www.maledatimes.com September, 2017 - MALEDA TIMES - Page 4
Loading...
You are here:  Home  >  2017  >  September  -  Page 4
Latest

ውል ያልተፈጸመባቸው የ40/60 ቤቶች በአዲሱ ዓመት ለካድሬዎች ይተላለፋሉ

By   /  September 7, 2017  /  Ethiopia, ባላገሯ በአሜሪካ  /  Comments Off on ውል ያልተፈጸመባቸው የ40/60 ቤቶች በአዲሱ ዓመት ለካድሬዎች ይተላለፋሉ

ባለ ‹‹4 መኝታ ቤቶች›› ተገንብተዋል የተባለው ሐሰት ነው  ዋዜማ ራዲዮ- በ40/60 ልማት ላይ የተሳተፉና ለዋዜማ ዘጋቢ የሚያውቁትን መረጃያቀበሉ አንድ የንግድ ባንክ የግንባታ ክትትል ባለሞያ ውል የማይፈጸሙባቸው 324 ‹‹ባለ 4-መኝታ ቤቶች›› በመጪው ዓመት ምናልባትም ከከተማው ምርጫ በኋላከድርጅት ለሚወከሉ ካድሬዎች ሊሰጡ እንደሚችሉ የሚያመላክት መረጃን ሰጥተዋል፡፡በተጨማሪም በተለምዶ ‹‹ባለ 4-መኝታ ቤቶች›› እየተባሉ የሚጠሩ የ40/60 ቤቶችእንደሚባለው በዲዛይን ስህተት የተሠሩ እንዳልሆኑም እኚህ ባለሞያ ማስተባበያሰጥተዋል፡፡ መንግሥት በበኩሉ ‹‹ለሙከራ በሠራኋቸው የሰንጋ ተራና የክራውንሳይቶች ባለ አንድ መኝታ አልገነባሁም፣ ባለ 4 መኝታ ቤቶችን ግን በዲዛይን ስህተትሠርቻለሁ ሲል መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ‹‹መጀመርያዉኑ 4 መኝታ የሚባል ዲዛይን አልተሠራም፤ የተገነባው ባለ 1 ባለ2 እና ባለ3 መኝታ ነው፡፡ በዲዛይን ስህተት ነው የሚባለውም ሐሰት ነው›› ሲሉ እኚህከዋዜማ ጋር ቆይታ ያደረጉት ባለሞያ ተችተዋል፡፡ 4 መኝታ የሚባለው ነገር የመጣው ከውል ጋር መታረቅ ያልቻለን የካሬ ሜትር ልዩነትን ለመሸፈን ተብሎ እንጂ ‹‹4 መኝታ›› ያለው ቁጠባ ቤት ሲጀመርም የሚታሰብ ነገር አይደለም›› የሚሉት ባለሞያው ‹‹ባለ አንድ መኝታ አልገነባንም›› የተባለውም መንግሥትን ትዝብት ውስጥየሚጥል እንደሆነ ያብራራሉ፡፡ ‹‹ሁሉም ቤቶች ዕቃ ማስቀመጫና የሠራተኛ ማረፊያ ጠባባብ ክፍሎች አሏቸው፤ ያንን ቆጥረው ነው በዲዛይን ስህተት 4 መኝታ ገነባንየሚሉት›› ብለዋል፡፡ ይህንኑ ሐሳባቸውን የሚያጠናክር ማስረጃዎችን ከዋናው የፕላን ቅጂ ጋር ያቀረቡት ባለሞያው እርሳቸው ፕሮጀክቱ ላይ መሳተፍ ከጀመሩ ጀምሮ ቤቶቹ ‹‹ባለ 4 መኝታ›› ተብለው እንዳልተወሰዱና ኋላ ላይ ግን የካሬ ሜትር ተቃርኖ መኖሩ ሲታወቅ  መስተዳደሩ ባለ 4 መኝታ በዲዛይን ስህተት ምክንያት ተገነባ ብሎ ማውራትመጀመሩን ይናገራሉ፡፡ ‹‹…ከአባተ ጋር በነበረ ስብሰባ ላይ እነዚህ ቤቶች ወደፊት ውል ካልተፈጸመባቸው ምን እናደርጋቸዋለን?›› የሚል ነገር ተነስቶ እንደነበር አውቃለሁ የሚሉትባለሞያው፤ ምክትል ከንቲባው አቶ አባተ በወቅቱ  “ሰፊ ቤት ሰጥተነው ቤቱ ይሰፋብኛ ብሎ ይቅርብኝ የሚል ዜጋ ይኖራል ብዬ አላምንም፤ ካለ ግን እሰየው፣ ቤቱቹንእኛው እንወስዳቸዋለን›› ማለታቸውን ስብሰባው የተካፈሉ ባልደረቦቼ ነግረውኛል ይላሉ፡፡ ከተራዘመ የግንባታ ሂደት በኋላ ባለፈው የሰኔ ወር ዕጣ ወጥቶባቸው ለባለዕድለኞች እየተላለፉ የሚገኙት እነዚህ የሰንጋ ተራና የክራውን 40/60 ቤቶች የወለልስፋታቸው ከውል ውጭ መሆኑ ለረዥም ጊዜያት ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡ ይህን ተከትሎ መስተዳደሩ ‹‹የዲዛይን ስህተት አጋጥሞኝ ነው›› ቢልም እውነታው ከዚህእንደሚለይ እኚህ ባለሞያ በዝርዝር ያስረዳሉ፡፡ ‹‹ሲጀመር የዲዛይን ችግር ብሎ ነገር የለም፡፡ ዲዛይን ታይቶ ሳይጸድቅ ሲሚንቶ አይቦካም፡፡›› የሚሉት ባለሞያው ኾኖም የወለል ስፋት ልዩነት ቀድሞ በውል ላይከሰፈረው ጋር ለምን ሊቃረን እንደቻለ፣ ወይ ቤቱን ወይ ውሉን ለምን ቀደም ብሎ ማስተካከል እንዳልተቻለ ለርሳቸውም ግልጽ አይደለም፡፡ ‹‹ዞሮ ዞሮ ችግሩ እንደሚባለው በቅርብ የተደረሰበት ሳይሆን ቀደም ብሎም ይታወቅ ነበር›› ይላሉ፡፡ እንደ ችግር መታየት የጀመረው ግን ኋላ ላይ ነው፡፡ ለማስተካከልብዙም ያልተሞከረው ምናልባት ‹‹ባለ4 መኝታ›› ቤቶቹ ለድርጅት ሰዎች ለመስጠት እንዲያመች ይሆን ወይ ተብለው ከዋዜማ የተጠየቁት እኚህ የግንባታ ክትትልባለሞያ ‹‹አይመስለኝም›› ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹…መስተዳደሩ በዚህ ደረጃ ነዋሪውን ሆን ብሎ ያጭበረብራል ብዬ አላምንም፤ ምናልባት በመሥሪያ ቤቶችመካከል አለመናበብ የተከሰተ ይመስለኛል፣ ያን ለመሸፈን እንደማምለጫ የተጠቀሙበት ነገር ነው የሚሆነው›› ይላሉ፡፡ ‹‹የዲዛይን ችግሩን››ተከትሎ ‹‹የባለ 3 መኝታ ቤት›› ቆጣቢዎች ‹የባለ 4 መኝታ ቤቶችን የማይወስዷቸው ከሆነ መስተዳደሩ ሙሉ ክፍያ ፈጽሞ ቤቶቹን ለራሱእንደሚያስቀራቸው በይፋ መግለጹ ይታወቃል፡፡ ቤቶቹ ለምን በውሉ መሠረት ሳይገነቡ ቀሩ ለሚለው ጥያቄ በቤት ቆጣቢዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥረው የነበሩት እነዚህ መንግሥት ‹‹ባለ 4 መኝታ›› ቤቶች እያለየሚጠራቸው ቤቶች ከኔ እውቅና ውጭ በዲዛይን ስህተት የተፈጠሩ ናቸው ቢልም ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑት እኚህ የዋዜማ ምንጭ ግን ይህ ነጭ ውሸት እንደሆነአስረግጠው ይናገራሉ፡፡ ‹‹…ምን መሰለህ…ቤቶቹ ንግድ ባንክ ውል ከማዘጋጀቱ በፊት ግንባታቸው ተጀምሮ ነበር፡፡ ቆጣቢዎች ከፈጸሙት ውል ጋር የሚቃረኑ የሆኑት ግን በመስተዳደሩእንዝላልነት እንጂ በዲዛይን ስህተት አልነበረም፡፡››ካሉ በኋላ፣ ‹‹…እውነት ለመናገር…አሁንም ቢሆን ‹‹ባለ 4 መኝታ›› የሚባል ቤት አልተገነባም፡፡ የሆነውምንድነው…ኦሪጅናል ዲዛይኑ ላይም ማየት እንደሚቻለው ሁሉም ቤቶች አንዲት ጠበብ ያለች ዕቃ ቤትና የሠራተኛ ማረፊያ (Maid’s Room) እንዲኖራቸውተደርገው ነው የተዘጋጁት፡፡ ኪችንና ሽንት ቤትን እንደ ወጥ ክፍል እንደማትቆጥረው ሁሉ በዲዛይን ቋንቋ ዕቃ ቤትና የሠራተኛ ማረፊያ እንደ መኝታ ቤት መቁጠርየተለመደ አይደለም፡፡ ለዚህም ነው በሁለቱም ሳይቶች ላይ ባለ አንድ መኝታ፣ ባለ ሁለትና ባለሦስት መኝታ አፓርታማ ቤቶች የየራሳቸው ተጨማሪ ክፍሎችየተገነቡላቸው፡፡ ይቺን ካሬ የማትሞላ የሠራተኛ ማረፊያ ክፍል ምክንያት አድርገው ነው ቆጣቢውን እያወናበዱት ያሉት›› ይላሉ፡፡ በዚህ የተነሳ የባለ አንድ መኝታ ቤትቆጣቢዎች ከውድድር ውጭ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ ያም ኾኖ የቤቶቹ ስፋት ከውል ውጭ መሆኑን ባለሞያው አልካዱም፡፡ ‹‹…እውነት ነው…ባንካችን ከቆጣቢዎች ጋር ከገባው ውል አንጻር የቤቶቹ ካሬ ሰፋ ብሏል፡፡እንጂ በዲዛይን ስህተት ባለ 4 ክፍል መኝታ ተገነባ የሚባለው በፍጹም የተሳሳተ ነው፡፡ እኛ ያቀረብነው ሐሳብ ሁሉም ውል ፈጻሚ ባለ አንድ መኝታ ተመዝጋቢዎችንጨምሮ ማለቴ ነው በገባው ውል መሠረት እኩል ይወዳደር፣ የካሬ ሜትሩን ስፋት የተራዘመ ጊዜ ተሰጥቷቸው እንዲከፍሉ ይደረግ›› የሚል ነበር፡፡ መስተዳደሩ ግንለምን እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ ችግሩን በዲዛይን አሳቦ የባለ አንድ መኝታ ተወዳዳሪዎችን ከጨዋታ ውጭ ማድረጉ አግባብ እንዳልነበረም በዝርዝር አስረድተዋል፡፡ ቤቶቹ ከመመረቃቸው በፊት ከንግድ ባንክና ከመስተዳደሩ ቤቶች ልማት ጋር የነበሩ ውይይቶቹን ያነሱት ባለሞያው ‹‹እኛ ያላለቁ ቤቶችን አንረከብም፣ ከውል ውጭቆጣቢዎችን የተጋነነ ክፍያ አንጠይቅም የሚል አቋም ይዘን ቆይተን ነበር ይላሉ፡፡ ‹‹የቤቶቹን የካሬ ስፋት ከውሉ ጋር መቃረኑን ተከትሎ ምን ቢደረግ ይሻላል?›› በሚል ቤቶቹ ከመመረቃቸው ቀደም ብሎ ተከታታይ ውይይቶች አካሄደናል ያሉትእኚህ የዋዜማ ምንጭ የንግድ ባንክ ተወካዮች የውል ማሻሻያ እንዲደረግ ሐሳብ ያቀረቡ ሲሆን ምክትል ከንቲባው አቶ አባተ ስጦታው በበኩላቸው ውል ብናሻሽልለትችት እንዳረጋለን፣ የቤት ሥራቸውን በትትክል አልሰሩም ነው የምንባለው፣ ከዚህ ይልቅ ባለ አንድ መኝታዎችን ከውድድር ብናወጣቸው ነው የሚሻለው፣ ሌሎቹንካሬ ጨመርንላቸው እንጂ አልቀነስንም፣ ቤቱ ሰፋብኝ ብሎ መዋዋል ያልፈለገ መብቱን እናከብርለታለን፤ እኛም የቤት እጥረት አለብን እኮ፣ የሚተርፉትን ቤቶችተረክበን ለአመራሮቻችን እንሰጣቸዋለን›› ሲሉ በአንድ የውስጥ ስብሰባ መናገራቸውን እንደሚያውቁና በኋላም በዚሁ ጉዳይ ላይ የተናጠል ውሳኔ መወሰናቸውንያስታውሳሉ፡፡ ‹‹እርሳቸው የሚመሩት ተከታታይ ስብሰባ ነበር የሚደረገው፡፡ ምን ያህል ዋጋ ጭማሪ እናድርግ? የቤቶቹ ስፋት ካሬ መጨመሩ ክፋት ባይኖረውም ከውል ውጭመሆኑ ሊያስተቸን ይችላልና ምን ብናደርግ ይሻላል በሚሉ ነጥቦች ላይ ስብሰባ ተካሄዷል፡፡ አንድም ቤቶቹ ላይ በጊዜ ዕጣ ማውጣት ያልተቻለው በነዚህአለመግባባቶች ምክንያት ነበር፡፡ በዲዛይን ችግር የተነሳ የመኝታ ቤት ቁጥር ጨምሯል በሚል ማስተባበያ ሰጥተን ቤቶቹን ለኛው እናስቀራቸው የሚል ነገር የመጣውግን ኋላ ላይ ነው፡፡›› ይላሉ ባለሞያው፡፡ ዋዜማ የ40/60 ቤቶች የመጀመርያ ዲዛይን ቅጂ ያገኘች ሲሆን የወለል ፕላኑ እንደሚያመለክተው 12 ፎቆች የሚረዝሙት ሕንጻዎች 10 ወለሎቹ ተመሳሳይአቀማመጥን የሚከተሉ በወለል 6 አባወራዎችን ብቻ የሚይዙ እንደሆኑ ለመረዳት ችላለች፡፡ በእያንዳንዱ ወለል ሁለት ባለ አንድ መኝታ፣ ሁለት ባለ ሦስት መኝታ እናሁለት ባለ አንድ መኝታ ክፍሎችም ይገኛሉ፡፡ ሁሉም ክፍሎች ዕቃ ክፍልና የሠራተኛ ማረፊያን ያካትታሉ፡፡ እያንዳንዱ ሕንጻ ሁለት ሊፍቶች የተገጠሙለት ሲሆንየቆሻሻ መወርወርያ (ጋርቤጅ ሹተር) እንዲሁም የአደጋ ጊዜ መውጫ ደረጃዎችንም ተነድፈውለት ነበር፡፡ በሁለቱም ሳይቶች በድምሩ 19 ሕንፃዎች ተገንብተዋል፡፡ ሕንፃዎቹ መጀመርያ ጊዜ ሊገነቡ የነበረው ባለ አንድ መኝታ ቤት 55 ካሬ ሜትር፣ ባለ ሁለት መኝታ ቤት 75 ካሬ ሜትርና ባለ ሦስት መኝታ ቤት 100 ካሬ ሜትር የነበረ ቢሆንም፣ በተደረገው የዲዛይን ለውጥ ካሬ ሜትሮቹ ተቀይረው፣ ባለ ሁለት መኝታ ቤት 124.97 ካሬሜትር፣ ባለ ሦስት መኝታ ቤት 150.09 ካሬ ሜትርና ባለ “አራት መኝታ ቤት“ 168.6 ካሬ ሜትር ስፋት እንዲኖራቸው ሆኗል፡፡ ባለ አራት መኝታ የተባሉትን ቤቶች ምናልባት በየዓመቱ ለመንግሥት ሹሞች ከፍተኛ የቤት ጥያቄ እየቀረበለት ማስተናገድ ያልቻለው የቀድሞው የመንግስት ቤቶችኤጀንሲ በግዢ ሊረከባቸው እንደሚችል ይገመታል፡፡ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በቅርቡ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ኾኖ እንደ አዲስ ከተዋቀረ ወዲህ ከማዕከልናከክፍለ ከተማ የሚገኙ ባለሞያዎችን በከፍተኛ ወርሃዊ ደመወዝ እየወሰደ ይገኛል፡፡ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮም በቤቶች ግንባታ ዘርፍ ለመሠማራት ዝግጅት እያደረገነው፡፡ ለጊዜው በሰንጋ ተራና በክራውን ውል ያልተፈጸመባቸውን ቤቶች በቁጥር ምን ያህል እንደሆኑ በውል ባይለይም ከመጪው ዓመት የከተማዋ ምርጫ በኋላለሚሾሙ መካከለኛ ካድሬዎች እነዚህን ቤቶች እንዲወስዷቸው እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

Read More →
Latest

After big dam gamble, Ethiopia seeks private energy for power surge

By   /  September 6, 2017  /  AFRICA, CRIME, EASTAFRICA, WEST AFRICA, ኣማርኛ  /  Comments Off on After big dam gamble, Ethiopia seeks private energy for power surge

By William Davison Ethiopia’s public investment in mega dams has been a bold attempt to make up for Africa’s power deficit. But despite some impressive achievements, doubts remain about the efficiency of those schemes, as the government leaves its comfort zone to try and attract private capital into renewable energy projects. The stink of garbage […]

Read More →
Latest

የአባቶቻችን ሀገር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን እስኪሆን ድረስ ትግሉ ይቀጥላል::

By   /  September 6, 2017  /  Addis Admas, Ethiopia, ባላገሯ በአሜሪካ  /  Comments Off on የአባቶቻችን ሀገር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን እስኪሆን ድረስ ትግሉ ይቀጥላል::

በሸንቁጥ አየለ የአባቶቻችን ሀገር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን እስኪሆን ድረስ ትግሉ ይቀጥላል:- ወያኔ የሸረበዉ የቅማንት-አማራ ግዛት የማካለል ሂደት ሁሉ የተለመደ ወንጀል ነዉ:: =========================================== ወያኔ የሰራዉ ህገ መንግስት ፈራሽ ነዉ::ወያኔ የከለለዉ ክልል ፈራሽ ነዉ::የአማራ: የኦሮሞ: የደቡብ: የትግሬ የእንቶኔ ብሎ ወያኔ የከለለዉ ክልል ሁሉ ፈራሽ ነዉ::ህገወጥ እና ወንጀል ነዉና::አሁንም ወያኔ የቅማንት መሬት ይሄ : የአማራ መሬት ያኛዉ ብሎ የሚከልልለዉ […]

Read More →
Latest

“የቴዲ አፍሮ አልበም ምረቃ እገታ የእኔ ስህተት አይደለም” ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር

By   /  September 6, 2017  /  Ethiopia, ባላገሯ በአሜሪካ  /  Comments Off on “የቴዲ አፍሮ አልበም ምረቃ እገታ የእኔ ስህተት አይደለም” ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር

? “የቴዲ አፍሮ አልበም ምረቃ እገታ የእኔ ስህተት አይደለም” ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ቴዲን ጨምሮ በዝግጅቱ ላይ እንዲታደሙ የተጠሩት 900 ናቸው… እነሆ ዝርዝሩ… በቴዲ አፍሮ የሲዲ አልበም ምርቃት ክልከላን በተመለከተ አንዳንድ የማህበራዊ እና የመገናኛ ብዙሀን ሚድያዎች ጉዳዩን እኔላይ ማላከካቸው አግባብ አይደለም ሲል ጆርካ ኢቨንት ለሁሉ አዲስ ተናገረ፡፡ የቂርቆስ ክፍለከተማ ፖሊስ መምርያ ሀላፊ ምክትል ኮሚሽነር ሽመልስ ሽፈራው […]

Read More →
Latest

ኢትዮጵያ ያለ«ኢትዮጵያዊነት» ልትኖር አትችልምን?

By   /  September 6, 2017  /  Addis Admas, Ethiopia, ባላገሯ በአሜሪካ  /  Comments Off on ኢትዮጵያ ያለ«ኢትዮጵያዊነት» ልትኖር አትችልምን?

  በፍቃዱ ዘ ሃይሉ በአዲስ አበባና ዙሪያዋ በጣም ተወዳጁ ኤፍኤም ሬዲዮ ሸገር ነው ቢባል የሚያጣላን አይመስለኝም። ሸገር መፈክሩ “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” የሚል ነው፡፡ አሁን ደግሞ ፖለቲከኞችም ይህንኑ መፈክር የንግግራቸው ማሳረጊያ ዓረፍተ ነገር እያደረጉት ነው። ሰማያዊ ፓርቲ ከመግለጫዎቹ ግርጌ “ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር” የሚል ዓረፍተ ነገር ያስቀምጣል። አዲሱ በእነሰይፉ ፋንታሁን እና ሠራዊት ፍቅሬ… የተከፈተው ኢትዮ ኤፍኤም […]

Read More →
Latest

ኦነግ በኦሮሚያ የሚደረገውን አድማና ትግል እየመራ መሆኑን አስታወቀ

By   /  September 5, 2017  /  Ethiopia, ባላገሯ በአሜሪካ  /  Comments Off on ኦነግ በኦሮሚያ የሚደረገውን አድማና ትግል እየመራ መሆኑን አስታወቀ

Dawuud Ibsa (center) ዋዜማ ራዲዮ- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በቅርቡ የተደረገውን ቤት የመቀመጥ አድማ ጨምሮ በኦሮሚያ ወጣቶች በአፋኙ ስርዓት ላይ የሚያደርጉትን ትግል ከፊት ሆኜ እየመራሁት ነው ሲል አስታወቀ። ድርጅቱ በኤርትራ አስመራ ለአስር ቀናት ያደረገውን ጉባዔ ሲያጠቃልል ባወጣው መግለጫ የኦነግ ክንፍ የሆነው የኦሮሞ ወጣቶች ክንፍ (ቄሮ) እያካሄደ ያለው ትግል ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን አስምሮበታል። ኦነግ ለቄሮ የሚያደርገውን ድጋፍ […]

Read More →
Latest

‘I can’t pay’: taxing times for small traders in Ethiopia hit by 300% rate hike

By   /  September 5, 2017  /  AFRICA  /  Comments Off on ‘I can’t pay’: taxing times for small traders in Ethiopia hit by 300% rate hike

  William Davison, Addis Abeba  In the dense cobblestone streets of Burayu town, outside Addis Ababa, Melaku Abdella and his family had been making a living selling basic items such as vegetables, cooking oil and soft drinks at competitive prices from their kiosk. But after the Ethiopian government stung him with a more than 300% […]

Read More →
Latest

በሽሬና ወልቃይት ጸለምት ኣውራጃዎች የኮሌሯ ወረርሽን እንደ እሳት ሰደድ ተቀጣጥለዋ !!!!

By   /  September 5, 2017  /  Ethiopia, ባላገሯ በአሜሪካ  /  Comments Off on በሽሬና ወልቃይት ጸለምት ኣውራጃዎች የኮሌሯ ወረርሽን እንደ እሳት ሰደድ ተቀጣጥለዋ !!!!

መንግስት ግን በሽታው ኮሌሯ ብሎ የጠሩ ዜጎች እንደ ወንጀሎኞች ይመለከታቸዎል !!! ——————————————————— የኮሌሯው ወረርሽን በወልቃይት ሕሞራ በኣዲ ጎሹ በመዘጋ በጸለምት ቆላማ ወረዳዎች ፣ በባድመ ፣በሸራሮ ፣ በሰዬምት ኣድያቦ ፣ በእስገደ ፣ በጽንብላ ፣ በታሕታይ ቆራሮ ፣ በዛና ፣ በመደባይ ፣ በሰለክለካ ፣ወረዳዎች እንዲሁም የሽሬ ኣውራጃ ኩቷ ገጠም የሆኑ የኣክሱም ኣውራጃ ወረዳዎች በሽታው ተስፋፍታል ። በኮሌራው […]

Read More →
Latest

ጃዋር መሃመድ ከቴዲ አፍሮ ጎን በሰበአዊ መብት መከራከር ዘንድ ቆመ

By   /  September 4, 2017  /  Addis Admas, Ethiopia  /  Comments Off on ጃዋር መሃመድ ከቴዲ አፍሮ ጎን በሰበአዊ መብት መከራከር ዘንድ ቆመ

  ምንጭ (ዘ-ሐበሻ) የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር ጀዋር መሐመድ አምባገነኑ የሕወሓት መራሹ መንግስት በቴዲ አፍሮ ላይ በተደጋጋሚ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አወገዘ:: “ገዥው አካል ለቴዲ አፍሮ የሚያቀርበውን ትርዒት በተደጋጋሚ በመሰረዙ ተገቢ ያልሆነ እና ኢፍትሃዊ ውሳኔ ነው” ያለው ጀዋር በቴዲ ላይ መንግስት የሚወስደው ክልከላ “ይህ ሁሉ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነትን እና ዒላማው የኪነጥበብ ጥቃትን ስለሚያካትት ሁሉም ሊያወግዘው ይገባል” […]

Read More →
Latest

የቴዲ አፍሮን የሲዲ ምረቃ እንዳይካሄድ ያገደው የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መሆኑ ታወቀ

By   /  September 4, 2017  /  Addis Admas, Ethiopia  /  Comments Off on የቴዲ አፍሮን የሲዲ ምረቃ እንዳይካሄድ ያገደው የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መሆኑ ታወቀ

ይልቅ ወሬ ልንገርህ በታምራት ሀይሉ በትላንትናው እለት ሊካሄድ ፕሮግራም ተይዞለት የነበረው የተወዳጁ አርቲስት ቴዲ አፍሮ የሲዲ ምረቃ ፕሮግራም ሊካሄድ ያልቻለው በአዘጋጁ ጆርካ ኤቨንት በኩል መቅረብ የነበረበት የእውቅና/ፍቃድ ወረቀት ባለማቅረቡ እንደሆነ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ም/ኮምሽነር ሽመልስ ሽፈራው ዛሬ ለቁም ነገር መጽሄት ተናግረዋል። ባለፈው ሀሙስ ጠዋት የፖሊስን ድጋፍ የሚጠይቅ ደብዳቤ የጆርካ ኤቨንት ሰዎች ይዘው […]

Read More →
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar