመጠቀም የክልል የጤና ዘርፍ ባለሞያዎችን በማነቃቃትም የበለጠ ለውጥ ለማምጣት መታቀዱን አቶ ሄኖክ ገልፀዋል።
ማይክሮ ኒውትሬንት ኢንሺየቲቭ ከማህበሩ ጋር የቅንጅት ስራውን ለጊዜው በቫይታሚን ኤ ላይ የጀመረ ቢሆንም በቀጣይ ግን በአዮዲን፣ በዚንክ  እና ፎሊክ አሲድ ጠቀሜታ እና አጠቃቀም ላይ ለማህበረሰቡ በቂ መረጃ የመስጠት ሰፊ አቅም እንዳለው አቶ ሄኖክ ጨምረው ገልጸዋል።n
(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 9ኛ ዓመት ቁጥር 430 ረቡዕ ህዳር 25/2006 )
ማስታወሻ ፡- ተጨማሪ ዜናዎችና ዘገባዎችን በድረገጹ ያገኛሉ www.sendeknewspaper.com
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 4, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 4, 2013 @ 10:39 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar