www.maledatimes.com ሰበር ዜና – የመስቀል ክብረ በዓል የዓለም ቅርስ ሆነ ( ሔኖክ ያሬድ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሰበር ዜና – የመስቀል ክብረ በዓል የዓለም ቅርስ ሆነ ( ሔኖክ ያሬድ)

By   /   December 4, 2013  /   Comments Off on ሰበር ዜና – የመስቀል ክብረ በዓል የዓለም ቅርስ ሆነ ( ሔኖክ ያሬድ)

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 5 Second

source reporter የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ)

በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ  ባኩ ከተማ ነው፡፡

ስለቅርሱ የመረመረው ኮሚቴ ባቀረበው ውሳኔ ሐሳብ ላይ እንደተመለከተው፣  የመስቀል ክብረ በዓል የኢትዮጵያን ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶችን የያዘ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ መምጣቱና በአገሪቱ ማኅበራዊ አንድነትንና የርስ በርስ ትስስርን፣ ብዝኃነትንም የሚያንፀባርቅ፣ በበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች መካከል ትስስርን የፈጠረ በመሆኑ ዓለም አቀፍ መስፈርቱን አሟልቷል ብሎታል፡፡

የዩኔስኮ ኮሚቴው በረቡዕ ስብሰባ ውሎው  ከመስቀል ሌላ ከተለያዩ አገሮች 13 መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርሶችን በሰው ዘር ቅርስነት መመዝገቡንም በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
መስቀልን ጨምሮ እ.ኤ.አ. በ2013 የተመረጡትን የ14ቱ መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርሶች ገጽታ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችና ፎቶዎችም በዕለቱ በድረ ገጹ ላይ መለቀቃቸው ታውቋል፡፡

በየዓመቱ መስከረም 17 ቀን በመላ አገሪቱ በአደባባይ ደመራ የሚከበረው የመስቀል ክብረ በዓል የመጀመርያው መንፈሳዊ (ኢንታንጅብል) ባህላዊ ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበላት ኢትዮጵያ፣  ዘጠኝ  ግዙፍ (ታንጀብል) ቅርሶች ማስመዝገቧ ይታወቃል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 4, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 4, 2013 @ 10:39 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar