www.maledatimes.com 2013 - MALEDA TIMES - Page 17
Loading...
You are here:  Home  >  2013  -  Page 17
Latest

አይ አበሻ! አበሻና ልመና፦ አንድ (መስፍን ወልደ-ማርያም)

By   /  December 16, 2013  /  AFRICA  /  Comments Off on አይ አበሻ! አበሻና ልመና፦ አንድ (መስፍን ወልደ-ማርያም)

ኅዳር 2006 በዓለም ሕዝቦች መሀከል ውድድር ቢደረግ ያለጥርጥር አበሻ አንደኛ ከሚወጣባቸው ነገሮች አንዱ ልመና ሳይሆን አይቀርም፤ ለአበሻ፣ ልመና የኑሮ ዘዴ ነው፤ እንዲያውም ከልመና ውጭ የሆነ ኢትዮጵያዊ ኑሮ የለም ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ ስለዚህም ልመና ባህላዊ ጥበብ ሆኖአል፤ አንዳንድ አላዋቂዎች፣ አንዳንድ አዋቂዎችም አንዳንዴ እየተሳሳቱ ልመናን እንደነውር ይገልጹታል፤ ልመና ነውር አይደለም፤ ለጨዋ ልጆችማ አንዳንድ አጥንትን የሚያበላሽ ሥራ ከመሥራት ለምኖ […]

Read More →
Latest

ያ’ገሬና የኔ – አትክልት አሰፋ (ጋዜጠኛ) – ከቫንኩቨር

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia, POEMS  /  Comments Off on ያ’ገሬና የኔ – አትክልት አሰፋ (ጋዜጠኛ) – ከቫንኩቨር

እናቴና አገሬ ሙግት ገጠሙና፣ ሚስቴና እናት አለም ተወዳደሩና፣ ልጄ እና እማምዬ ፉክክር ገቡና፣ አንዱን ምረጥ ብለው ድርቅ ሲሉብኝ፤ እናቴም ውዴ ናት፣ ሚስቴም የኔ ፍቅር፤ ልጄም ንጉሴ ነው፤ የሚጣፍጥ ከማር፤ የግሌ የራሴ የማ’ለውጣቸው፣ በሰላሳ ዲናር የማልቀይራቸው፤ እናት፣ ሚስት፣ ልጄ፤ ሁሉም የኔ ናቸው። እኔ ግን ያገሬ፤ እኔስ የ ‘ማምዬ… የግል ንብረት ነኝ ብዬ መለስኳቸው። ዲሴምበር 15/2013- ቫንኩቨር […]

Read More →
Latest

የሰአሊው ጥበብ

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on የሰአሊው ጥበብ

አቤት!! ጊዜው እንዴት ይነጉዳል? 10 ዓመት!! ድፍን 10 ዓመት ሆነ፡- ከተያየን፡፡ ይገርማል!! ከ10 አመት በፊት ነበር እንደዘበት ጓደኝነታችን የተጀመረው፡፡ በሥራ አጋጣሚ ነው ለትውውቅ የበቃነው፡፡ እሱ የሥዕል ኢግዚቢሽን አዘጋጅቶ ነበር፡- በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ አዳራሽ፡፡ ያኔ በረቂቅ የሥዕል ስራዎቹ የተነሳ እንደዘበት የጀመርነው ውይይት ነው ወደጥብቅ ግንኙነት የተቀየረው፡፡ እርግጥ ነው ከዚያ በፊትም ትውውቅ ነበረን፡፡ በሰዓሊነት ሙያው ቦሌ ማተሚያ […]

Read More →
Latest

የፌስቡክ ተቃርኖዎች (ጽዮን ግርማ ከአዲስ አበባ)

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on የፌስቡክ ተቃርኖዎች (ጽዮን ግርማ ከአዲስ አበባ)

tsiongir@gmail.com በዓለም ዙሪያ አንድ ቢልዮን ያህል ተጠቃሚዎችን አፍርቷል፡፡ በተጠቃሚዎቹ ብዛት ከማኅበራዊ ድር ዐምባዎች ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል፡፡ በቢልዮን ከሚቆጠሩት የፌስቡክ ተስተናጋጆች መካከል ከግማሽ ሚልዮን በላይ (867,000) የሚኾኑት ከኢትዮጵያ የተመዘገቡ ናቸው፡፡ ይህ አኀዝ ከአጠቃላይ የአገሪቱ ሕዝብ ብዛት 0.99 በመቶውን ብቻ እንደሚይዝ በየጊዜው መጠናዊ መረጃ የሚሰጠው የሶሻል ቤከርስ (Social Bakers) ድረ ገጽ ያስረዳል፡፡ በዚህ አኀዝ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ […]

