www.maledatimes.com ኢትዮጵያን በሙስና ከሚታወቁ የዓለም አገሮች ተርታ ያሰለፈው ሪፖርት ይፋ ሆነ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢትዮጵያን በሙስና ከሚታወቁ የዓለም አገሮች ተርታ ያሰለፈው ሪፖርት ይፋ ሆነ

By   /   December 4, 2013  /   Comments Off on ኢትዮጵያን በሙስና ከሚታወቁ የዓለም አገሮች ተርታ ያሰለፈው ሪፖርት ይፋ ሆነ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 27 Second

ትናንት ኅዳር 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በመላው ዓለም ይፋ የሆነው የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ተቋም የሙስና አመላካች ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ ከሙስና ጽዱነት ተርታ ውጭ ከሆኑና በሙስና ተግባር በከፍተኛ ደረጃ ከሚፈረጁ አገሮች አንዷ ሆና መገኘቷን ይፋ አደረገ፡፡

ሪፖርቱ በሚከተለው የሙስና መለኪያ ሚዛን መሠረት፣ ከሙስና ጽዱ የሚባሉ አገሮች ከዘጠና እስከ መቶ ነጠብ የሚያገኙት ናቸው፡፡ በአንፃሩ ከፍተኛ ሙስና ተንሰራፍቶባቸዋል፣ የሙስና ጎሬ ሆነዋል ተብለው የሚታሰቡ አገሮች ደግሞ ከመለኪያው ከ50 በመቶ በታች የሚያስመዘግቡት ናቸው፡፡ በመንግሥት ተቋሞች ውስጥ ከፍተኛ ሙስና ተንሰራፍቶባቸዋል ተብለው ከተለዩት ውስጥ ኢትዮጵያ 33 ከመቶ የመለኪያውን ነጥብ በማስመዝገብ ከከፍተኛ ሙስኞች ተርታ እንደምትሰለፍ የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ከ177 አገሮች ውስጥ 111ኛውን ደረጃ መያዟም በሪፖርቱ ይፋ ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ መላው አገሮች ለሙስና ተጋላጭነት ከሚለኩባቸው መመዘኛዎች መካከል፣ የፕሬስ ነፃነት፣ የተጠያቂነትና የሰዎች የመደመጥ መብት፣ የፍትሕ አካላት ከተፅዕኖ ነፃ መሆን፣ የሕግ የበላይነት፣ የሰብዓዊ ልማት መለኪያና ሌሎችም ጠቋሚዎች እንደሚካተቱ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በድረ ገጹ ይፋ አመላክቷል፡፡ 

ኢትዮጵያ በፕሬስ ነፃነት ከ179 አገሮች 127 ደረጃን በመያዝ የፕሬስ ነፃነት ከሌሉባቸው አገሮች ተርታ ትመደባለች፡፡ በፍትሕ አካላት ነፃነትና ከተፅዕኖ ውጭ ካልሆኑ አገሮች መካከል አንዷ ስትሆን ከ142 አገሮች ውስጥም 93ኛ መሆኗ ይፋ የተደረገው ዓምና ነበር፡፡

ተቋሙ 177 አገሮችን በሙስና እንደሚጠረጠሩበት ደረጃቸው በመመዘን ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሐራ በታች ከሚገኙ አገሮች 90 ከመቶው ለሙስና በሚያስጠረጥራቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሆነው አግኝቷቸዋል፡፡ ቦትስዋና ከሰሐራ በታች አገሮች ዝቅተኛ የሙስና ወንጀል የሚፈጸምባት ስትሆን፣ ሶማሊያ ከሁሉም አገሮች በታች በመሆን ሙስና የተንሰራፋባት ተብላለች፡፡ በዓለም ላይ ከ177ቱ ውስጥ 69 ከመቶ አገሮች ከፍተኛ የሙስና መናኸሪዎች መሆናቸውን ሪፖርቱ ያረጋግጣል፡፡

ከሰሐራ በታች የሚገኙትን አገሮች በሙሰኝነት ተፈርጀው የሚመሩት የምሥራቅ አውሮፓና እስያ አገሮች ሲሆኑ፣ 95 ከመቶ በላይ አገሮች ከፍተኛ ሙሰኞች ሆነው ተመዝግበዋል፡፡ 

በዓለም ላይ ከፍተኛ ሙስና ከተንሰራፋባቸው አሥር አገሮች ስድስቱ ከሰሐራ በታች አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡

CORRUPTION MEASUREMENT TOOLS

CORRUPTION PERCEPTIONS INDEX (2013)

 

RANK:
111/177
SCORE:
33/100
  • ETHIOPIA
Flag of Ethiopia

FACTS & FIGURES

* POPULATION (2010):
82.9 MILLION
* GDP (2010):
$29.72 BILLION
* INFANT MORTALITY RATE (PER 1,000 LIVE BIRTHS – 2010):
67.8
* LIFE EXPECTANCY (2009)
58.12 YEARS
* LITERACY RATE (2008)
29.8%

(* World Bank data)

OUR CHAPTER

TRANSPARENCY ETHIOPIA

Phone: +251 1 43 1506
Website: http://transparencyethiopia.org/

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on December 4, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 4, 2013 @ 11:15 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar