አምነስቲ ኢንተርናሽናል በወጣው ሪፖርት ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ምልከታና ግኝቶቹን ይፋ አደረገ
አምነስቲ ኢንተርናሽናል በወጣው ሪፖርት ተከትሎ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያካሄደውን ምልከታ እና ግኝቶች ይፋ አደረገ። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ይህን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል። የመግለጫው ሙሉ ቃል በግንቦት 2012 ዓም አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተሰኘው ድርጅት “Beyond Law Enforcement: Human Rights Violations by Ethiopian Security Forces in Amhara and Oromia”. በሚል ርዕስ የሰብዓዊ መብት ሪፖርት አውጥቷል። የሪፖርቱን መውጣት ተከትሎ […]
Read More →የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴው ግድብ ለሚያደርጉት ድርድር ስኬታማነት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ
የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚያደርጉት ድርድር ስኬታማነት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡ በአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና የደህንነት ክፍል ተወካይ እንዲሁም የህብረቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ቦሬል በህዳሴው ግድብ ዙሪያ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም ሶስቱ ሃገራት ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ እያደረጉት ላለው ድርድር ስኬታማነት ህብረቱ ድጋፉን ያደርጋል ብለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም ሃገራቱ የጋራ መግባባት […]
Read More →“በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አገር ውስጥ ያለውን ህዝብ “ተነስ ውጣ” ከሚሉ የግጭት አነሳሽ መልዕክቶች ይልቅ ለአገር ሰላምና አንድነት የሚጠቅሙ ስራዎች ላይ እገዛ ማድረግ ይኖርባቸዋል” ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ።
“በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አገር ውስጥ ያለውን ህዝብ “ተነስ ውጣ” ከሚሉ የግጭት አነሳሽ መልዕክቶች ይልቅ ለአገር ሰላምና አንድነት የሚጠቅሙ ስራዎች ላይ እገዛ ማድረግ ይኖርባቸዋል” ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ። በተለያዩ አለም አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለአገሪቱ ልማት፣ ዴሞክራሲና ሰላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ። በዚያው ልክ በአገሪቱ ያለውን ሰላም ለማደፍረስ ከውጭ ሆነው ‘ተነስ […]
Read More →የፌደራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ያደረጉትን የችሎት ስራ ሃምሌ 13 ቀን ይጀምራሉ
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በከፊል ዝግ ያደረጉትን የችሎት ስራ ከሃምሌ 13 ቀን ጀምሮ በየደረጃው መደበኛ ችሎት ሊጀምሩ ነው፡፡ በዚህም ከሃምሌ 13 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረሰ በሁሉም ፍርድ ቤቶች የመልስ መልስ፣ አስተያየቶች፣ የትዕዛዝ ውጤቶችን ለመቀበል የተቀጠሩ እንዲሁም እልባት ለመስጠት ጥቂት ሂደት የቀራቸው ጉዳዮች እና እስረኛ ያላቸው መዛግብት በየቀጠሮ […]
Read More →5910 ጀነሬተሮች ርክክብ መደረጉን እና የመስኖ አገልግሎት ለማስፋፋት ጠቃሚ መስመር መዘርጋቱን ተገለጸ
ውሃ ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ የማይተካ ሚና ያለው ውድ ሃብት በመሆኑ ሁሉም በአግባቡ መጠበቅና መጠቀም እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ ገለጹ። 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የውሃ መሳቢያ ሞተር ፓምፖች ለሁሉም ክልሎች ማከፋፈል ጀምሯል። የውሃ፤ መስኖና ኢነርጂ እንዲሁም የግብርና ሚኒስቴሮች በጋራ በመሆን የኮሮና ወረርሸኝ በግብርናው ዘርፍ ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ መቀነስና ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ […]
Read More →በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ በተከሰተው ሁከትና ግርግር የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች ተያዙ
በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ በተከሰተው ሁከትና ግርግር የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች ተያዙ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ ሰሞኑን በተከሰተው ሁከትና ግርግር አጥፊዎች ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የጦር መሣሪያዎች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ። በባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ከበደ እንደገለጹት÷ በወረዳው ለጥፋት የተንቀሳቀሰው ቡድን ሲገለገልባቸው የነበሩ የጦር መሣሪያዎች […]
Read More →ኢትዮጵያ የጎብኚዎች መዳረሻ ስፍራዎቿን በኦን ላይን ማስተዋወቅ ጀመረች
የኢትዮጵያን የጎብኚዎች መዳረሻ ስፍራዎች በኦን ላይን ማስተዋወቅ መጀመሩን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ የቱሪዝም ዘርፉ ኮሮና ወረርሽኝ ያሳደረበትን ተጽዕኖ የሚያገግምበትን አቅጣጫ በማስቀመጥ 3 በሊዮን ዶላር ለማግኘት ማቀዱን በሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ተወካይ አቶ እንደገና ደሳለኝ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡ በተጠናቀቀው በጀት አመት በኢትዮጵያ ኮሮና ባስከተለው ቀውስ ከዘርፉ ለማግኘት ከታቀደው ሁለት ሦስተኛውን ገቢ ብቻ ማሳካት መቻሉንም ዳይሬክተሩ […]
Read More →በደምቢዶሎ “ተማሪዎችን አግተዋል” በሚል የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦች በሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው
****************** በደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የነበሩና ወደ ቤተሰቦቻቸው በመጓዝ ላይ የነበሩ “ተማሪዎችን አግተዋል” በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦች በዛሬው ዕለት በሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው ፡፡ በእነ ከሊፋ አብዱረሂማን በሚጠራው የክስ መዝገብ ውስጥ 17 ግለሰቦች በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ 3 ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት ክሱን አድምጧል፡፡ ህዳር 24 እና 25 ፣2012 በደምቢ […]
Read More →በለንደን ከፍተኛ የሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
በሃጫሉን ግድያ አስመልክቶ በሃገራችን ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ አካባቢ በግፍ የተገደሉትን ንጹሃንን በማሰብ እና ለተደረገው የዘር ማጥፋት ወንጀልን በመቃወም እና ፍትህን ለማግኘት ያስችል ዘንድ ኢትዮጵያውያኖች በእንግሊዝ አደባባይ መውጣታቸው ተገልጿል። በዛሬው እለት ከማለዳው ጀምሮ ሲተም የነበሩት ኢትዮጵያውያኖች አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ባንዲራ በማውለብለብ የህዝባቸው የሃገራቸው አለኝታ የሆነውን አርማ ይዘው መንቀሳቀሳቸውን ገልጸዋል። ይህም ሆኖ ሳለ በአሁን ሰአት የሃጫሉ መገደል […]
Read More →