Read More →
Latest

ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ስምንት ሺ ሰራተኞችን ገምግሞ ስምንቱን አባረረ

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ስምንት ሺ ሰራተኞችን ገምግሞ ስምንቱን አባረረ

በፀጋው መላኩ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የቀድሞው ከፍተኛ ባለሥልጣናቱ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙና ኮሚሽን ዐቃቤ ሕግ ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ ባለፉት ወራት በሰራተኞቹ ላይ ግምገማ ያካሄደ ሲሆን በዚህም ከተገመገሙት 8ሺ ሰራተኞች ውስጥ ስምንቱን አባሯል። በዚሁ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት አዲሱ የባለሥልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በከር ሻሌ ስምንት ሺ ሰራተኞች ተገምግመው ስምንቱ ከስራ […]

Read More →
Latest

በአዲስ አበባ በሥጋ ውጤቶች ላይ ሊጣል የታሰበው ግብር እያወዛገበ ነው · የሥጋን ዋጋ እንዳያንረው አስግቷል

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on በአዲስ አበባ በሥጋ ውጤቶች ላይ ሊጣል የታሰበው ግብር እያወዛገበ ነው · የሥጋን ዋጋ እንዳያንረው አስግቷል

የሰንደቅ ዜናዎች (ህዳር 25/2006) በፀጋው መላኩ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከስጋ ነጋዴዎች ግብርን ለመሰብሰብ ቀደም ሲል ሲጠቀምት የነበረውን የቁርጥ ግብር አሰራር በመቀየር አንድ ነጋዴ በሬ በቄራ ካሳረዱ በኋላ ተጣርቶ በሚሸጠው የሥጋ መጠን ግብር ለመጣል እንቅስቃሴን በመጀመሩ አሰራሩ ውዝግብን አስነስቷል። ባለስልጣን መስሪያቤቱ ግብሩን ለመጣል አንድ በሬ ከእርድ በኋላ የሚወገደው ተወግዶ ምን ያህል ኪሎ የተጣራ ክብደት ይኖረዋል የሚለውን […]

Read More →
Latest

ይድረስ ለምሁሩ ወዳጄ (በድጋሚ የቀረበ)

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on ይድረስ ለምሁሩ ወዳጄ (በድጋሚ የቀረበ)

    ይድረስ የኑሮ ውድነት ላነተበህ፣ ኢትዮጽያዊ ጨዋነት ከሰውነት ተራ ላወጣህ ምሁሩ ወዳጄ!… ያቺ ከልደታባዕታ የማታደርስህን ገቢ ለመሸሸህ ከግማሽ እድሜህ በላይ ቆርሰህ እስከፒ.ኤ.ቺ.ዲ ዲግሪ ድረስ ተማርክ፤ለፋህ፣ ደከምክ፡፡ እነሆ ተምረህ ስታበቃ የደመወዝህ ስኬል እንደአሮጌ የባቡር ፉርጎ እየተጎተተ 6 ሺ ብር ላይቆመ፡፡ ከዚህ ላይ መንግስት 35 በመቶ ታክስ ሲያነሳለት፣የጡረታ ፣የአባይ ግድብ መዋጮ ሲቀነጫጨብለት..ከዚያም ከዚህም የቃረምካቸው የቅሌት መዝገቦች(ብድሮች) ሲወራረዱ…ጠላትህ ክው ይበል ክው የሚያደርግፍራንክ ይዘህ ወደሚስትና ልጆችህ ትነጉዳለህ፡፡ አማኝ ነህና ለዚህም ተመስገን ትላለህ…“ተመስገን፤ ይህንንምአታሳጣኝ!..ይህንንም ያጡ ብዙዎች አሉና አንተ በቸርነትህ ጎብኛቸው… አስባቸው!” እያልክ ነግቶ በመሸ ቁጥርለብቻህ ታጉተመትማለህ፡፡.. ጮሌዎቹ ባልንጀሮችህ “መንገዱን እወቅበት!” እያሉ ጠዋት ማታ ይጎተጉቱሃል፡፡ እነሱን እያቸው!…መንግስትንደመወዝ ጨምርልኝ ከማለት ይልቅ “ይህ ልማታዊ መንግስታችን ባዶ ካዝና ነው የተረከበው፤ የገቢያችን ማነስድህነታችን የፈጠረው ችግር ነው!…ችግሩ በልማታዊ መንግስታችን ጥረት ይፈታል!…”በማለት በየመለኪያቤቶች ጭምር ዲስኩራቸውን እየነፉ፤ ግን ቀብረር…ሞልቀቅ ያለ ኑሮአቸውን ያጣጥማሉ፡፡ ከየት አምጥተውይመስልሃል ወዳጄ?!…ዕድሜ ለልማታዊ መንግስታችን!.. የአንተን ኪስ በጥሩ ደመወዝ መሙላት ቢያቅተውም፤የሁነኛ ወጃጆቹን ቀዳዳ በርሜል ለመሙላት ግን ላቡን መዝራት አልተሳነውም፡፡ ለአንተና ለመሰሎችህ ግንበየቴሌቪዥኑ መስኮት፣ በየስብሰባ አዳራሹ ቋቅ እስኪልህ ድረስ “ዋንኛው ጠላታችን ኪራይ ሰብሳቢነት ነው!”ሲል ዲስኩሩን ይግታቹሃል፡፡ አንተም ምስኪኑ…አንዳንዴ የሰማህው ሁሉ እውነት እየመሰለህ ይህንኑበየሄድክበት እንደበቀቀን ስትደግም ትውላለህ፤ “ዋንኛው ጠላታችን ኪራይ ሰብሳቢነት ነው!…ኪራይ ሰብሳቢነትየሥርዓቱ አደጋ ነውና በተባበረ ክንድ እናጥፋው!…..ተረረረም..ተረረም…” ያ አብሮ አደግህ ዶ/ር እንቶኔ 6 ሺ ብር የማትሞላ ወርሃዊ ደመወዝ ይዞ ግራውንድ ፕላስ ዋን ቤት ሰርቷል፡፡ልጆቹን ለንደን ፣ አሜሪካ ልኮ ዶላር እየመነዘረ ያስተምራል፡፡ ያኛው (ስሙን ቄስ ይጥራውና!)… ከካድሬውበላይ ካድሬ ነኝ የሚለው….፤ መሽቶ በነጋ ቁጥር በፓርቲው እየማለና እየተገዘተ ራሱን ወደንዑስ ከበርቴ መደብከፍ ካደረገ ሰንብቷል፡፡ አንተ ግን በፈሪሃ እግዚአብሄር ተሞልተህ… ባዶ ኪስህን…ባዶ ሆድህን…ባዶ ቤትህንይዘህ ትናውዛለህ፡፡ ለልጆችህ ወርሃዊ ክፍያ አጥተህ ስንቱን ስትቧጥጥ እንደምትኖር የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻነው፡፡…ደግሞ ይህቺ ባዶነትህ ውስጥ የተሰካች ኩራትህ አናትህ ላይ ወጥታ ስትጨፍር ወግ ነውና ኮራ..ጀነንትላለህ፡፡ ሰው እናድርግህ! ያሉህን “ልማታዊዋን” እየሸሸህ…እየሸሸህ፤ እነሆ በማትሸሸው ድህነት ማጥ ውስጥቦክተህ….ሐሩር እንደመታው ቄጤማ ከነቤተሰብህ ጠውልገህ ትኖራለህ፡፡ ደሃ ነህ!…ገና ጠግበህ መብላትየምትመኝ ነህ!…እናም በስርቆት ከደረጁት ጋር ተሰልፈህ ዛሬም ባልበላ አንጀትህ “ዋንኛው ጠላታችን ኪራይሰብሳቢነት ነው!” እያልክ ትዘምራለህ፡፡ ሌላው መንገድ ያንተ አይደለምና ምን ምርጫ አለህ? ንጹህነትህንየሚጠየፉ ሌቦችን ከማጀብ ውጪስ ምን ተስፋ አለህ?…ግን ይህ ጽዱ ኢትዮጽያዊ ንጽህናህ!…ደግነትህ!…ጨዋነትህ! የት ድረስ ያዘልቅህ ይሆን?…እንጃ?!….አንድዬ ይታደግህ አቦ!… ፍ.አ (ነሐሴ 2005)

Read More →
Latest

ስብሰባው (በድጋሚ የቀረበ)

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on ስብሰባው (በድጋሚ የቀረበ)

