ከአማራ ብሐራዊ ንቅናቄ(አብን) የተሰጠ መግለጫ፤
ድርጅታችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተፈፀመው «የዘር ማጥፋት ወንጀል» እንደሆነ በመግለፅ በጥፋቱ የተሳተፉ፣ ሕዝቡን ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ የመንግስት አመራሮችም በጉድለታቸው ልክ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እና ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን የመልሶ ማቋቋም ስራ እንዲሰራ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። አብን ጥቃቱ መፈፀም ከጀመረበት ዕለት አንስቶ የነቃ ክትትል በማድረግ በርካታ ወገናዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል። ጥቃቱ […]
Read More →በመቀለ ‘ሕገወጥ ሰልፍ ሊያካሂዱ ሲሉ ተይዘዋል’ የተባሉ ዘጠኝ ወጣቶች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው!
በመቀለ ‘ሕገወጥ ሰልፍ ሊያካሂዱ ሲሉ ተይዘዋል’ የተባሉ ዘጠኝ ወጣቶች ላይ የትግራይ ፓሊስ ምርመራውን በመጨረሱ ፋይላቸውን ክስ እንዲመሰረት ወደ ዐቃቤ ሕግ ማስተላለፉን ገልጿል። ከዚህ ቀደምም ሦስት ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረባቸውንና ከሰባት ቀን በኋላ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ነው ቢቢሲ የዘገበው። እንደ ቢቢሲ ዘገባ ወጣቶቹ ከ46 ቀናት በፊት፣ ሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ በመቀለ የሮማነት አደባባይ ላይ መንግሥትን በኃይል ለመጣል […]
Read More →ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ በህወሓትና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ያለው ፍጥጫ በንግግር ሊፈታ ይገባል ሲል መክሯል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የሠላም ኖቤል ተሸላሚው ዐቢይ አሕመድ አስታራቂና የሚያቀራርቡ ንግግሮቻቸውን ወደ ተግባር እንዲለውጧቸው ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ጠይቋል። ቡድኑ በተጨማሪም ያለውን ውጥረት ለማርገብ አስፈላጊ ከሆነም የአፍሪካ ሕብረት ወይም የአፍሪካ መሪዎች በማሸማገሉ በኩል ተሳትፎ ሊያደርጉ ይችላሉ ከማለት በተጨማሪ በተለይ የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ ብሏል። ኢንተርናሽናል […]
Read More →የቀድሞው ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ የጥበቃ ኃላፊ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት እሳቸውም እራሳቸውን አግልለዋል!!
የቀድሞው ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ የጥበቃ ኃላፊ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ሲሆን እሳቸዉ እና ቤተሰቦቻቸው በተደረገላቸዉ ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መባላቸዉን በቲዉተር ገፃቸዉ ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ራሳቸውን አግልለዋል! ትናንት ምሽት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተተረከ ዘጋቢ ፊልም ምርቃት መርሀ ግብር ላይ በክብር እንግድነት ተጋብዘው መገኘት ያልቻሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በኮሮና ቫይረስ በመጠርጠራቸው […]
Read More →የግድቡ ውኃ ሙሌት መካሔድ የህወሓትን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ያከሸፈ መሆኑ ተገለጸ
***************************************** የህዳሴው ግድብ ውኃ ሙሌት ህወሓት በፕሮጀክቱ ላይ የሚነዛውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ያከሸፈ ነው ሲሉ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለፁ። ርእሰ መስተዳድሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ግድቡ የመጀመሪያ ዙር ውኃ ሙሌት ላይ በመድረሱ መላው ኢትዮጵያዊያንን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። ግድቡ ባጋጠሙት ችግሮች ግንባታው መዘግየቱን ያስታወሱት አቶ አሻድሊ የውኃ ሙሌት እንዲጀመር የለውጥ ኃይሉ የኢትዮጵያ […]
Read More →አሜሪካ ሶማሊያ በሚገኙ የአይ.ኤስ.አይኤስ ታጣቂዎች ላይ የአየር ጥቃት ሰነዘረች
************************************ የአሜሪካ ጦር ኃይል ማክሰኞ ዕለት ሶማሊያ ውስጥ በሚገኙ እና አሜሪካ በምትደግፋቸው ኃይሎች ላይ ጥቃት የፈጸሙ የአይኤስአይኤስ ታጣቂዎችን ዒላማ ያደረገ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ሲኤንኤን አስነብቧል። “የአሜሪካ-አፍሪካ ኮማንድ የሶማሊያ አይኤስአይኤስ አሸባሪዎች ላይ የአየር ጥቃቱን የፈጸመው ሐምሌ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ቲምሪሽ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የኮማንዱ አጋር ኃይሎች ላይ ቡድኑ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ መሆኑን” የአፍሪካ ኮማንዱ ረቡዕ […]
Read More →የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያለው እንቅስቃሴ በስኬት የታጀበ መሆኑን ማሳያ ነው _ ምሁራን
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር ውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ኢትዮጵያ እያደረገች ያለው እንቅስቃሴ በስኬት የታጀበ መሆኑን በግልፅ እንደሚያሳይ የውሃ ጂኦ ፖለቲካ እና የህግ ጉዳይ ምሁራን ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አብስረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጉዳዮች እና የኦሬንታል ጥናት ማዕከል መምህር […]
Read More →የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት ተጠናቀቀ
********************************** የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የውሃ ሙሌቱ በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ክረምቱ ገና ሳይገባደድ የመጀመሪያው ዙር ሙሌቱ በጥቂት ቀናት ሞልቶ መጠናቀቁና መፍሰስ መጀመሩ ለአገሪቱ ትልቅ የድል ምዕራፍ መክፈቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል። ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ ላደረገው የኢትዮጵያ ህዝብና በድርድር ሂደት […]
Read More →የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቤጂንግ እሳት አደጋ ደረሰበት
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በሻንጋይ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እቃ በሚጭነበት ወቅት በእሳት ተያያዘ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በቻይና ሻንጋይ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እቃ በሚጭነበት ወቅት በእሳት ተያያዘ። አየር መንገዱ አደጋውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ቦይንግ 777 ኢቲ ኤአርኤች እቃ ጫኝ አውሮፕላን እቃ ሲጭን በነበረበት ወቅት በእሳት መያያዙን ገልጿል።
Read More →ከለይቶ ማቆያ የሚያመልጡ የኮቪድ-19 ተጠርጣሪዎች መኮብለል!
በጋምቤላ ክልል በኮሮና የተጠረጠሩ ሰዎች ከለይቶ ማቆያ እየጠፉ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ማስታወቁን ዶቼ ቨለ አስነብቧል። የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ኡጁሉ እንደተናገሩት በለይቶ ማቆያነት ከሚያገለግለው ከጋምቤላ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ጊዜያት ያመለጡ ሰዎች ቁጥር 18 ደርሷል። ሰዎቹን ፈልጎ ማግኘቱ አስቸጋሪ እንደሆነ የጠቀሱት ሃላፊው ከመካከላቸው እስካሁን የተገኘ አለመኖሩን አስረድተዋል። የክልሉ ነዋሪዎች በሽታው የለም መመርመሪያውም በትክክል […]
Read More →