”ህወሓት በአባላቶቼ ላይ ለሚያደርሰው ግፍና ጭቆና መፍትሄ ይሰጠኝ” ሲል የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ት-ዴ-ፓ) ጠየቀ።
ፓርቲው አቤቱታውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በደብዳቤ ማሳወቁን ጠቁሟል። የፓርቲው ሊቀ-መንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ፓርቲው መሰረቱን ትግራይ ክልል በማድረግ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ነጻነት፣ እኩልነትና ብልጽግና የሚታገል ነው ሲሉ ገልጸዋል። ለዚህም አባላቶቹን በመመልመልና በማብቃት በትግራይ ክልል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። ይሁንና አባሎቻቸው ላይ በተደጋጋሚ ችግር እየደረሰ መሆኑንና […]
Read More →የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰማንያ ሰባተኛው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በዚህም መሠረት፡- ም/ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በገንዘብ ሚኒስቴር የቀረቡትን የተለያዩ የብድር ስምምነቶች የማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡ ሁለቱ የብድር ስምምነቶች የተደረጉጉት ከኮሪያ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ ጋር ሲሆን አላማቸውም ለኮሮና ቫይረስ (COVID-19) አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ የበጀት ድጋፍ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ እና ለኮሮና ቫይረስ (COVID-19) የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች አቅርቦት ማስፈጸሚያ የሚውሉ ናቸው፡፡ ሶስተኛው የብድር ስምምነት ከዳንስኬ ባንክ ኤ.ስ ጋር የተደረገ […]
Read More →አምነስቲ ኢንተርናሽናል በወጣው ሪፖርት ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ምልከታና ግኝቶቹን ይፋ አደረገ
አምነስቲ ኢንተርናሽናል በወጣው ሪፖርት ተከትሎ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያካሄደውን ምልከታ እና ግኝቶች ይፋ አደረገ። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ይህን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል። የመግለጫው ሙሉ ቃል በግንቦት 2012 ዓም አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተሰኘው ድርጅት “Beyond Law Enforcement: Human Rights Violations by Ethiopian Security Forces in Amhara and Oromia”. በሚል ርዕስ የሰብዓዊ መብት ሪፖርት አውጥቷል። የሪፖርቱን መውጣት ተከትሎ […]
Read More →“በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አገር ውስጥ ያለውን ህዝብ “ተነስ ውጣ” ከሚሉ የግጭት አነሳሽ መልዕክቶች ይልቅ ለአገር ሰላምና አንድነት የሚጠቅሙ ስራዎች ላይ እገዛ ማድረግ ይኖርባቸዋል” ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ።
“በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አገር ውስጥ ያለውን ህዝብ “ተነስ ውጣ” ከሚሉ የግጭት አነሳሽ መልዕክቶች ይልቅ ለአገር ሰላምና አንድነት የሚጠቅሙ ስራዎች ላይ እገዛ ማድረግ ይኖርባቸዋል” ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ። በተለያዩ አለም አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለአገሪቱ ልማት፣ ዴሞክራሲና ሰላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ። በዚያው ልክ በአገሪቱ ያለውን ሰላም ለማደፍረስ ከውጭ ሆነው ‘ተነስ […]
Read More →ኢትዮጵያ የጎብኚዎች መዳረሻ ስፍራዎቿን በኦን ላይን ማስተዋወቅ ጀመረች
የኢትዮጵያን የጎብኚዎች መዳረሻ ስፍራዎች በኦን ላይን ማስተዋወቅ መጀመሩን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ የቱሪዝም ዘርፉ ኮሮና ወረርሽኝ ያሳደረበትን ተጽዕኖ የሚያገግምበትን አቅጣጫ በማስቀመጥ 3 በሊዮን ዶላር ለማግኘት ማቀዱን በሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ተወካይ አቶ እንደገና ደሳለኝ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡ በተጠናቀቀው በጀት አመት በኢትዮጵያ ኮሮና ባስከተለው ቀውስ ከዘርፉ ለማግኘት ከታቀደው ሁለት ሦስተኛውን ገቢ ብቻ ማሳካት መቻሉንም ዳይሬክተሩ […]
Read More →በደምቢዶሎ “ተማሪዎችን አግተዋል” በሚል የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦች በሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው
****************** በደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የነበሩና ወደ ቤተሰቦቻቸው በመጓዝ ላይ የነበሩ “ተማሪዎችን አግተዋል” በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦች በዛሬው ዕለት በሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው ፡፡ በእነ ከሊፋ አብዱረሂማን በሚጠራው የክስ መዝገብ ውስጥ 17 ግለሰቦች በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ 3 ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት ክሱን አድምጧል፡፡ ህዳር 24 እና 25 ፣2012 በደምቢ […]
Read More →በሚኒሶታ-ሚድዌስት የኢፌዴሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የኮቪድ-19 የድጋፍ አሰባሰብ ወቅታዊ ሪፖርት
መግቢያየኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ቫይረሱ በአገራችን የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቋቋም አቅጣጫ መውረዱ ይታወሳል። በሚድዌስት ከሚገኙ የተለያዩ ከዳያስፖራ አደረጃጀቶች ጋር ቴሌ-ኮንፈረንሶችን በማካሄድ ኮሚቴ በማደራጀት በአገሩ አሰራር GoFundMe ሂሳብ በመክፈት፣ የህክምና ቁሳቁሶችን በኢትዮዽያ አየር መንገድ እንዲጓጓዝ ዋሽንግተን ዲሲ ወደ ሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ ትዕዛዙ እንዲደርስ በማድረግና በየስቴቱ የተዋቀረው ኮሚቴ ገንዘብ በመሰብሰብና በማስተባበር ወደ አገር ቤት ገንዘቡ እንዲላክ በማድረግ ላይ […]
Read More →የአማራ ባንክ አክስዮን ሽያጭ ለአምስት ሳምንት ተራዘመ፡፡
ዛሬ የሚጠናቀቅ የነበረው የአማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የአክሲዮን ሽያጭ ለአምስት ሳምንታት መራዘሙን አደራጅ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በ”ፋይናንስ ሴክተሩ”እንዲሳተፉ የተመለከተውን አዋጅ መሠረት አድርጎ መመሪያ የወጣው የካቲት 20/2012 ዓ.ም ላይ እንደሆነ አደራጅ ኮሚቴው ዛሬ በሰጠው መግለጫ አመላክቷል። ይህም ማለት የባንኩ የአክሲዮን ሽያጭ ማጠናቀቂያ እንደሆነ ተገልጾ ከነበረው የካቲት 30/2012 ዓ.ም በ10 ቀናት ብቻ የቀደመ ነው። ይህም በቂ […]
Read More →የኢትዮጵያን አትሌቶች ማንኛውም አትሌት የፈለገውን ባንዲራ ይዞ መውጣት ይችላል ሲሉ ገለጡ!
በችካጎ ማራቶን በተከናወነው የማራቶን ሩጫ ላይ የሁለተኛ ደረጃ ላይ አሸናፊ የሆኑት ደጀን ደበላ እና አሰፋ መንግስቱ ፣ ማንኛውም ሰው በሩጫው ወቅት የፈለገውን ባንዲራ ይዞ መሮጥ አለበት ሲሉ ተደምተዋል በተለይም ሃገርን ወክሎ እና የሃገርን ባንዲራ ማውለብለብ በሚቻልበት ወቅት ፣ የአሸባሪ ቡድን ባንዲራ ይዞ መገኘትም እንደፍላጎትህ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በተለይም አትሌት አሰፋ መንግስቱ ሰው የፈለገውን ይዞ የመምጣት […]
Read More →