የዓለማየሁ ታደሰ የጥበብ ጉዞ በጨረፍታ
ʻባቢሎን በሳሎንʼ በኢትዮጵያ የቴአትር ኢንዱስትሪ ታሪክ ውጤታማና መድረክ ላይ ብዙ ከቆዩት መካከል ይመደባል። በርግጥ ቴአትር ተመልካች ሆኖ ባቢሎን በሳሎንን ያልተመለከተ ማግኘት ከባድ ነው። የቴአትሩ ሥም በተነሳ ቁጥር አንድ የማይረሳ ተዋናይ ቢኖር ዓለማየሁ ታደሰ ነው። ሐረር ተወልዶ ያደገው ዓለማየሁ ታደሰ ወደ ፊልም ኢንዱስትሪ በጥልቀት ከመግባቱ በፊት ሰዎች የበለጠ የሚያውቁት በቴአትሮች ላይ በሚጫወታቸው ገፀ ባሕሪያት ነበር። ከሌሎች […]
Read More →በአዲስ አበባ 200 ህፃናት በጉዲፈቻ የሚያሳድጓቸውን ወላጆች እየጠበቁ ነው
በከተማዋ ኹለት መቶ የሚሆኑ ወላጅ አልባ ህፃነት በጉዲፈቻ የሚያሳድጋቸውን ቤተሰብ እየተጠባበቁ መሆኑን የከተማዋ ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።የህፃናት ድጋፍ ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር ገነት ጴጥሮስ እንደተናገሩት ቢሮው በዚህ ዓመት ብቻ በጉዲ ፈቻ እንዲያድጉ 94 ወላጅ አልባ ህፃናትን ለተለያዩ ቤተሰቦች ሰትቷል። 96 ህፃናትን ደግሞ በአደራ መልክ ለአደራ ቤተሰብ እንዳስረከቡ ያሳወቁት ዳይሬክተሯ በቅርቡ ወደ አሳዳጊ ወላጆቻቸው የሚሔዱ 50 […]
Read More →ተጨማሪው በጀት ከብድር ፖሊሲው ጋር ይጋጫል ተባለ
በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወስኖ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተላከው የፌደራል መንግስት የ2011 ተጨማሪ በጀት ከኢትዮጵያ የብድር ፖሊሲ ጋር ይጋጫል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተቃውሞ አነሱ። የሚንስትሮች ምክር ቤት የካቲት 23/2011 በነበረው 64 መደበኛ ስብሰባ ለተያዘው በጀት ዓመት የ34 ቢለዮን ብር የሚጠጋ ተጨማሪ በጀት ላይ የይሁንታ ውሳኔ ባማሳለፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቤት […]
Read More →በጌዲኦ የተፈናቃዮች ሰብኣዊ ቀውስ ሕዝቡን አስቆጣ
• ኮሚሽኑ ድጋፍ እንዳደርግ የተጠየኩት መጋቢት 1 ነው ብሏል ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ የተፈናቀሉ የጌዲኦ ተወላጆች ላይ የደረሰው የሰብኣዊ ቀውስ መንግሥት ትኩረት ነፍጎታል በሚል ሕዝቡን አስቆጣ። የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በግጭት ምክንያት በቅርቡ ለተፈናቀሉ 54 ሺሕ በላይ ዜጎች ድጋፍ እንዳደርግ የተጠየኩት መጋቢት 1/2011 ነው ብሏል። ከወራት በፊት በኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂና በደቡብ ጌዲኦ አዋሳኝ […]
Read More →የሞጆ ደረቅ ወደብ በፈታሽ እጥረት ምክንያት ደንበኞቹ እየተጉላሉበት ነው
በሞጆ ወደቅ ወደብ የፈታሾች እጥረት የፈጠረው መጉላላት አስመጪዎችን እያማረረ ነው ሲሉ፣ የወደቡ ደንበኞች ለአዲስ ማለዳ ቅሬታቸውን አሰሙ። ከዚህ ቀደም በደረቅ ወደቡ በቀን እስከ 200 ኮንቴነር ይፈተሽ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ቁጥሩ ከ300 እስከ 400 ኮንቴነር ከፍ ብሏል። ፍተሻ የሚደረግባቸው ኮንቴነሮች ቁጥር ይጨምር እንጂ፣ የእቃዎቹ ብዛት እና የሰው ኃይሉ አለመመጣጠን አስመጪዎችን እንዳስመረረ ነው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ […]
Read More →ኢዴፓ የፓርቲው አርማና ሥም ቅርሶች ሆነው እንዲቀመጡለት ወሰነ
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ከሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ውኅደት ከፈጸመ በኋላ ኢዴፓ የሚለው መጠሪያ፣ የፓርቲው አርማና ሌጋሲዎች ለሌላ ወገን እንዳይተላለፉና ለታሪክ ቋሚ ቅርሶች ሆነው እንዲቀመጡ ወሰነ። ኢዴፓ ኹለተኛ ልዩ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን መጋቢት 1/2011 በራስ ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ከመላው አገሪቱ የተገኙ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በተገኙበት አካሄዷል። በእለቱም የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በአጀንዳነት የተወያዩበት ‹‹ኢዴፓ ከሰማያዊ ፓርቲ፣ […]
Read More →141 የሞት ፍርደኞች ምሕረት እየጠበቁ ነው
• የ141 የሞት ፍርደኞች መረጃ ተደራጅቶ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቀርቧል በኢትዮጵያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙ 141 ታራሚዎች ምሕረት እንዲደረግላቸው ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቤት አሉ። ከሞት ፍርደኞቹ ውስጥ 137ቱ ወንዶች ሲሆኑ፣ ቀሪ አራቱ ሴቶች ናቸው። አዲስ ማለዳ መረጃ ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው የሞት ፍርዱ ምሕረት ይደረግላቸው ዘንድ የጠየቁት 141 ፍርደኞች መረጃ […]
Read More →የቡራዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ቢዘገይም የበጀቱ ግማሽ ተከፍሏል
• በከተማዋ የነበረው አለመረጋጋት ግንባታው እንዲዘገይ አድርጓል ተብሏል ኅዳር 2011 መጠናቀቅ የነበረበት የቡራዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የመጀመሪያውን ዙር ግንባታን ለማከናወን የሚያስፈልገው 700 ሚሊዮን ብር ሙሉ ወጪ ቢከፈልም የተጠናቀቀው ግንባታ 45 በመቶ ብቻ መሆኑ ታወቀ። የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ግንባታ በኹለት ምዕራፎች ይከናወናል በሚል በመንግሥት ከአንድ ነጥብ አራት እስከ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር የተመደበለት ነበር፡፡ ልዩ […]
Read More →ዕጣ የወጣባቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች የጋዜጣ ሕትመት ተቋረጠ
ባለፈው ረቡዕ የካቲት 27/2011 እጣ የወጣባቸው ከ52 ሺሕ የሚጠጉ የ20/80 እና 40/60 መኖሪያ ቤቶች ዝርዝር በጋዜጣ እንዳይታተም ታገደ። ለወትሮው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሲተላለፉ የእድለኞችን ዝርዝር ይዞ የሚጣውና በአዲስ አበባ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ስር የሚታተመው አዲሰ ልሳን ጋዜጣ እንደሆነ ይታወቃል። ጋዜጣው የባለፈውን ሳምንት የኮንዶሚኒየም እጣ እድለኞች ዝርዝርም በማግሥቱ ሐሙስ የካቲት 28 አትሞ እንዲያወጣ ረቡዕ አመሻሽ የዕድለኞቹ […]
Read More →ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንትና የቦርድ አባል ውስጥ ግማሾቹ ሴቶች እንዲሆኑ ታዘዘ
በዩኒቨርሲቲ የፕሬዘዳንትነትና የቦርድ አባልነት ስብጥር ውስጥ ግማሾቹ ሴቶች እንዲሆኑ ለዩኒቨርሲቲዎች መመሪያ መስጠቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ። ሚንስትሯ ሒሩት ወልደማሪያም (ፕሮፌሰር) ለአዲስ ማለዳ ልዩ እትም መጽሔት እንግዳ ሆነው በቀረቡበት ቃለ ምልልስ እንዳሉት ለሚንስቴሩ ተጠሪ በሆኑት 45 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚገኘው ቦርድ እንዲሻሻል ተደርጓል። በዚህም በሁሉም የዩኒቨርሲቲ ቦርዶች ውስጥ ሃምሳ በመቶዎቹ ሴቶች እንዲሆኑ መደረጉን ሚንስትሯ ገልፀዋል። […]
Read More →