ሞልቶ ከተረፉን ስብሰባዎች መካከል በአንዱ ውስጥ ነበርኩ፡፡ ስብሰባው ስለመንግስት የዕድገትናትራንስፎርሜሸን ዕቅድ እና የክልሎች እንቅስቃሴ የሚወራበት ነበር፡፡ያው እንደደንቡ የተመረጡት ሹም ከአንድሰዓት በላይ ጊዜ ወስደው ጥናት ያሉትን አቀረቡ፡፡አወያዩ አቅራቢውን የጎንዮሽ በማየት እያደነቁ “ዌል! እጅግበሳል ትንታኔ የተንጸባረቀበት ጹሑፍ ነው፡፡እሳቸው ያሉትን መልሼ አልደግመውም፡፡ግን መታለፍ የሌለባቸውዋና ዋና ነጥቦችን ላንሳ” አሉንና ንግግራቸውን እየጎተቱ ልክ እንደበቀቀን ሰውየው ያሉትን ምንም ሳያስቀሩመልሰው ደገሙልን፡፡ደግመውልን ሲያበቁ መድረኩ ለአስተያየትና ጥያቄ ክፍት መሆኑን አበሰሩ፡፡ጥቂት እጆችአየር ላይ ታዩ፡፡ሰብሳቢው ብርጭቆ የሚያህል መነጽራቸውን ግራና ቀን ሲያንከራትቱ ቆዩና “አንተ በቀኝ በኩልያለኸው..አዎ!..ቀይ ከረባት ያሰርከው ” ብለው መነጋገሪውን አሻገሩ፡፡ተመራጩ ተናጋሪ ቀጠለ፡፡ “በቅድሚያ ክቡር አቶ እገሌ ላቀረቡልን ፕረዘንቴሽን ያለኝን ልባዊ አድናቆት ልገልጽ እወዳለሁ፡፡በእውነቱፕረዘንቴሽኑ በአሁኑ ወቅት በተለይ በክልሎች ያለውን ችግር አንድ በአንድ ነቅሶ ያሳየ በመሆኑ በዚህ ረገድየምጨምረው ብዙም ነገር አይኖረኝም፡፡ክቡር አቶ እገሌ እንዳሉት ለዚህች ሳታጣ ላጣች አገራችን መደህየትተጠያቂዎቹ ጸረ ልማት ኃይሎች መሆናቸውን የተናገሩት በትልቁ ሊሰመርበት ይገባል…. ” ሌላኛው ቀጠለ፡፡“እኔም እንደወንድሜ ክቡር አቶ እገሌ ላቀረቡልን ጥናታዊ ጹሑፍ ያለኝን ክብር ሳልገልጽአላልፍም፡፡ጹሑፋ ብዙ ያላወኩትን ነገር ያሳወቀኝ ነው፡፡ከዚህ በኃላ የማቀርበው አንድ ሁለት ጥያቄዎችይኖሩኛል፡፡ይኸውም የአገራችንን ዕድገትና ልማት የሚያደናቅፉ ሓይሎች እስከመቼ ነው የምንታገሳቸው?ይህስብሰባ አንድ ቁርጥ ያለ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ለመጠየቅ ነው፡፡አመሰግናለሁ፡፡” ሌላኛውም ማይክሮፎኑን አስጠግተው ለመናገር ጉሮሮአቸውን ጠራረጉ፡፡“እ..እ..እ..እ….ክቡር ሰብሳቢለሰጡኝ ዕድል አመሰግናለሁ፡፡በእውነቱ በእንዲህ ዓይነት ትልቅ አገራዊ ፋይዳ ባለው ስብሰባ ላይ በመገኘቴየተሰማኝን ደስታ በዚህ አጋጣሚ ልገልጽ እወዳለሁ፡፡ጥናት ያቀረቡትም እጅግ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ ጥናቱ መሬትላይ ያሉ ችግሮቻችን በሚገባ የዳሰሰ ነው፡፡አገራችን ለዘመናት የተጎዳችው እንዲህ ዓይነት ችግሮቻችን በሚገባየሚዳስሱ ጥናቶች ባለመኖራቸው ነው፡፡እናም ስብሰባውን አዘጋጆች የምጠይቀው ይህ ጠቃሚ ጥናትለሚመለከታቸው ስቴክሆልደሮች ሁሉ ተባዝቶ እንዲሰጥ መደረግ እንዳለበት ለማሳሰብ ነው፡፡አመሰግናለሁ፡፡” ሌሎችም ሶስት ተናጋሪዎች በተመሳሳይ መንገድ አድናቆታቸውን ገለጹ፡፡የስብሰባው ተካፋዮችም ንግግሮችን ሁሉሳይታክቱ በጭብጨባ ከማድመቅ አልቦዘኑም፡፡ እነሆ የሻይ ዕረፍት ሆነ፡፡ ምሳ ሰዓትም ደርሶ መብልና መጠጡተወራረደ፡፡ በስብሰባው ማሳረጊያ ላይ የአቋም መግለጫ ወጣ፡፡ተጨበጨበ፡፡የውሎ አበል ለተሰብሳቢውበነፍስወከፍ ታድሎ የዕለቱ  መርሃግብር ተጠናቀቀ፡፡ ምሽትም ላይ ኢቴቪ በዕድገትና በትራንስፎርሜሽኑ ዕቅድና ትግበራ ላይ ያተኮረ የአንድ ቀን አውደጥናት በሸራተንሆቴል ሲካሄድ መዋሉን አበሰረ፡፡ “በስብሰባው ላይ የተገኙት ክቡር አቶ እገሌ ባቀረቡት ጥናታዊ ጹሑፍየአገሪትዋን ልማትና ዕድገት በአስተማማኝ መልኩ ለማስቀጠል ጸረ ሰላም ኃይሎችን መታገል እንደሚገባበአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ተሰብሳቢዎችም ዕቅዱን ለማሳካት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ቃል መግባታቸውየሪፖርተራችን ዘገባ ያሳያል” አለ፡፡ እነሆ ወራት ተቆጠሩ፡፡ክቡር ሚኒስትሩም የመ/ቤታቸውን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማሲያቀርቡ ያን ዓውደጥናት አልዘነጉትም፡፡ ከተለያዩ ክልሎችና ሴክተር መ/ቤቶች ለተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮችየአንድ ቀን አውደጥናት መሰጠቱን፤ በዕለቱም በቀረበው ጥናት መሰረት በልማት ረገድ ክልሎች ያለባቸውችግሮች መቀረፋቸውን ለፓርላማው ተናገሩ፡፡ዓውደጥናቱን ጨምሮ ለዚህ ዓመት ከተያዘው በጀት 30 ሚሊየንብር ጥቅም ላይ መዋሉንና የበጀት አፈጻጸማቸው ከዓመት ዓመት መሻሻል እያሳየ መምጣቱን አከሉ፡፡የፓርላማአባላቱም ስለሪፖርታቸው አጨበጨቡ፣አደነቁ፡፡ኢቴቪም የሚኒስቴሩ ሥራ አበረታች መሆኑን ፓርላማውመናገሩን ምሽት ላይ ነገረን፤እኛም የተደነቀውን፣የተጨበጨበለትን….አይተን፣ሰምተን እንደቅዱስ ቃሉ ይሁንብለን ዝም አልን፡፡

