የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የመገንባት ኃላፊነት የተሰጠው ቤቶች ኮርፖሬሽን አዲስ አደረጃጀት ሊያዋቅር ነው
በበጀት ዓመቱ የአዳዲስ ቤቶች ግንባታ ባለመጀመሩ አላስፈላጊ ወጪ እየጨመረ ነው በጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ መስክ ግዙፍ ሥልጣን ተሰጥቶት የተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ኮርፖሬሽን አዲስ አደረጃጀት ሊያዋቅር ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮና በሥሩ ካሉ ተቋማት የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን፣ በዚህ ሳምንት አዲስ አደረጃጀት ለማዋቀር የሚያስችሉ ሥራዎችን መሥራት ይጀምራል ተብሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ እስካሁን […]
Read More →‹‹ዛሬ ነገ እየተባለ የጠፋው ጊዜ ከባድ ጉዳት አድርሷል›› የአገር መከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ
በተደረገለት የሰላም ጥሪ መሠረት አገር ቤት ገብቶ በሰላም ለመንቀሳቀስ ከኤርትራ የተመለሰው በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ‹‹ሸኔ›› የተባለው የኦነግ ቡድን፣ ከኤርትራ ይዞት ከመጣው ውጪ ሠራዊቱን ካምፕ ባለማስገባቱና ዛሬ ነገ እየተባለ በባከነው ጊዜ ምክንያት ከባድ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ፡፡ ዓርብ ጥር 3 ቀን 2011 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የአገር መከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹምና […]
Read More →በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው የታሰሩ የደኅንነት ሠራተኞች የሚስጥር ስም ‹‹አቤ ከቤ›› እንደነበር ተገለጸ
በቂሊንጦ ቃጠሎ በወቅቱ የነበሩ የፍትሕ ሚኒስቴር ኃላፊዎችም መጠየቅ አለባቸው ተባለ በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሠራተኞች የነበሩ ግለሰቦች የሚስጥር ስም፣ ‹‹አቤ ከቤ›› እንደነበር ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤት ተናገረ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 943/2008 ድንጋጌ ሥልጣን እንደተሰጠው በመግለጽና በችሎት ተገኝቶ እንደ መርማሪ ፖሊስ ሆኖ መከራከር […]
Read More →በምዕራብ ጎንደር በተፈጠረው ግጭት የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ድንበር ላይ ቆመዋል
ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በተፈጠረ ግጭት ሳቢያ፣ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ነዳጅ የሚያመላልሱ የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች መተማ ከተማ ለመቆም እንደተገደዱ ተገለጸ፡፡ ማክሰኞ ታኅሳስ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውኃ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት አባላትና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ግጭት ተፈጥሮ የሰው ሕይወት ከጠፋ በኋላ የፀጥታ ሥጋት በመጋረጡ ምክንያት፣ ከሱዳን ቤንዚን ጭነው ወደ […]
Read More →የቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ አምስት ኃላፊዎች በሙስና ወንጀል ተከሰሱ
በመንግሥት ላይ ከ319.4 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብሏል ሥልጣናቸውን ያላግባብ ተገልግለው በመንግሥት ላይ ከ319.4 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ፣ አምስት ኃላፊዎችና ሦስት በግል ሥራ ተሰማርተዋል የተባሉ ግለሰቦች ላይ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ጥር 2 ቀን 2011 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት […]
Read More →በሙስና ወንጀል የተከሰሱ የአቢሲኒያ ባንክ ሠራተኞች ጥፋተኛና ነፃ ተባሉ
ትክክለኛውን የስዊፍት መክፈያ መልዕክት መለያ ቁጥር፣ የተቀባይን ስምና አድራሻ በማስተካከል፣ ሌሎችንና ራሳቸውንም ለመጥቀም በአቢሲኒያ ባንክ ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው የተከሰሱ አራት ሠራተኞች ጥፋተኛና ነፃ ተባሉ፡፡ የወንጀል ድርጊቱን ፈጽመዋል ተብለው በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት፣ በኢቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ዓለም አቀፍ የባንኮች ግንኙነት መምርያ የትራንስፈር ሰርቪስና ኮሮስፖንዲንግ ባንኪንግ ኦፊሰር ወ/ሮ ሔለን አሰፋ፣ የትራንስፈር […]
Read More →ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሪዮስ ዛሬ ጐንደር ይገባሉ
ህዝቡ በጉጉት ይጠብቃቸዋል ተብሏል ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሪዮስ ዛሬ ጐንደር የሚገቡ ሲሆን ከ27 ዓመታት በኋላ የጐንደርን መሬት ይረግጣሉ ተብሏል፡፡ የአቀባበሉ ኮሚቴ አባል ዲያቆን አደራጀው አዳነ ለአዲስ አድማስ እንደገለፀው የጐንደር ህዝብ በጉጉት ነው የሚጠብቃቸው፡፡ ለፓትሪያሪኩ ከጐንደር አፄ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ፋሲል ግንብ አጠገብ እስከሚገኘው አደባባይ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ድረስ በበርካታ ህዝብና ተሽከርካሪዎች ታጅበው እንደሚጓዙ የተገለፀ ሲሆን፤ […]
Read More →በጎንደር የንፁሃን ህይወትን ያጠፉ በህግ ይጠየቃሉ ተባለ
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር በገንዳ ውሃ ከተማ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ህፃናትን ጨምሮ 8 ሰዎች የሞቱበትን ሁኔታ የሚያጣራ ቡድን ወደ ሥፍራው እንደሚላክ የገለፀው የአማራ ክልል መንግስት፤ ያልተመጣጠነ ኃይል የተጠቀሙ በህግ ይጠየቃሉ ብሏል፡፡ በአካባቢው በመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ላይ ተሰማርቶ የነበረው ሱር ኮንስትራክሽን ድርጅት፣ ተሽከርካሪዎቹን ለማንቀሳቀስ በሞከረበት ወቅት በተፈጠረ አለመግባባት ክስተቱ መፈጠሩን የጠቆሙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ […]
Read More →ላለፉት 2 ወራት በብሄር በግጭት ሳቢያ የ256 ዜጐች ህይወት ጠፍቷል ለጠፉት ህይወት ዳውድ ኢብሳ ተጠያቂ ነው
በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በተፈጠሩ ግጭቶችና በተሰነዘሩ ጥቃቶች ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ 256 ዜጐች መገደላቸውን የሠብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሠመጉ) አስታወቀ፡፡ የተለያየ መነሻ ምክንያት ባላቸው ብሔር ተኮር ግጭቶች ሳቢያ የሰው ህይወት በከንቱ እየጠፋ መሆኑ እንዳሳሰበው የገለፀው ሠመጉ፤ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል ክልሎችና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በህዳርና ታህሳስ 2011 ዓ.ም በተፈጠሩ ግጭቶች 256 ሰዎች መገደላቸውንና በአስር ሺዎች […]
Read More →Sidama referendum should proceed without further delay
After the Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF) assumed power in 1991, the Sidama nation was granted regional self-administration. This proved to be short-lived. Five districts of the south were then merged together without due consultation to construct the Southern Nations Nationalities and Peoples’ Regional State (SNNPRS). However, the constitution provides the right to statehood, […]
Read More →