www.maledatimes.com January, 2018 - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  2018  >  January
Latest

“ጃ ያስተሰርያል!” አራት አመታት ተከልክሎ በነበረ መድረክ? ክንፉ አስፋ

By   /  January 27, 2018  /  Addis Admas, Ethiopia  /  Comments Off on “ጃ ያስተሰርያል!” አራት አመታት ተከልክሎ በነበረ መድረክ? ክንፉ አስፋ

            ቴዲ ወደ ባህርዳር ሲያቀና “እንዘምራለን”  ማለቱን ያስተውሏል!።  የጉዞውን አላማ እንዲያ ሲል ነበር ረቂቅ በሆነ መንገድ የገልጸው።  በመዘመር እናበመዝፈን መሃል ያለውን ጥልቅ ልዩነት የማይረዳ ብቻ ነው ለሰሞኑ “አሲዮ ቤሌማ” እጅ የሚሰጠው።  ከኮንሰርቱ ጀርባ ያለው “የፍቅር ጉዞ” የሚለው መሪ ቃልውስጥም ከውቅያኖስ የጠለቀ መልዕክት አለ። ይህንን ቃል የተረዳ ብቻ ነው የተልእኮውን ስኬት ሊያበስር የሚችለው። ዝግጅቱ ኮንሰርት እንጂ ዳንኪራአይደለም። ሁለት ወይንም ሶስት ሰዓት ብቻ የፈጀ ኮንሰርት። ጥላቻ ሳይሆን ፍቅር የነገሰበት ኮንሰርት።  ትንሳዔን አብሳሪ ኮንሰርት። መዝሙር ውስጥ መልዕክት አለ። የሚያንጽ፣ የሚያነቃቃ መልዕክት። መላው በጠፋበት በዚህ ወቅት፤  ኢትዮጵያ የምትሻው የተስፋ ቃል ብቻ የሚደሰኩርላትን ሳይሆን ድልድይ የሚዘርጋላትን ሰው ነው።  ጥላቻነግሷል። በሃገራችን ስር ሰድዶ፤ ቤተ እምነትን ሳይቀር አምሶታል፤  ጥላቻ – ጥላቻን ይወልዳል እንጂ ችግርን አይፈታም።  እሱን ለማንገስ ላለፉት 27 ዓመታትብዙ ድንጋይ ተፈንቅሏል። አዎ ጥላቻ በሽታ መሆኑን አይተናል። ይህን ክፉ በሽታ ለማርከስ  የፍቅርን ዳገት መውጣት ግድ ይላል። ጉዞውን ቴዲ ጀመረው። ጥላቻን የሚያከስሙ ዜማዎቹን የሰሙ …  እነ ለማ መገርሳእነ … ዶክተር አብይ ተከተሉት።  ለማ መገርሳ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ማለቱ  የቴዲ “ሲንድረም” ስለመሆኑ የሚጠራጠር ይኖር ይሆን?             ጎበዝ፣  ዘመኑንም እንቃኘው እንጂ!   ሰው ለታቦት ንግስ ወጥቶ በዚያው የሚቀርበት ዘመን እኮ ነው ያለነው። ወገን የእሬቻን በዓል ለማክበር ሄዶእስከዘላለሙ የማይመለስበት ወቅት ላይ ነን።  ልቅሶና ሃዘንን ሰብሰብ ብሎ በጋራ የማይካፈሉባት ምድር፣  ምእመናን ለጸሎት ወጥተው የሚታፈኑበት ሃገር ላይእንደተቀመጥን ለአፍታም አንዘንጋው።  ኮንስርት ማድረግ  ብርቅ የሆነበት ሃገር። ዳር ድንበር እንዲያስከብር የተላከ ወታደር  መሃል  ከተማ ገብቶ የወገን ደምየሚያፈስስበት ምድር!  በዚህች ያልታደለች ሃገር፣ በዚህ አስከፊ ዘመን፣   “ጃ ያስተሰርያል”ን  አጥንት ይዘን ስንጓተት አጃኢብ አይሆንም?             ይህ እሰጥ እገባ  ልብ ላለው ሁሉ ቅንጦት ይሆናል።  ነገሩን በደንብ የተረዳው ወገን፣  ከ 50 ሺህ ሕዝብ  በላይ በታደመበት ዝግጅት ላይ  “ምንይፈጠር ይሆን?”  እያለ የልቡ ትርታ ከፍ እና ዝቅ ይል ይሆናል እንጂ፣  ቀሪ ሂሳብ አያወራርድም።  ጥሩ ዜና በሚናፈቅበት በዚህ ቀውጢ ሰዓት፣  ሰማይ ላይየወጣን የሕዝብ እምቅ ስሜት ተቆጣጥሮ በሰላም ማጠናቀቅ መቻል እጅግ የሚደነቅ ነገር  ነው። ስለዚህም ጉዳዩ የገባቸው ዝግጅቱ  “እንኳን በሰላም አለቀ!” ይላሉ።  ሻንጣ በጀርባ ሸክፎ ማራቶንን መሮጥ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ የሚያውቀው ሯጩ ብቻ ነው።            እርግጥ ነው ሕዝብ ፍላጎቱን ገልጿል። የሕዝብ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ማግኘት ነበረበት።  የሕዝቡ ጫና ቀላል አልነበረም።  ይህንን በተመለከተ ከቴዲአካባቢ የሚሰማው ነገር የህዝብ ስሜትን ያለመረዳት ጉዳይ አይደለም።   ስሜትን መረዳት እና ስሜትን መንዳት ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው።   26ኛውየአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ቴዎዶር ሩዝቬልት በአንድ ወቅት ሲናገሩ “በመሪዎች እና በአለቃ መካከል ያለውን ልዩነት ሰዎች ይጠይቃሉ።  መሪ ይመራል።አለቃ ደግሞ ይነዳል” ብለዋል።  መንዳት እጅግ ቀላል ነው። ውል ለማስያዝ መምራቱ ነው ከባድ።         አራት አመታት ሙሉ ተከልክሎ የነበረ መድረክ፣  በሰላም እንዳያልቅ፣   እንከን የሚያሸትቱ ተንኳሾች  አሰፍስፈው የሚጠብቁት ነገር ነበር። የጌታቸውማንጉዳይ ጣልቃ መግባት ነገሮችን አስቀድሞ የመረዳት፣ አርቆ የማሰብ እና የመብሰል ውጤት ነው።  በዚህ ፍቅር ጉዞ እቅድ ላይ  “ጃ ያስተሰርያል”አልነበረም።  ጉዞው ለመዝፈን ሳይሆን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው።  የሰላም እና የፍቅር መልዕክት።  በዚያ ውስጥ ሃዘን አለ። በዚያ ውስጥ ብሶት አለ። በዚያውስጥ ቁጭትም አለ።   በነገራችን ላይ በኮንሰርቱ ላይ ባለስልጣኖቹ በይገኙም ልጆቻቸው እና ሚስቶቻቸው በሙሉ ስቴዲየም ገብተው ከሕዝቡ ጋር ሲደሰቱነበር። ሕዝብ በአንዲት ቃል ብቻ ማነሳሳት እጅግ ቀላል ነው።  በረጅሙ የሚያይ ሳይሆን አጭሩን አላማ የመረጠ ይህንን ማድረግ ይቀልለዋል። ከዚህ ግፊትየሚገኘው ውጤት፣  ኪሳራ እንጂ ትርፉ ሚዛን ሊደፋ አይችልም።  ጥይቱንም፣ ቀለሃውንም የያዙ ሃይሎች ሰፍ ብለው ይህችን ወቅት እንደሚጠብቁአንዘንጋ። እያወራን ያለነው ስለ ሞብ  ስነ-ልቦና ነው። ሞብ  የማህበረሰብ ስነ-ልቦና አካል ነው። የስነልቦና ምሁራን የሆኑት ጉስታቭ ሌቦን እና ሲግሞንድ ፍሬድ”ሰዎች አንድ አላማ ይዘው በሲሰባሰቡ በሚጋሩት የጋራ የሆነ አመለካከት፣  ግላዊ ሃላፊነትን ከአናታቸው አርደው ስለሚጥሉ፣  ምንም ነገር ከማድረግአይቆጠቡም ” ይሉናል።             ይህን ያህል ግዙፍ ኮንሰርት ይቅርና ሰዎቹ የራሳቸው የመቀሌው ስብሰባም “በሰላም አለቀ” ይሉን የለ? በረጅሙ እየተነፈሱ “የአዲስ አበባው ጥምቀትበዓል በሰላም ተጠናቀቀ” ብለውናል። በተዘዋዋሪ ሰላም የምትለው ቃል  እንደ ዳይኖሰርስ  ከምድሪቱ ጠፍታለች እያሉን እኮ ነው። ሰዎቹ እኮ አስከሬን አጅቦየሚሄድን ለቀስተኛ እንኳን ማመን የተሳናቸው፣ በራስ ገመድ ተጠልፈው፣  የራሳቸውን ጥላ እንኳን የሚፈሩ፣….  ምጥ ውስጥ ያሉ ናቸው።  የፈሪ ዶላ ረጅምነው እንዲሉ በጋራ ሆኖ ያዜመ ላይ ሳይቀር የሚተኩሱት  ለዚህም ነው።             ትልቁን ጥበብ እና ማስተዋል የሚጠይቀው ሕዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ ሊመጣ የሚችለውን ችግር ማስወገድ መቻል ነው።  ይህ አርቆ ማሰብንይጠይቃል። ቅዝምዝም ሲወረወር ጎንበስ ብሎ የሚያልፍ  አስተዋይ ብቻ ነው። የሕዝብን ስሜት ማረጋጋት መቻል ራሱን የቻለ ጥበብ ይጠይቃል። ብሶትያጋለው ሕዝብ ነው። እልህ የተናነቀው ሕዝብ። በቋፍ ላይ ያለ ሕዝብ።   አንድ ነገር ለማድረግ ጥቂት ቃላት ብቻ ይበቃሉ። ደግሞ ጨዋ ነው። መሪውን የሚሰማ – ለሚወድደው የሚታዘዝ ሕዝብ።             ሁሉም ነገር ግዜውን ጠብቆ ይከሰታል። ከዚህ ቀደም ቴዲ “ጃ ያስተሰርያል”ን ለምን አልዘፈነም ብለን ጮኸናል። ለጩኸታችን ምክንያቱ አጥጋቢይሁንም-አይሁን፣  ወቅቱ ይህንን ለማለት ይፈቅድ ነበር። ከአመታት በፊት “ጃ ያስተሰርያል”  ሲዘፈን የነበረው ሁነታ አሁን የለም። አሁን  ስለ ለውጥ እና ስለአዲስ ንጉስ መምጣት አይደለም የምንጨነቀው። የመኖር እና የአለመኖር፣ የለህልውና ጥያቄ ላይ ደርሰናል።  የንጹሃን ደም በየቀኑ ይፈስሳል።  ሃገር እንደጉድይዘረፋል። እየተካሄደ ያለውን ግፍ ቃላት አይገልፀዉም።  ነገሩን ከስሜት መነጽር ወጣ አድርገን እንመልከተው።  ፈጥኖ መፍረድ እና ፈጥኖ መናደድ ከአመክንዮ ሳይሆን ይልቁንም ከፍርሃት እና ከድንቁርና ጋር እጅ ለእጅ የሚሄድ ነገር ነው። […]

