በአዲስ አበባ ጎዳና ተዳዳሪ በመምስል ልዩ ልዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ 1 ሺ የሚጠጉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
#AddisAbaba ፖሊስ የምርመራ ስራ እየሰራ ይገኛል። ተጠርጣሪዎቹ ከህዝብ በደረሰ መረጃ መነሻ በማድረግ በ7 ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 20 ቦታዎች ላይ ግንቦት 22 ቀን 2013 በተከናወነ የኦፕሬሽ ስራ የተያዙ ናቸው። አጠቃላይ ቋሚ አድራሻ የሌላቸውና በዋና ዋና አደባባዮች እና በምሽት በሰዋራ ቦታዎች የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ 999 ግለሰቦች ናቸው የተያዙት። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ፦ – አብዛኞቹ ማስቲሽና […]
Read More →ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሀገራችን ድረ-ገጾች ላይ የመረጃ መበርበር ሙከራ ሲያደርግ ቆይቷል
#ጥንቃቄ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሀገራችን ድረ-ገጾች ላይ የመረጃ መበርበር ሙከራ ሲያደርግ ቆይቷል የተባለ ቡድን አሁን ላይ 37 ሺህ በሚደርሱ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ። ይህን ያሳወቀው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ነው። ተቋሙ ባወጣው መረጃ “ሳይበር ሆርስ ግሩፕ” የተሰኘው የመረጃ ሰርሳሪ ቡድን አዲስ የኮምፒውተር […]
Read More →የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕወሃትን ህጋዊ ሰውነት መሰረዙን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ላይ ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ የሕወሃትን ህጋዊ ሰውነት መሰረዙን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህግ ከተቋቋመባቸው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ፥ ቁጥጥር እና ክትትል ነው። በመሆኑም በምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት ፓርቲዎች የተለያዩ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም መሰረት ቀደም ብሎ መስፈርት አሟልተው […]
Read More →ዩቲዩብ (YouTube) ብዙ ቪዲዮዎች ላይ ማስታወቂያዎች ማሳየት እንደሚጀምር ገልጿል
ዩቲዩብ (YouTube) ብዙ ቪዲዮዎች ላይ ማስታወቂያዎች ማሳየት እንደሚጀምር እና ለሁሉም ማስታወቂያ ግን ክፍያ ላይፈጽም እንደሚችል አስታውቋል። ኩባንያው በአሁኑ ወቅት የማስታወቂያ ገቢውን በሽርክና መርሃ ግብሩ ላይ ከተመዘገቡ ቪዲዮ ሠሪዎች ጋር ይጋራል። ከዚህ በኋላ ግን ዩቲዩብ የሽርክና መርሃ ግብሩ አካል ያልሆኑ በአንዳንድ ቪዲዮዎች ላይም ማስታወቂያዎችን ማስገባት እጀምራለሁ ብሏል። በአገልግሎት ውሉ ላይ በተደረጉ ለውጦች ምክንያት ዩቲዩብ ከማስታወቂያዎቹ የሚገኘውን […]
Read More →ከድባጤ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ዕርዳታ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን ገለጹ!
በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በምግብ፣ በአልባሳት እና በመጠለያ እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ለአብመድ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ የተጠየቀው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለተፈናቃዮች አስቸኳይ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ታረቀኝ ተሲሳ ከኅዳር 5 ጀምሮ ከተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በድባጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ 1 […]
Read More →የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ሱዳን ድርድሩን አልማማበትም ማለቷ ተገልጿል !!
ታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በኢትዮጵያ፣ በግብጽ እና በሱዳን በውሃ ሚኒስቴሮች ደረጃ ሊካሄድ ለዛሬ ቀጠሮ በተያዘለት ድርድር ላይ ሱዳን እንደማትገኝ በደብዳቤ አስታውቃለች። ለዚህም ምክንያቷ የአፍሪካ ህብረት ባለሞያዎች የተሰጣቸው የአደራዳሪነት ሚና ዝቅተኛ ነው የሚል እንደሆነ የሱዳን ዜና አገልግሎት ሱና ዘግቧል፡፡ የሱዳን ወገን የድርድሩ አካሄድ ካልተለወጠ በድርድሩ አልሳተፍም የሚል አቋም በባለፈው ድርድር ወቅት ማንጸባረቋን የኢትዮጵያ የውሃ መስኖና ኢነርጂ […]
Read More →መንግስት ከህወሓት ወንጀለኞች ጋር ድርድር አይቀመጥም – አቶ ደመቀ መኮንን
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ከህወሓት ወንጀለኞች ጋር ለድርድር እንደማይቀመጥ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ። አቶ ደመቀ መኮንን ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አን ሊንዴ ጋር በስልክ ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ በውይይታቸው በዋናነት መንግስት በትግራይ ክልል እየወሰደ ባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ትኩረት አድርገው መምከራቸውን ከውጭ […]
Read More →በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ ተሰጠ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለሚድያ አካላት ማብራሪያ ሰጥተዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ በትግራይ እየተካሄደ ስላለው የሕግ ማስከበር ሥራና አስተዳደሩ በትግራይ ክልል ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራቸውን ስራዎች በተመለከተ አብራርተዋል፡፡ በጊዜያዊ አስተዳደሩም […]
Read More →በመዲናዋ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ 19 ቦንብና ሌሎች በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ
በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የተከማቹ 19 ቦንቦችና እና ሌሎች በርካታ የጦር መሳሪያዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የጦር መሳሪያ አከማችተው በሚገኙ ተቋማት ላይ የሚደረጉ ፍተሻዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ኮሚሽኑ ገልጿል። የጥፋት ሃይሎች ለመዲናዋ የደገሱላትን ሽብርና እልቂት ለመቀልበስ የሚከናወነው ጠንካራ ህግን የማስከበር ተግባር በህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት መረጃ ሰጪነት እየታገዘ […]
Read More →በአማራ ክልል ለቤተ እምነቶች ጥበቃ ሊደረግ እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ
በአማራ ክልል ለቤተ እምነቶች ጥበቃ ሊደረግ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከጸጥታ አካላት ባገኘው መረጃ መሰረት፣ የኦርቶዶክስ አልባሳት ለብሶ መስጅድ፣ እንዲሁም የሙስሊም አልባሳት ለብሶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት ለመፈፀም ተልዕኮ የያዙ አካላት ወደ ክልሉ ገብተዋል። በመሆኑም በክልሉ ያሉ ሁሉም አማኞች ቤተ እምነታቸውን በመጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
Read More →