በብዕር ስም የሚንቀሳቀሱ አክቲቪስቶቹን ማን ነዉ እያሲያዛቸዉ ያለዉ? – ሸንቁጥ አየለ
ሰሞኑን የአማራ አክቲቪስቶች በወያኔ መጠለፋቸዉን አንዳንድ ወንድሞች እዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለጥፈዉ አነበብኩ:: የመረጃዉ አስገራሚነት ደግሞ አንዳንዶቹ ስድስት አክቲቪስቶች ናቸዉ የተጠለፉት ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ ሁለት ናቸዉ ወይም ሶስት ናቸዉ የሚል መረጃ ላይ መከራከራቸዉ ነዉ:: ነገሩን ጠጋ ብሎ ለመረመረዉ ሰዉ ደግሞ አንድም ተጠለፈ ስድስትም ተጠለፈ ለዉጥ የለዉም:: በጣም አስገራሚዉ ነገር ታዲያ እነዚህ ሁለት ወይም አንድ ወይም […]
Read More →ነገሪ ሌንጮ፣ አቦይ ስብሃት በሙስና መታሰራቸውን ይንገሩን ክንፉ አሰፋ
የነጋዴዎች አድማ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ገዥው ፓርቲ ከየአቅጣጫው በመወጠሩ – የችግሩን ትኩረት አቅጣጫ ማስቀየር አለበት። የተለመደ የፉገራ ካርዳቸውን መዘዝ አድርገው ለዶ/ር ነገሪሌንጮ ሰጡዋቸው። ኦቦ ነገሪ ሌንጮ 34 የመንግስት ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ትናንት ምሽት አብስረዋል። እነማን እንደታሰሩ ግን አልገለጹም። ታሳሪዎቹንሊያውቁዋቸው ስለማይችሉ ሊገልጹ እንደማይችሉ ግልጽ ነው። እንደወትሮው ተጽፎ የተሰጣቸውን ከማንበብ ውጭ አማራጭ የላቸውም። የፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን መታሰር እንደማንኛውምተራ ሰው በዜና የሰሙት ነገሪ ሌንጮ ምን አፍ ኖሯቸው ስለ ባለስልጣናት መታሰር ይነግሩናል? ስራዎቼን ሁሉ በግምት ነው የምሰራው – መረጃ እንኳን አይሰጡኝም የሚሉ ጠቅላይ ሚኒስትርስ ምንአቅም ኖሯቸው ጉዳዩን ያስፈጽሙታል? የሙስና ጉዳይ በየአመቱ ነው የሚነሳው። ችግር ሲመጣ እየጠበቁ ለአቅጣጫ ማስቀየርያ ይለቁብናል። አንዳንዴ በሙስና ታሳሪ ገጸ-ባህርያትን ይፈጥሩና አስቂኝ ድራማ ያሳዩናል። ሌላ ግዜ ደግሞየንግድ ባላንጣዎቻቸውን ለመበቀል ይጠቀሙበታል። አንዳንዴም ለመታመን ሲሉ ተራ የመንግስት ሰራተኞችን እና ነጋዴዎችን ይዘው ያጉሯቸውና ግርግሩ ሲረሳሳ ደግሞ ይለቋቸዋል። በእርግጥ የሙስና ተጠርጣሪዎችን ማሰር ቢያስቡ- መጀመርያ አቦይ መስፍንን ወይንም አዜብ መስፍንን በማሰር ያሳዩን ነበር። ጸረ-ሙስናው ዘመቻ እውን ቢሆን ኖሮ የህወሃት የጦር አለቆችበሙሉ መኖርያቸው ቂሊንጦ በሆነ። የአቶ ስብሀት ነጋ ልጅ ተከስተ ስብሀት ነጋ እና እህት ቅዱሳን ነጋ ህልቕ መሳፍርት ንብረት ቢታገድ ነበር ጸረ-ሙስና ዘመቻ ተጀመረ ምንለው። የሙሰኞች ንብረት ታገደ የምንለው የጄነራል ሳሞራ የኑስ፣ የሌ/ጄ ታደሰ ወረደ፣ የሌ/ጄ ገዛኢ አበራ፣ የሌ/ጄ ብርሃነ ነጋሽ፣ የሌ/ጄ ሳእረ መኮንን ቦሌ ላይ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ቤቶችሲታገዱ ነው። ሌ/ጄ ገዛኢ አበራ፣ ሌ/ጄ ብርሃነ ነጋሽ ፣ ሌ/ጄ ሳእረ መኮንን ፣ ሌ/ጄ አበባው ታደሰ፣ ሜ/ጄ አብርሃ ው/ገብርኤል ፣ ሜ/ጄ ዮሃንስ ገ/መስቀል፣ ሜ/ጄ ስዮም ሃጎስ፣ ሜ/ጄ ሃየሎም አርአያ፣ ሜ/ጄ ገ/እግዚአብሄር መብራቱ፣ ብ/ጄ ታደሰ ጋውና፣ ብ/ጄ ተክላይ አሽብር፣ ብ/ጄ ፍስሃ ኪዳነ፣ ብ/ጄ ፓትሪስ፣ ብ/ጄ መስፍን አማረ፣ ብ/ጄ ምግበ ሃይለ፣ ብ/ጄ ሃለፎም ቸንቶ፣ ኮ/ል ታደስ ንጉሴ፣ ኮ/ልጸሃየ መንጁስ በህዝብ ገንዘብ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ያሰሩዋቸው በሚሊዮኖች የሚገመቱ ቤቶች በወር ደሞዛቸው እንዳልሆነ ፖሊስና አቃቤ ህግ ሳያውቁት ቀርተው ነው? እነ ብርሃኔ ገብረ ክርስቶስ፣ አባዲ ዘሙ፣ ስብሃት ነጋ፣ ሽመልስ ኪዳኔ፣ አርከበ እቁባይ፣ አባይ ጸሃዬ፣ ገብረ መድህን ገብረ ዮሃንስ፣ ደብረጽዮን ገብረ ሚካአኤል, ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ ታደሰ ሃይሌ፣ ሰምሃል መለስ ዜናዊ ከባህር ማዶ ያከማቹት በቢሊዮን የሚቆጠር የህዝብ ገንዘብ እስቲ ይታገድ እና ነገሪ ሌንጮን እንመን። ይህን መራራ ሃቅ የሚክድ የለም። ራሳቸውም የሚሉት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲፈሩ ሲቸሩ “ሙስና አለ – ማስረጃ የለም” ብለውናል። አቦይ ስብሃት ደግሞ በሰንደቅ ጋዜጣ አዳልጧቸው “መቶሚልዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፤ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ሲያስፈራሩት ይታያሉ” ብለው ነበር። የየሃገራቱን የሙስና መጠን ደረጃ በየአመቱ የሚዘግበው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናልየተባለዉ ተቋም ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሙስና ከሚፈፀምባቸዉ ሃገራት አንዷ መሆኗን አመልክቷል። እንደ ተቋሙ ዘገባ ከሆነ ከኢትዮጵያ በህወሃት ዘመን ተዘርፎ የወጣው ገንዘብ 17 ቢሊየን ዶላርይደርሳል። ጥናት ከተደረገባቸው 174 ሃገሮች መካከል ኢትዮጵያ 113ኛ ቦታን ይዛለች። ይህ ቁጥር መንግስታዊ ሙስናው ሃገሪቱን ምን ያህል እንደ መዥገር እመጠጠ መሆኑን ያሳየናል። በታቦኢምቤኪ የመሩት ሌላ ጥናት ደግሞ በአምስት ዓመታት ዉስጥ ብቻ ከኢትዮጵያ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ 10 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ወደ ዉጭ እንዲወጣ ተደርጓል። በአንድ ወቅት በጸረ-ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናቱን ንብረት የመመዝገብ ደንብ ወጣና ስራውን ጀመረ። ብዙ የተወራለት ይህ ኮሚሽን ወደ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ቤት ነበር ቀድሞ ያመራው። አይተሳሞራም የጸረ-ሙስናውን ቡድን አስቀምጦ “ስራችሁን አደንቃለሁ። ጥሩ ጅምር ነው። ግን ከላይ ጀምሩ” ብሎ ወደ አዜብ መስፍን መራቸው። ንብረት መዝጋቢዎቹ ወደ አዜብ ቤት ሳይደርሱግማሽ መንገድ ላይ እንደጠፉ ይነገራል። አዲዮስ ፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን! የሲቪክ ማኅበራት በነፃነት መንቀሣቀስ በማይችሉበት፣ የፕሬስ ነጸነት በታፈነበትና የህግ የበላይነት በሌለበት ሃገር ሙስናን እናጠፋለን ማለት በህዝብ ሳይሆን በራስ ላይ መቀለድ ነው የሚሆነው።አላማው ከችግሩ አቅጣጫ ለማስቀየር ከሆነ ደግሞ ሌላ ካርታ መጠቀሙ የሚበጅ ይመስላል። ደጋግማችሁ በተባላ ካርታ አትጫወቱ።
Read More →ሌንጮ ለታ እቅጩን ተናገሩ – “ተቃዋሚዎች ራሳችንን ማታለል የለብንም” | ሊታይ የሚገባው ወቅታዊ ቃለምልልስ ይዘናል
<…ተቃዋሚዎች ራሳችንን ማታለል የለብንም። በአስቸኳይ ከኢህአዴግ ተቃራኒ የሆነ ሀይል መፍጠር አለብን። እነሱ ስልጣን ላይ ሲወጡ ሁለት ስትራቴጂ ነድፈው ነው። ከቻሉ ኢትዮጵያን መግዛት ካልቻሉ እስር በእርስ አጋጭተው አገሪቱን በትነው ወደ መጡበት መሄድ ነው። በአስቸኳይ አማራውም ሌላውም ብሄር የተወከለበት …ሁል ጊዜ ከወያኔ የሚመጣ ነገር መጠራጠር አለብን። እነሱ በሚሰጡን አጀንዳ መነታረክ የለብንም የአዲስ አበባም ጉዳይ ቢሆን እነሱ አማራና […]
Read More →በሲያትል የኢትዮጵያዊው አሟሟት እንቆቅልሽ አልተፈታም
አድማስ ዜና፦ ከሲያትል የተሰማው ዜና አሳዛኝ ነው። ባለፈው እሁድ፣ ጁላይ 23 ንጋት ላይ ነው፣ የ 36 ዓመቱ ይትባረክ ደሞዝ፣ ለባለቤቱ፣ “ጓደኞቼን አንድ ቦታ ማድረስ አለብኝ” ይላትና ይወጣል። በምን ምክንያት እንደሆነ አይታወቅም፣ የጠቀሳቸው ሰዎችና እሱ፣ 25 ጫማ ርዝመት ባለው የይትባረክ ጀልባ ላይ ተሳፍረው ዩኒየን በተባለ ሐይቅ ላይ ነበሩ። በመካከል ድንገት ለፖሊስ አንድ ጥሪ ይደርሳል፣ ጥሪውም […]
Read More →የግብር አሰባብሰብ የአዲስ አበባን ንግድ ተቋማትን እያዘጋ ነው ክልሎችም ይቀጥላሉ
በመዲናችን አዲስ አበባ እና በክክል ከተሞች የተካሄደው የቀን ገቢን አስልቶ የተተመነው የታክስ (ግብር አሰባሰብ ስርአት የተዛባ ከመሆኑ የተነሳ በሃገሪቱ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ለውጥ እንንደሚያመጣ ተፈረⶆል ። እንደ አንዳንድ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች አገላለጽ ከሆነ መንግስት ይህንን ያህል ጫና በማህበረሰቡ ላይ ልጭን የተፈለገበት ዋነኛ ምክንያት በእራሱ በመንግስት ባለስልጣናት በስውር የተመዘበሩ ገንዘቦችን በህዝቡ ላብ ሊተካው ስላሰበ ነው ሲሉ ጠቁመዋል […]
Read More →የግብሩ አመጽ – የፍጻሜው ጦርነት ክንፉ አሰፋ
የአስቸኳይ (የአፈና) ግዜ አዋጁ ገና አልተነሳም። በአዲሱ የግብር ትመና ሳብያ ከዳር እስከዳር የተነሳው ሕዝባዊ አድማ እና አመጽ ግን አዋጁን ውድቅ ያደረገው ይመስላል። አንድ ስርዓት ራሱ ያወጣው ህግ በህዝብ ሲሻርበት – ያኔ ነው ያበቃለት! ከቶውን “የአለምን ኢኮኖሚ እየመራች ያለች ሃገር” የበጀት ሸክሟን ለምን በህዝብ ላይ መጣል እንዳለባት ግልጽ አልሆነም። እውነታው ከነዚህ ሁለት እይታዎች ውጭ […]
Read More →በአዲስ አበባ ሳሪስ፣ ኮልፌ፣ ቡራዩ፣ ደምቢዶሎ፣ ነጆ፣ ነቀምቴ በሥራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው | ወደ ሰሜን ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች ማስጠንቀቂያ ተላለፈ!!
(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት መራሹ መንግስት የጣለውን አግባብ ያልሆነ ግብር በመቃወም የተጀመረው የሥራ ማቆም አድማ በተለያዩ ቦታዎች እየተስፋፋ ነው:: በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሳሪስ እና ኮልፌ አካባቢ ንግድ ሱቆች መዘጋጋታቸው ታውቋል:: ሳሪስ ሙሉ በሙሉ ዝግ ስትሆን በኮልፌ አካባቢ ግን አንዳንድ ነጋዴዎች የመንግስትን ማስፈራሪያ ተቀብለው መክፈታቸው ተሰምቷል:: ለነዚህ ሱቃቸውን በመክፈት መንግስትን ለተባበሩት ነጋዴዎች ከአካባቢው ነዋሪዎች ማስጠንቀቂያ እንደተላለፈላቸው ለማወቅ […]
Read More →EU commend Ethiopia’s initiative to make political reforms
AFRICA INTELLIGENCE MEDIA By Tesfa-Alem Tekle July 20, 2017 (ADDIS ABABA) – The European Union (EU) on Thursday commended the ruling party, Ethiopia peoples Revolutionary Democratic Front (EPRDF) for opening space for dialogue with opposition parties. Currently, 21 political parties, including the ruling coalition EPRDF are engaged in consultations and debate to bring about political […]
Read More →ደራሲና ጋዜጠኛ ነጋሽ ገ/ማርያም በ93 ዓመታቸው አረፉ
ሰበር ዜና / Shocking News by Getu Temesegen #ETHIOPIA | Veteran journalist and author Negash Gebre-Mariam has died, aged 93. (1917 – 2009) • ሥርዓተ ቀብራቸው ነገ፣ ሐምሌ 11 ቀን 2009ዓ.ም በጉርድ ሾላ ሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን በ 9፡00 ሰዓት ይፈጸማል *** በኢትዮጵያ ዘመናዊ ጋዜጠኝነት ታሪክ ከፋና ወጊዎቹ አንዱ ነበሩ፡፡ ከባህላዊው […]
Read More →ዛሬ ብአዴን የተባለው ድርጅት አስገራሚ እና ለመዋጥ እጅግ የሚከብድ መራራ ሀቅ ይዞ ወጥቷል
ከቬሮኒካ መላኩ ዛሬ ብአዴን የተባለው ድርጅት አስገራሚ እና ለመዋጥ እጅግ የሚከብድ መራራ ሀቅ ይዞ ወጥቷል ። ብአዴን የተናገረው እንደወረደ ሲቀርብ << በአማራ ክልል ውስጥ በደርግ ጊዜ ከተተከሉ የኤሌክትሪክ ማሰራጫዎች ውጭ ምንም አይነት አዲስ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ባለፉት 25 አመታት አልተሰራም >> ይላል። ይሄን አይነት የኢኮኖሚ አፓርታይድ እና “ባንቱስታይዜሽን ” በኢትዮጵያ ውስጥ መኖሩን ሁሉም ህዝብ አውቆ ለአመታት […]
Read More →