Read More →
Latest

 የገዱ አንዳርጋቸው መግለጫ ሲተረጎም ክንፉ አሰፋ

By   /  January 27, 2018  /  Addis Admas, Ethiopia, ባላገሯ በአሜሪካ  /  Comments Off on  የገዱ አንዳርጋቸው መግለጫ ሲተረጎም ክንፉ አሰፋ

 የገዱ አንዳርጋቸው መግለጫ ሲተረጎም ክንፉ አሰፋ ኦቦ ለማ መገርሳ ህወሃት ያጎራቸውን 2,345 እስረኞች ነጻ አወጡ የሚለውን ዜና በቀኝ እየሰማን፣ የጉዱ አንዳርጋቸው መግላጫ ደግሞ በግራ በኩል ብቅ አለ። ሰበር ጋዜጣዊ መግለጫ። በርግጥም “ወገብ የሚሰብር”። ልዩ መግለጫው ተከባብዶ ሲነገረን “ገዱ ደግሞ ስንት ሺህ አማሮችን ከእስር አስለቀቀ” እያልን በጉጉት ባንጠብቅም  “የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ሕዝቦች ሆይ  በወልድያ እና በቆቦ ለተፈጸመው እልቂት […]

Read More →
Latest

ናይጄሪያዊው ሰባት ዓመት ፅኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነበት

By   /  January 18, 2018  /  Addis Admas, Ethiopia, ባላገሯ በአሜሪካ  /  Comments Off on ናይጄሪያዊው ሰባት ዓመት ፅኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነበት

ሪፖርተር ፡ ታምሩ ጽጌ እንዳይመረትና እንዳይዘዋወር ክልከላ የተጣለበትን አደንዛዥ ዕፅ (ኮኬይን) ይዞ ለማለፍ ሲሞክር ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ሥር ውሎ ክስ የተመሠረተበት ናይጄሪያዊ፣ በሰባት ዓመታት ፅኑ እስራትና በ15,000 ብር እንዲቀጣ ውሳኔ ተሰጠ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የመሠረተውን ክስ ሲመረምር የከረመው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ወንጀል ችሎት፣ ቅጣት የጣለበት ናይጄሪያዊ […]

Read More →
Latest

‹‹ኢትዮጵያውያን የህዳሴ ግድቡን ለመገንባት ጫናውን ለብቻቸው ስለተሸከሙ ዕዳ አለብን›› – የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር  

By   /  January 18, 2018  /  Addis Admas, Ethiopia, ባላገሯ በአሜሪካ  /  Comments Off on ‹‹ኢትዮጵያውያን የህዳሴ ግድቡን ለመገንባት ጫናውን ለብቻቸው ስለተሸከሙ ዕዳ አለብን›› – የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር  

ማለዳ መረጃ ማእከል የእርስዎ የዜና አውታር ሪፖርተር: ዮሐንስ አንበርብር የኢትዮጵያና ግብፅ የሚኒስትሮች ስብሰባ ዛሬ ይጀመራል የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡን በመገንባት ጫናውን ለብቻቸው እንደተሸከሙ፣ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር ተናገሩ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን መልዕክት ሲያደርስና በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ […]

Read More →
Latest

በኢትዮጵያ የታሠሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ተጠየቀ

By   /  January 18, 2018  /  Addis Admas, Ethiopia  /  Comments Off on በኢትዮጵያ የታሠሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ተጠየቀ

 Maleda Times Media Group ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ጠየቀ። ድርጅቱ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተዉ የተሻለ የፖለቲካ መድረክ በሀገሪቱ ለመፍጠር ፤የኢትዮጵያ መንግስት በፀረ ሽብር ሕጉ «ጥፈተኛ ናችሁ »ብሎ ያሰራቸዉን ጋዜጠኞች ሊለቅ ይገባል። ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተዉ ይህ ድርጅት ጋዜጠኞቹ እንዲፈቱ የጠየቀዉ፤የኢትዮጵያ መንግስት በወንጀል ድርጊት የተፈረደባቸዉና በዓቃቬ ህግ […]

Read More →
Latest

ኔዘርላንድስ የኤርትራውን አምባሳደር “ተቀባይነት የሌለው ሰው” ስትል አወጀች

By   /  January 18, 2018  /  Addis Admas, Ethiopia  /  Comments Off on ኔዘርላንድስ የኤርትራውን አምባሳደር “ተቀባይነት የሌለው ሰው” ስትል አወጀች

 ኔዘርላንድስ የኤርትራውን አምባሳደር ተከስተ ገብረመድህን ዘሙይን በሀገሯ ተቀባይነት የሌለው ሰው በማለት ኔዘርላንድን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች። በኔዘርላንድስ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር በተጻፈ ደብዳቤ አምባሳደሩ ለምን ከሀገር እንዲወጡ እንደተወሰነ በዝርዝር ተቀምጧል። ደች አርጎስ የተባለው ሬዲዮ ዘገባን ተከትሎ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ በጻፉት ደብዳቤ ከዚህ ውሳኔ የደረሱት፤ የኤርትራ ስደተኞች የቆንሱላ አገልግሎቶችን ለማግኘት በኤርትራ ኤምባሲ የዲያስፖራ ግብር እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ ብለዋል። የውጪ […]

Read More →
Latest

አቶ አባይ ወልዱ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

By   /  January 18, 2018  /  Addis Admas, Ethiopia  /  Comments Off on አቶ አባይ ወልዱ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

By  Getu Temesgen Maleda Times Media group  ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት ሹመት ሰጡ። በዚህም መሰረት አቶ አባይ ወልዱን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እንዲሁም ወይንሸት ታደሰን የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልእክተኛ ባለሙሉ ስልጣን ሆነው መሾማቸውን የፕሬዘዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል። በቅርቡ በአፍሪካ ኅብረትና በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፣ የሹመት […]