Read More →
Latest

Israeli president condemns rejection of Ethiopian-born MP as blood donor

By   /  December 16, 2013  /  AFRICA, Ethiopia  /  Comments Off on Israeli president condemns rejection of Ethiopian-born MP as blood donor

Parliamentary session is called after ‘special’ blood of Ethiopian-born MP is rejected by emergency services Harriet Sherwood theguardian.com,  Shimon Peres says all citizens are equal and should be able to donate blood. Photograph: Hector Guerrero/AFP/Getty Images Israel‘s president, Shimon Peres, has criticised the refusal of the country’s emergency medical services to accept a blood donation from an […]

Read More →
Latest

ብዙም ያልተነገረ ታሪክ ===== ወሰን ሰገድ ገብረኪዳን

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on ብዙም ያልተነገረ ታሪክ ===== ወሰን ሰገድ ገብረኪዳን

ይህ የወርሃ ታህሣሥ ብዙም ያልተነገረ ትውስታ ነው፡፡ በዘመናዊው ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሁሌም የሚታወስ ወር ነው፡- ታህሣሥ፡፡ “የታህሣስ ግርግር” ይሰኛል፡፡ መንግስቱ ንዋይና ግርማሜ ንዋይ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱበትና በአፄው ሥርዓት ላይ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉት በታህሣሥ ወር የመጀመሪያ ሳምንት፡- ከታህሣስ 5- 7 ቀን 1953 ነው መፈንቅለ መንግስት ሙከራው የተቃጣው፡፡ ከዛሬ 53 ዓመት በፊት መሆኑ ነው፡- የእነመንግስቱ ንዋይ […]

Read More →
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar