ዩቲዩብ (YouTube) ብዙ ቪዲዮዎች ላይ ማስታወቂያዎች ማሳየት እንደሚጀምር ገልጿል
ዩቲዩብ (YouTube) ብዙ ቪዲዮዎች ላይ ማስታወቂያዎች ማሳየት እንደሚጀምር እና ለሁሉም ማስታወቂያ ግን ክፍያ ላይፈጽም እንደሚችል አስታውቋል። ኩባንያው በአሁኑ ወቅት የማስታወቂያ ገቢውን በሽርክና መርሃ ግብሩ ላይ ከተመዘገቡ ቪዲዮ ሠሪዎች ጋር ይጋራል። ከዚህ በኋላ ግን ዩቲዩብ የሽርክና መርሃ ግብሩ አካል ያልሆኑ በአንዳንድ ቪዲዮዎች ላይም ማስታወቂያዎችን ማስገባት እጀምራለሁ ብሏል። በአገልግሎት ውሉ ላይ በተደረጉ ለውጦች ምክንያት ዩቲዩብ ከማስታወቂያዎቹ የሚገኘውን […]
Read More →ከድባጤ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ዕርዳታ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን ገለጹ!
በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በምግብ፣ በአልባሳት እና በመጠለያ እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ለአብመድ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ የተጠየቀው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለተፈናቃዮች አስቸኳይ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ታረቀኝ ተሲሳ ከኅዳር 5 ጀምሮ ከተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በድባጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ 1 […]
Read More →የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ሱዳን ድርድሩን አልማማበትም ማለቷ ተገልጿል !!
ታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በኢትዮጵያ፣ በግብጽ እና በሱዳን በውሃ ሚኒስቴሮች ደረጃ ሊካሄድ ለዛሬ ቀጠሮ በተያዘለት ድርድር ላይ ሱዳን እንደማትገኝ በደብዳቤ አስታውቃለች። ለዚህም ምክንያቷ የአፍሪካ ህብረት ባለሞያዎች የተሰጣቸው የአደራዳሪነት ሚና ዝቅተኛ ነው የሚል እንደሆነ የሱዳን ዜና አገልግሎት ሱና ዘግቧል፡፡ የሱዳን ወገን የድርድሩ አካሄድ ካልተለወጠ በድርድሩ አልሳተፍም የሚል አቋም በባለፈው ድርድር ወቅት ማንጸባረቋን የኢትዮጵያ የውሃ መስኖና ኢነርጂ […]
Read More →መንግስት ከህወሓት ወንጀለኞች ጋር ድርድር አይቀመጥም – አቶ ደመቀ መኮንን
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ከህወሓት ወንጀለኞች ጋር ለድርድር እንደማይቀመጥ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ። አቶ ደመቀ መኮንን ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አን ሊንዴ ጋር በስልክ ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ በውይይታቸው በዋናነት መንግስት በትግራይ ክልል እየወሰደ ባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ትኩረት አድርገው መምከራቸውን ከውጭ […]
Read More →በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ ተሰጠ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለሚድያ አካላት ማብራሪያ ሰጥተዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ በትግራይ እየተካሄደ ስላለው የሕግ ማስከበር ሥራና አስተዳደሩ በትግራይ ክልል ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራቸውን ስራዎች በተመለከተ አብራርተዋል፡፡ በጊዜያዊ አስተዳደሩም […]
Read More →በመዲናዋ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ 19 ቦንብና ሌሎች በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ
በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የተከማቹ 19 ቦንቦችና እና ሌሎች በርካታ የጦር መሳሪያዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የጦር መሳሪያ አከማችተው በሚገኙ ተቋማት ላይ የሚደረጉ ፍተሻዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ኮሚሽኑ ገልጿል። የጥፋት ሃይሎች ለመዲናዋ የደገሱላትን ሽብርና እልቂት ለመቀልበስ የሚከናወነው ጠንካራ ህግን የማስከበር ተግባር በህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት መረጃ ሰጪነት እየታገዘ […]
Read More →በአማራ ክልል ለቤተ እምነቶች ጥበቃ ሊደረግ እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ
በአማራ ክልል ለቤተ እምነቶች ጥበቃ ሊደረግ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከጸጥታ አካላት ባገኘው መረጃ መሰረት፣ የኦርቶዶክስ አልባሳት ለብሶ መስጅድ፣ እንዲሁም የሙስሊም አልባሳት ለብሶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት ለመፈፀም ተልዕኮ የያዙ አካላት ወደ ክልሉ ገብተዋል። በመሆኑም በክልሉ ያሉ ሁሉም አማኞች ቤተ እምነታቸውን በመጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
Read More →የሃይማኖት አባቶች የእርስ በእርስ ግጭቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲቆም ጠየቁ !
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። ከነገ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ለአንድ ሣምንት የሚቆይ ጸሎትና ምህላ በሁሉም እምነት ተቋማት እንደየ እምነት ስራቱ እንዲከናወን ተገልጿል። የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ክልል መንግስት ከሁሉም በፊት ቅድሚያ ለሀገር ሠላም እና መረጋጋት በመስጠት በመካከላቸው የተጀመረውን የእርስበርስ ግጭት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ […]
Read More →የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አጸደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመቀበልና ለማጽደቅ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል፡፡
Read More →ፌዴሬሽን ምክርቤት ለቅዳሜ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ
ምክር ቤቱ 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ አስቿኳይ ስብሰባ ቅዳሜ ጥቅምት 28 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ይካሄዳል ተብሏል፡፡ የፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት ጥቅምት 27 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም በፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።
Read More →