Read More →
Latest

አንድም እናት መሞት የለባትም በሚለው የመንግስት አዋጅ ወጣቶች በሃኪሞች ግዴለሽነት እየሞቱ ነው ።

By   /  January 18, 2018  /  Addis Admas, Ethiopia  /  Comments Off on አንድም እናት መሞት የለባትም በሚለው የመንግስት አዋጅ ወጣቶች በሃኪሞች ግዴለሽነት እየሞቱ ነው ።

በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ አጣዬ ከተማ ባለው ሆስፒታል እየተከናወነ ያለው አስደንጋጭ ትእይንት ህዝብን አስደንግጧል ፣ ባለፉት ወራት ብዙ ወጣቶች ወደ ሆስፒታሉ ገብተው ህይወታቸውን እያጡ መመለሳቸው መንግስትም ምላሽ እንዲሰጣቸው ፣ህዝቡም የአመለካከት አድማሱን አስፍቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሲሉ ገልጠዋል ። በትላንትናው እለት ከዞኑ መስተዳድር ከሚኖሩ ዜጎች ለማለዳ እና ዘሃበሻ መረጃ ማእከል አቤቱታቸውን ያደረሱን ግለሰቦች […]

Read More →
Latest

ማዕከላዊ እስር ቤትን መዝጋቱን ትንሽ ብታቆዩት

By   /  January 3, 2018  /  Addis Admas, Ethiopia, ባላገሯ በአሜሪካ  /  Comments Off on ማዕከላዊ እስር ቤትን መዝጋቱን ትንሽ ብታቆዩት

  ማዕከላዊ እስር ቤትን መዝጋቱን ትንሽ ብታቆዩት የደርግ ባለስልጣናት በአስራ አንደኛው ሰዓት ላይ ከርቸሌን ማሰማመር ጀምረው ነበር።   በወቅቱ ምን እንደታያቸው ግልጽ ባይሆንም፤የኋላ ኋላ ግን ያንን ማድረጋቸው እንደጠቀማቸው አይተናል። በጅምር ላይ ከነበሩ የልማት ተቋማት ይልቅ ይህ የእስር ቤት  ግንባታ ቅድሚያ ተሰጠውና፣  ከርቸሌ ቅጥር ግቢ ውስጥ “አለም በቃኝ” የተሰነውን ክፍል እንዲገነባ አደረጉ።   በመጨረሻም “አለም በቃኝ”  የደርጎች  ማረፍያ […]

Read More →
Latest

ግልፅ ደብዳቤ ለአርቲስት ዘለቀ ገሰሰ :- ብዙ ዜጎች በሚሞቱባት ሀገር ፓርቲዎችን በሴራ እያፈረሱ ለአገዛዙ እድሜ ማራዘሚያነት እንዲውሉ መስራት ግን ታሪክ ይቅር የማይለው ሀገራዊ በደል ነው። 

By   /  January 2, 2018  /  Addis Admas, Ethiopia, ባላገሯ በአሜሪካ  /  Comments Off on ግልፅ ደብዳቤ ለአርቲስት ዘለቀ ገሰሰ :- ብዙ ዜጎች በሚሞቱባት ሀገር ፓርቲዎችን በሴራ እያፈረሱ ለአገዛዙ እድሜ ማራዘሚያነት እንዲውሉ መስራት ግን ታሪክ ይቅር የማይለው ሀገራዊ በደል ነው። 

ግልፅ ደብዳቤ ለአርቲስት ዘለቀ ገሰሰ ጉዳዩ:- ፓርቲያችንን አላማውን ለማሳት የሚያደርጉትን ተግባር እንዲያቆሙ ስለማሳሰብ ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የድርሻውን ሃላፊነት ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ወጣት ሳሙኤል አወቀን ጨምሮ ብዙ አባላት ውድ የሆነውን የህይወት መስዕዋትነት ከፍለዋል። ቆራጥ አባሎቹም በየማጎሪያ ቤቱ እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ብዙዎች አካላቸው ጎድሉዋል፣ ከስራ ተባረዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ ቤተሰባቸው ተበትኑዋል። ነገር ግን ይህንን ብዙ መስዕዋትነት የተከፈለበትን ፓርቲ […]

Read More →
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar