ከረጲ የኃይል ማመንጫ ጋር በተያያዘ በሕግ ተጠያቂ የሆነ አካል የለም ተባለ
ከዛሬ ሰባት ወር በፊት ከተመረቀ በኋላ በቀናት ወስጥ ስራ ያቆመው የረጲ ኃይል ማመንጫ 50 ሜጋ ዋት እንዲያመነጭ ታስቦ ቢገነባም ግማሹን ብቻ ማምረት እንዲችል በመዳረጉ ኃላፊነት ወስዶ እስካሁን በሕግ ተጠያቂ የሆነ ድርጅትም ወይም ግለሰብ አለመኖሩ በፓርላማ አባላት ጥያቄ ቀረበበት። በ2ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የኃይል ማመንጫው በተያዘለት ጊዜ ካለመጠናቀቁም በተጨማሪ፤ እንዲያመነጭ ከታሰበው የኃይል መጠን ወደ […]
Read More →አዲስ አበባ 74 ጊዜያዊ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቢያስፈልጋትም እየተገነቡ ያሉት 18 ናቸው
በአዲስ አበባ ከተማ 74 ጊዜያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ እና መለያ ቦታዎች ቢያስፈልጉም ግንባታቸው እየተካሔደ ያለው የ18ቱ ብቻ መሆኑ ታወቀ፡፡ በከተማዋ ደረቅ ቆሻሻ ከምንጩ ሳይለይ ወደ ጊዜያዊ ማቆያና መለያ ቦታዎች መከመሩ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉትን ጥሬ እቃዎች ከማስቀረቱም ባሻገር ከ60 ዓመታት በላይ የከተማዋን ቆሻሻ በመሸከም እያገለገለ ላለው ረጲ መጨናነቅን እየፈጠረ መሆኑ በተደጋጋሚ ይነሳል። በዚህም ባለፈው ዓመት […]
Read More →ለተረጂዎች የተገዛ 928 ኮንቴነር ዘይት ለ10 ወራት በሞጆ ደረቅ ወደብ ይገኛል
• ዘይቱ የአደጋ ሥጋት የተደቀነበት በመሆኑ የጤና ፍተሻ ሊደረግበት ነው ተባለ ለ10 ወራት በሞጆ ደረቅ ወደብ የተቀመጠው የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን 928 ኮንቴነር ዘይት የአደጋ ሥጋት የተደቀነበት በመሆኑ የጤና ፍተሻ ሊደረግበት ነው። ኮሚሽኑ ከውጭ አገራት ያስገባው 928 ኮንቴነር ወይም 24 ሚልዮን 684 ሺሕ 800 ሊትር ዘይት ከሞጆ ደረቅ ወደብ ከወራት በፊት መውጣት የነበረበት […]
Read More →ክልሎች ከአዲስ አበባ ጎዳና በተነሱ ዜጎች ማቋቋም ላይ ውዝግብ ውስጥ ገቡ
የአማራ ክልል የጎዳና አዳሪ ሕፃናትን በማቋቋም ሥም ለረጅም ዓመታት ከኖሩበት ከተማ ለማስወጣት መጣደፍ ተገቢ አይደለም ብሏል በቅርቡ የአዲስ አበባ አስተዳደር በጎዳና የሚኖሩ ዜጎችን በማንሳት አብዛኞቹን ወደ ክልል ለመመለስ ተስማምቻለሁ በሚል አዲስ ፕሮጀክት ተግባራዊ ቢያደርግም ክልሎች ለመቀበል ባለመፍቀዳቸው ውዝግብ ውስጥ እየገቡ ነው። ከወር በፊት ከአዲስ አበባ ጎዳና አዳሪዎችን ማንሳት የተጀመረው በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስተባባሪነትም ጭምር […]
Read More →ሕገ ወጥ ኤጀንሲዎች በርካታ ሴቶችን ለዝሙት አዳሪነት እየተጠቀሙባቸው መሆኑ ተገለጸ
ሕገ ወጥ አሰሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በመርካቶ አካባቢ ምንም ፈቃድ ሳይኖራቸው፣ በርካታ ሴቶችን ወደ ውጭ አገር እንወስዳችኋለን በሚል ሰበብ በአንድ ቤት ውስጥ በማከማቸት ለዝሙት አዳሪነት ጭምር እየተጠቀሙባቸው መሆኑን አዲስ ማለዳ አረጋገጠች። በጉዳዩ ዙሪያ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የአዲስ አበባ አስተዳደር የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አስፋው መብራቴ፣ በመርካቶ አካባቢ እንደዚህ ዓይነት ወንጀሎች እንደሚፈጸሙ መረጃዎች […]
Read More →የፌደራል ዋና ኦዲተር የክልሎች ገቢና ወጪ ኦዲት የማድረግ ሥልጣን የሚሰጥ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ
የፌዴራል ዋና ኦዲተር የክልል መንግሥታት ከሚያገኙት ድጎማ በተጨማሪ በጀትና ገቢያቸው ኦዲት የማድረግ ሥልጣን የሚሰጠው ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለውይይት ሊቀርብ ነው። አሁን እየተሰራበት ያለው የፌደራል ዋና ኦዲተር ማቋቋሚያ አዋጅ 982/2008 ሕገ መንግሥቱን መሰረት ባደረገ መንገድ ማሻሻያ መደረጉን ተከትሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ እየመከረበት ሲሆን ወይይቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የሕዝብ ተወካዮች ምክር […]
Read More →በ3 ቢሊየን ብር የገበያ ማዕከል እገነባለው ያለው ድርጅት ውጥረት ውስጥ ገብቷል
• ድርጅቱ 28 ሚሊዮን ብር ከ3500 ባለአክሲዮች ሰብሰቧል የዛሬ ኹለት ዓመት ገደማ በ3 ቢሊየን ብር የገበያ ማዕከል እገነባለው ብሎ እስካሁን ወደ 28 ሚሊየን ከተለያዩ ባለሀብቶች የሰበሰበው የሕዳሴ አክስዮን ማኅበር ከአዲስ አበባ መስተዳድር ምንም ዓይነት ይሁንታ አለማግኘቱና የግንባታውን ተፈፃሚነቱ አጠራጣሪ ደረጃ መድረሱ ታወቀ። በዚህም የተነሳ ባለአክሲዮኖች ከድርጅቱ ኃላፊዎች ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ ገብተዋል። አዲስ ማለዳ ባደረገችው […]
Read More →የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግማሽ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት ሥራ ላይ አልዋለም
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በየበጀት ርዕሱ በመደበኛ በጀት 10 በመቶ ብቻ በመውሰድ 444 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በሥራ ላይ እንዳላዋለ ታወቀ። የሚንስቴሩ የ2009 የሒሳብ ኦዲት ግኝት በመንግሥት ወጪ ቁጥጥር ጉዳዮች አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ በተገመገመበት ወቅት እንደተገለፀው፣ በሥራ ላይ ያልዋለው በጀት ከአጠቃላይ በጀቱ ጋር ሲነፃፀር 20 በመቶ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በ2009 […]
Read More →አብን የአማራ፣ የጉራጌና የቅማንት ሕዝብ ˝የቁጥር ዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል˝ አለ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በ1999 በተካሔደው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ የአማራ፣ የጉራጌና የቅማንት ሕዝብ ላይ ˝የቁጥር ዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል˝ ሲል መንግሥትን ወቀሰ። በቆጠራው የተሳተፉ ባለሙያዎችና ባለሥልጣናት ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚል አቋም እንዳለውም አሳውቆም፣ በቆጠራው ለተፈጠረው ስህተት መንግሥት ካሳ ሊከፍል ገባል ሲል ጠይቋል። በ1999ኙ ሦስተኛው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ወቅት ከስድስት ሚሊዮን በላይ የአማራ ብሔር ተወላጆች ባለመቆጠር ወይም […]
Read More →የገንዘብ እጥረትያጋጠመው ዳሽን ቢራ 400 ሚልዮን ብር ከንግድ ባንክ ተበደረ
ዳሽን ቢራ አክስዮን ማኅበር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዚህ ቀደም ለወሰዳቸው ቆርኪ ፋብሪካና ብቅል ግብዓቶች ክፍያ ለመፈፀም 400 ሚሊየን ብር ከንግድ ባንክ እንደተበደረ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ገለፁ። በኢትዮጵያ የቢራ ኢንዱስትሪ በአቅም ደረጃ ከሔኒከንና ቢጂአይ ቀጥሎ ሦስተኛን ደረጃ የያዘው ዳሽን ቢራ በአገሪቷ ባለፉት ዓመታት በነበረው አለመረጋጋት ተከትሎ በተከፈተበት ዘመቻ በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው የገበያ ድርሻ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ […]
Read More →