www.maledatimes.com መንግስት እና ሰካራሙ ሰውዬ ==== by wosenseged gebrekidan - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መንግስት እና ሰካራሙ ሰውዬ ==== by wosenseged gebrekidan

By   /   December 4, 2013  /   Comments Off on መንግስት እና ሰካራሙ ሰውዬ ==== by wosenseged gebrekidan

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 42 Second

ሰማያዊ ፓርቲ የአጼ ምኒሊክን 100ኛ ዓመት ለማክበር ላቀረበው ጥያቄ የሠላማዊ ሰልፍና ስብበባ ማሳወቂያ (ልብ በሉ ማሳወቂያ) ክፍል ለፓርቲው የላከውን የክልከላ ደብዳቤ ሳነብ አፈርኩ፡፡

ከዚህ ቀደም ሰልፍ በጃንሜዳ ይደረግ ሲል የነበረው ይህ ክፍል፤ አሁን ደግሞ ጃንሜዳ ለጥበቃ አመቺ አይደለም ሲል ግራ ገባኝ፡፡ እናም ይህ የተሳከረ የክልከላ ምላሽ ሰካራሙን ሰውዬ አስታወሰኝ፡፡ ይኼኔ ከዚህ ቀደም “መንግስትና ሰካራሙ ሰውዬ” በሚል ርዕስ የከተብኩትን ፅሁፍ ደግሜ ላስነበብባችሁ ወደድኩ፡፡ እነሆ

==== መንግስት እና ሰካራሙ ሰውዬ ====

መንግስት እና ሰካራሙ ሰውዬ ይመሳሰሉብኝ ይዘዋል፡፡

እንዴት?

መልሱ ቀላል ነው፡፡ “ነገር በምሣሌ” እንዲሉ ከሰካራሙ ሰውዬ ተነሰተን ትረካችንን እንቀጥል፡

ነገረ እንዲህ ነው፡-

ሰውዬው በሃሳብ ይሰክራል፡፡ ሃሳቡን ለመርሳት ይጠጣል፡፡ ይጠጣና ይሰክራል፡፡ አንድ ቀን እንደወትሮው በሃሳብም በመጠጥም ሰክሮ እየተንገዳገደ ወደቤቱ ሲያመራ ያልጠበቀውና ያልገመተው አደጋ ገጠመው፡፡ ለዚያውም ደጃፉ ላይ፡፡ እንዳይታገል በሁለት ነገር ሰክሯል፤ ራሱን መሸከም እንኳ አይችልም፡፡ እንዳይጮህ ድምፅ ከየት ይመጣል!?….ወቸው ጉድ!!

ከዚያች ቀን በኋላ….
ሰውየው ነገር ዓለሙ ተምታታበት፡፡ አንደኛ በሃሳብ ይሰክራል፡፡ ቀጥሎ በመጠጥ፡፡ ቀማምሶ ወደቤቱ ሊያመራ ሲል ግን ያ ያልታሰበ አደጋ ህሊናውን ይፈታተነዋል፤ ያስበረግገዋል፡፡ በመሸ ቁጥር ከፊት ለፊቱ የሚመጣ ሰው ሁሉ፣ ማንም ይሁን ማን አንዳች ነገር ሊያደርገው የመጣ ይመስለዋል፡፡ ይኼኔ ነው ከዚህ ፍርሃቱ የሚያላቅቀው “መላ” የመጣለት፡፡ ከመጠጥ ቤት እንደወጣ በኪሱ ድንጋይ የመያዝ ሃሳብ ተከሰተለት፡፡ እናም ይህንኑ “መፍትሄ” ተግባራዊ ማድረጉን ቀጠለ፡፡

በሌላ ቀን…..
በጣም መሽቷል፡፡ እሱም እንደልማዱ ሰክሯል፡፡ የመጠጥ ቤቱን በራፍ ለቆ እንደወጣ በመዳፉ የሚሞላ ድንጋይ አንስቶ ኪሱ ከተተ፡፡ እየተወላገደ፣ እየተንገዳገደ ጥቂት እንደተጓዘ አንድ አምስት የሚሆኑ ሰዎች በርቀት ወደ እሱ ሲመጡ አየ፡፡ እንደመቆም እየቃጣው ትኩር ብሎ አያቸው፡፡ ነጠላ የለበሱ፣ ጋቢ የደረቡ፤ ፎጣ ጣል ያደረጉ ናቸው፡፡
“እነዚህስ ከለቅሶ ቤት የሚመጡ፤ ወይም ወደ ለቅሶ ቤት የሚሄዱ ሰላማዊ ሰዎች ናቸው” አለው አንደኛው ህሊናው፡፡

“አ!አ!…ማንንም እንዳታምን አለው፡፡” አለው ሌላኛው ህሊናው፡፡

ወደያው በስካር አንደበቱ ጮክ ብሎ “እያንዳንድሽ በአንድ ግቢ!” ድንጋዩን ከኪሱ እያወጣ፡፡

“እኛን ነው?” የሚል ድምፅ ተሰማ ከአምስቱ ሰዎች መሃል፡፡

“አዎ! እያንዳንድሽ በአንድ ግቢ ብያለሁ፤ በአንድ ተራ በሰልፍ ግቢ! አይ በአንድ አልገባም ካልሽ አናት አናትሽን ነው የምተረትርልሽ!…” አለ ድንጋዩን ለማወናጨፍ እየከጀለ፡፡

“ኧረ እኛ ለቀስተኞች ነን፤ መንገደኞች…እንለፍበት” የሚል የሴት ድምፅ በጨለማው ውስጥ ተሰማ፡፡

“የራሽች ጉዳይ! እናንተ ለቀስተኞች ናችሁ ብዬ፤ እኔ ሳለቅስ አልገኝም!…ባንድ ገብተሽ ታልፊ እንደሆን እለፊ፡፡ አሊያ!…” ድንጋዩን እንደመሰንዘር ቃጣው፡፡

ይኼኔ ሰዎቹ በቀስታ ተነጋግረው “በአንድ ገብተው” ከእሱ ተቃራኒ ያለውን የመንገዱን ዳርቻ ይዘው አለፉ፡፡ ከእለታት በኋላ ዞር ብሎ አያቸው፡፡ ሁሉም ነገረ ሠላም ነው፡፡ ሰዎቹም ጉዞአቸውን ቀጥለዋል፤ እየተሳሳቁ፡፡ ሳቃቸው በሩቁ ሲቅጨለጨል ቢሰማውም ቤቱ እስኪደርብ ድረስ “በአንድ ግቢ/ ግባ!” የሚለው ቃል ከአፉ አልተለየውም፡፡ እንደ አባባሉ ቃሉ ወደፊትም የሚለየው አይመስልም፡፡

ልክ እንደዚያው ሁሉ፡-
ይኼ መንግስትም ካራሙ ባህርይ የተጋባበት ይመስላል፡፡

ነገረ ስራው ሁሉ “በአንድ ግባ!!!!”የሆነ ይመስላል፡፡ ስለ ዲሞክራሲ ሲነሳ፤ “የዲሞክራሲ ትክክለኛ ፍቺ እኔጋ እኔ ብቻ ያለው” ይላል፡፡

“እሺ እሱኑ ተግባራዊ አድርገው?” ሲባል ይበረግጋል፡፡ በራሱ ሃሳብ ይናውዛል፡፡ የራሱን ሃሳብ እየጠጣ ይሰክራል፡፡ ከራሱ ጋር እየተጋጨ፣ ከራሱ ጋር እየተላተመ ይጮሃል፡- “በአንድ ግባ” እያለ፡፡

ምክንያቱም ያኔ በርግጓል፡፡ ደሞክራሲ የተለያየ አመለካከት ማስተናገድ ነው ብሎ ያልገመተውን “ውጤት” አግኝቷል፡፡ ስለዚህ “አንድ ብቻ” ማለቱን ተያይዞታል፡፡ “በአንድ ግቡ”ን መዝሙር አድርጎ ተያይዞታል፡፡

በዚህ በዚህ የተነሣ….
መንግስትና ሰካራሙ ሰውዬ ይመሳሰሉብኛል፡፡ አይ እ….ኔ!!!!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 4, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 4, 2013 @ 3:10 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar